በክፍል ሁለት ላይ የጌታ እናት ድንግል ማርያም በሰርጉ ቤት የተከሰተውን ክፍተት/ጉድለት ልጇ እንዲሞላላት መጠየቋን በተያያዘ የሚነሱ ሀሳቦችን ተመልክተናል። በዚህ ክፍልም ያልዳሰስናቸውን ሁለት ነገሮች ላይ ትኩረት እናድርጋለን።
" የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። " (ዮሐ 2፥3)
'' የወይን ጠጁ አልቆባቸዋል አለች። ''
ይህን የድንግል ማርያም ጥያቄ ያለ አግባብ ተለጥጦና ተመናፍሶ በዓለም ላያ የሚኖረውን የሰው ዘር በሙሉ ከዘላለም የሞት ፍርድ የሚያድን ምልጃ አድርገው የሚያስተምሩ አሉ። ይህ '' አልቆባቸዋል '' ወይም '' የላቸውየ '' የሚሰራው (Addressed የሚያደርገው) ላለቀው የወይን ጠጅ ብቻ እንጂ በኃጢአት ባርነትና በሞት ቀጠና ውስጥ የተዘፈቀውን የሰውን ልጅ የነፍስ ጉዳይ የሚመለከት አይደለም። ይሄ ዓለምን ያናጋ የሰውን ልጅ ሕይወት እንደቀየረ ተደርጎ የጌታን ወደ ምድር መምጣት የሚያደብዘዝ የሰውን ማስተዋል ያጨለመ ድፍን ውሸት ነው። ይሄ ከነፍስ ጥያቄ ጋር የሚያገናኘው አንዳች ጉዳይ የለውም።
የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣላበት ምክንያት ኃጢአት ነው ምልጃም ካስፈለገው በዚህ ጉዳይ እንጂ በሰርግ ቤት ውስጥ ባለቀ የወይን ጠጅ ፍጆታ አይደለም። በሰርጉ ላይ ምልጃ ያስፈልገዋል ብለን ልናነሳው የምንችለው ምንም ዓይነት ጥል የለም። እንደውም ጌታ በዚህ ሰርግ ላይ በወዳጅነት ነው የታደመው። ስለሆነም የወይን ጠጅ በማለቁ ከጌታ ጋር የተገባ ጥል ባለመኖሩ ምልጃ ልንለው እንኳ አንችልም።
ሲቀጥልም ይሄ ጥያቄ ምልጃ ነው እንኳ ብንል አሁን ካለው የምልጃ ፅንሰ ሀሳብ ጋር ፍፁም አይገናኝም። በሰርጉ ላይ ድንግል ማርያም በስጋዊ ሕይወት እያለች የተከናወነ ሲሆን አሁን በአፀደ ነፍስ እያለች አማላጅ ለማድረግ ይህን መጥቀስ በፍፁም አያስኬድምም ተገቢም አይደለም።
እረ ለመሆኑ ሌሎች ለጌታ የቀረቡትን ተማፅኖዎች ምን እንበላቸው? ለአብነት ያህል በማርቆስ ወንጌል 5፥22-43 (ሙሉውን እንድታነቡት እየመከርኩ) የምናገኘውን የምኩራብ አለቃ ጌታን የጠየቀው ጥያቄ የሞተችውን የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ ብላቴናን ከሞት ያስነሳው ምልጃ ምን ሊባል ነው? በቅንነት አስቡት።
እንደ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን እንደ ባለ አእምሮ ብናስበው ውሃን ወደ ወይን ጠጅ መቀየር ወይስ የሞተን ማስነሳት ያስገርመናል? እንደኔ ግን ሁለቱም ጌታ ሁሉን ቻይ በመሆኑና በኃይሉ ብዛት በችሎቱም ብርታት እንድስኳ የሚሳነው እንደሌለው እርግጥ ቢሆንም እጄን በአፌ የሚያስጭነኝ ግን የሞተን ማስነሳት ነው።
እንደ ዘመኑ የምልጃ አራጋቢዎች ቢሆን ኖሮ የምኵራብ አለቃው የኢያኢሮስ ምልጃ ዛሬም እየተወሳ አንዱ አማላጃችን አድርገውት ወርሃዊና ዓመታዊ የበአል ቀን ተሰይሞለት ባየን ነበር ነገር ግን በብልሃት አድርጎ ተረት የፈጠረው ዲያብሎስ አዋጭነቱ ላይ አላመነበትም ለማለት እገደዳለው።
'' የኢየሱስ እናት ''
ዮሐንስ ድንግል ማርያምን በቀራኒዮ መስቀል ስር ከጌታ አደራ የተሰጠው እናቱ እንደመሆኗ ደግሞም ወደ ቤቱም እንደወሰዳትና አብረው እንደመኖራቸው መጠን ጠለቅ ያለ ግንኙነት (የእናት ልጅ) ይኖራቸዋል ነገር ግን በወንጌሉ ላይ አንድም ቦታ በስሟ ወይም አሁን ዘመን ላይ እየተነሳች ባለው ልማድ መልኩ አልጠቀሳትም ለምን ይሆን? የእኔ ጥያቄ ነው።
እንደኔ መረዳት ግን በየትኛውም መልኩ ከመግለፅ የጌታ ወይም የኢየሱስ እናት ማለቱ የበለጠ ይገልጣታል እላለው። መቼም እንደ ባለ ዘመናችን ሰባኪያንና ቲቮዞአዊያን የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት (ሲያሻቸውም የዘርዓ ያዕቆብ አምላክ ሲሏትም በጆሮዬ ሰምቻለው) ማለት ድንግል ማርያምን ከማቅለል ባለፈ አላየውም። አዎ ኢየሱስን መውለዷ ማንም የሚቀማት ወይም የሚጋራት የለም። እሱን በመውለዷ ብቸኛ ፀጋ አላት። ይህንን ግን አውርደው ወንጌል እንኳ ባልተጠቀመበት መንገድ መጥራት ወንጌሉን መፃረር ነው።
ይቀጥላል..................
ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌ 2፥4-5
Monday, 31 December 2018
Wednesday, 26 December 2018
የጌታ ክብር መገለጥ (ክፍል ሁለት)
በክፍል አንድ የምንነጋገርበትን የፅሐፍ ሀሳብ እንደ መግቢያ እንዳየን የሚታወስ ነው። እነሆ አሁን ደግሞ ቃል በቃል ያለውን ሀሳብ እናያለን። የማስተዋል መንፈስ፣ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ መንፈስ፣ የምክርና የኃይል መንፈስ፤ መንፈስ ቅዱስ ሁላችንንም ይርዳ።
#ማሳሰቢያ:- የእግዚአብሔርን ክብር መግለጥ ማለት የቅዳሳንን ክብር ማቅለል አይደለም። ቀድሞውኑ የሰው ልጅ ምን ክብር አለውና የቅዱሳን ክብር እግዚአብሔር አይደለምን?
" በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። "
በዚህ ምንባብ ሶስት ሀሳቦች ላይ ጥያቄ በመመለስ እናያለን።
ሀ) ድርጊቱ የተፈፀመው የት ነው?
ቃና ከናዝሬት ሰባት ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን እስራኤል የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች። ቃና ዘገሊላ የተባለችው ሌላ ቃና የሚባል ስፍራ ስላለ ለመለየት ሲባል ነው። ይህ ማለት የኮተኬ ካራና የአየር ጤና ካራ እንደማለት ነው። ገሊላ ደግሞ ጌታ ያደገበት ስፍራ ወይም አቅራቢያ መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም። ከዚህም በመነሳት ለሰርግ ጥሪው የቅርብ ሰው እንደሆነ መረዳት እንችላለን። እናቱ ድንግል ማርያም በዛ አካባቢ የምትታወቅና ለሰርጉ ቤተ ሰዎች የቅርብ ሰው እንደሆነች ታሪኩ ያሳያል። ይህን ማወቅ ታሪኩን በትክክል እንድንረዳ ይጠቅመናል። በእርግጥ ቦታውን ማወቅ በራሱ የታሪኩን አግባብነት እንድናውቅ ካልሆነ በቀር በራሱ መንፈሳዊ ጉዳይ (Theologies) መሆን አይችልም። Theology ያለው ምልክቱ ላይ ነው።
ለ) ቀኑ መች ነው?
በሶስተኛው ቀን የሚለው ብዙ አስተምህሮዎች እንደሚያመለክቱት ከትርጓሜ መፅሐፍ ጨምሮ ጌታ ከተጠመቀበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን ጌታ ከተጠመቀ በኃላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በሲና በረሃ እንዳሳለፈና ከዛ ወዲህ ደግሞ ፊሊጶስ ናትናኤልን ወደ ኢየሱስ እስኪጠራበት ድረስ ሁለት በነገው የሚሉ ቀኖች እናነባለን (ዮሐ 1፥29 1፥35 ተመልከቱ)። በአጠቃላይ አርባ ሁለት ቀኖች በመኖራቸው ከተጠመቀ በኃላ ባለው በሶስተኛወ ቀን ነው ማለት እንዳንችል ይገድቡናል። ታዲያ ይህ ሶስተኛ ቀን የሚያመለክተው መች ነው የምትሉ ከሆነ ናትናኤል ከተጠራ ከቁጥር 44 ላይ ከተፃፈው በነገው በኃላ እንደሆነ ግን ጥርጥር የለውም። ጌታ ናትናኤልን ገና ከዚህ የሚበልጥ ታያለህ ካለው በኃላ ባለው በሶስተኛው ቀን ማለት ነው።
ሐ) የሰርጉ ዓይነት ምን ዐይነት ነበር?
በእስራኤል ባህል የሰርግ ስነ ስርአት ለቀናቶች የሚቆይ ሲሆን ብዙ ማህበረሰብ የሚሳተፍበት ነው። በዚህም ምክንያት የሰርጉ ድምቀት በሚሳተፉት ሰዎች ላይ የተመሰረተ ነው። የተሳካ ከሆነ የሁሉም ተሳታፊ ዘመድ አዝማዝ ክብር ሲሆን በአንፃሩም ሰርጉ ቢበላሽ ወይም ቢደበዝዝ ውርደቱ፣ ሀፍረቱና ተጠያቂነቱ በሰርጉ ለተሳተፉ ሁሉ እንጂ ለባለ ሰርጉ ብቻ አይደለም። የሰርጉን ቦታ እንዳየነው የጌታ እናት ማርያም ሳትጠራ እንደሄደች የምናውቀው ለሰርጉ ቤት የቅርብ ሰው እንደሆነች ስለሚያመለክት ነው። ደግሞ ሰርግ ስላለ ብቻ አይኬድም ጥሪ ወይም ዝምድና ያስፈልጋልና።
'' የኢየሱስ እናት በዚያ ነበረች '' ሲል ታዳሚ ከመሄዱ በፊት በዛ ስለመኖሩዋን ያሳያል። ይህ ማለት በጥሪ ሳይሆን በቅርበት ወይም በአገልግሎት እንደሆነ ለመረዳት ቀላል ነው። የወይን ጠጅ አልቆባቸዋል የሚለው ጥያቄ የሚነግረን ይህንኑ ነው። የቅርብ ተቆርቋሪ እንደነበረችና ድንግል ማርያምም በሰርጉ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት ጌታን እንደጠየቀች ጥርጥር የለውም።
"ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። "
መታደም ከላይ እንደገለፅኩት መጠራትን ያሳያል። የእንግሊዝኛውም መጽሀፍ ቅዱስ የሚነግረንም ይህን ነው (Jesus was called ይላል)። ጌታ በዚህ ጊዜ ሰላሳ ዓመት ስለሞላውና ራሱን ችሎ አገልግሎት ስለጀመረ እንዲሁም ደቀመዛሙርት ስላፈራ ከእናቱ ተለይቶ ብቻውን መጠራት ጀምሯል።
#ምልከታ:-
ብዙ አስተምህሮዎች ጌታ በሰርጉ የተገኘበት ምክንያት ነው የሚሉት
1) ማህበራዊ ጉዳይ (ዝምድና) ስለነበረው ነው የሚሉ አሉ
2) ሰርግ ሊባርክ የሚሉ አሉ
3) ክብሩን ሊገልጥ ነው።
የመጀመሪያውና ቀጥሎ ያሉው ሁለቱም ጥያቄ ያስነሳሉ ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ ጌታ የትም ቦታ ለማህበራዊ ግንኙነቶች ተልእኮ ሲያደርግ አናይም ከመለኮታዊ አጀንዳ ውጪ። ሲቀጥል ሰርግ በተፈጥሮው የተባረከ ስለሆነ የትኛውም ጋብቻ ከርኩሰትነት ወደ ቅዱስነት የሚለወጥ አይደለም (Declaration ግን ሊኖር ይችላል)። ዋናው ነገር የሰርጉ ጥሪ ምልክት በማድረግ መለኮታዊ አጀንዳውን ሊፈፅምና ክብሩን ሊገልጥ ምክንያት ሆኖል። ስለሆነም ጥሪው ጌታ የሄደበትን ጉዳይ ያገናዘበ ሳይሆን ለቤተሰቡ ቅርብ በመሆኑ ነው። ምንም እንኳ ለሰርግ ቢጠራም ጌታ የተንቀሳቀሰው የአባቱን ፍቃድ ለመፈፀም ነው።
" የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። "
እዚህ ክፍል ላይ ብዙዎችን ሲያጨቃጭቅ የኖሩ ጥያቄዎች አሉ።
1) የጌታ እናት ድንግል ማርያም የወይን ጠጅ ማለቁን እንዴን አወቀች?
2) ለምን ልጅዋን ጠየቀችው?
3) ወሃውን ወደ ወይን ይቀየራል ብላ አምና ነው ወይስ መፍትሄ ይሰጣል ብላ አስባ ነው የጠየቀችው?
እነዚህን ጥያቄዎች በታሪኩ አግባብ ከታዩ ለመመለስ ቀላል ነው። ግን በሃይማኖተኝነት ግለት (ግብዝነት) እዚህ ታሪክ ውስጥ የተደረጉትን በሙሉ መንፈሳዊ አድርጎ በማሰብ ከሆነ የተዛባና ከእግዚአብሔር ሀሳብና እቀድ ውጪ ያደርገናል።
ድንግል ማርያም የወይን ጠጁ እንዳለቀ ለማወቅ በቦታው መሆኗ በቂ ነው። እዛ በመሆንና በማየት የመጣ እውቀት ስለሆነ። መቼም እንዳሁኑ ዘመን አባባል ሳሎን ቅጭ ብላ ጓዳ ያለውን የጠጅ ጋን በመንፈስ አይታው ነው አንልም። ይገርማል የሰርጉን ቤት ጓዳ እንደሞላሽ የእኛንም ቤት ጓዳ ጎብኚ የሚሉ እጅግ ብዙ አሉና። እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ድንግል ማርያም ሁሉንም ነገር ታውቃለች ብለው ያምናሉ ይህ ደግሞ ስህተት ከመሆን ባለፈ በእግዚአብሔር ህልውና ላይ አመፃን ማድረግ ነው። ለዚህ ማመሳከሪያ ጌታ ኢየሱስ በአስራ ሁለት ዓመቱ በጠፋባቸው ጊዜ ዮሴፍና ማርያም ለሶስት ቀን በፍለጋ ባለፉ ነበር።
ልጅዋን የጠየቀችበት ምክንያት ድንግል ማርያም የእምነት ሰው ስለሆነች ነው። መፅሐፍም እንደሚል በልቧ ትጠብቀው እንደነበር ይናገራል። ይህ ደግሞ በልጇ ላይ ያላትን እምነት ያሳያል። ከጽንሰቱ ብስራት ጀምሮ የተከናወነውን ነገር ሁሉ ታውቃለች። የልጇን ማንነት በሚገባ የተነረዳች ከመሆኑም አንፃር የፈለገውን አድርጎም ቢሆን መፍትኤ ይሰጣል ብላ እርግጠኛ ስለነበረች ልጇን ጠይቃለች። '' ይኩነኒ በከመ ትበሌኒ '' ይሁን ይደረግልኝ ማለቷ ብቻ እኮ ስለ እምነቷ ማውራት ከበቂ በላይ ነው።
ጌታ ውሃውን ወደ ወይን ይቀይራል ብላ specifically እውቀት አላት ማለት አንችልም ነገር ግን ቀድሜ እንዳልኩት የልጇን ማንነት ላይ ባለ እምነት ግን ጠይቃለች። ማወቅ ያለብን ጉዳይ ማርያም ይህን ስትል ከማህበራዊ ግዴታን ወይም ከማህበራዊ ችግር ከፍታት የቀረበ ከመሆኑ ባሻገር ልንወስደው አንችልም። ምንም እንኳ እሷ ብትጠይቀውም ጌታ የእሷን ጥያቄ በእሱ መለኮታዊ እቅድ ውስጥ አስገብቶ ምልክት አድርጓል።
ይቀጥላል.............................
#ማሳሰቢያ:- የእግዚአብሔርን ክብር መግለጥ ማለት የቅዳሳንን ክብር ማቅለል አይደለም። ቀድሞውኑ የሰው ልጅ ምን ክብር አለውና የቅዱሳን ክብር እግዚአብሔር አይደለምን?
=}} (ዮሐንስ ወንጌል 2፥1-2)
" በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። "
በዚህ ምንባብ ሶስት ሀሳቦች ላይ ጥያቄ በመመለስ እናያለን።
ሀ) ድርጊቱ የተፈፀመው የት ነው?
ቃና ከናዝሬት ሰባት ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን እስራኤል የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች። ቃና ዘገሊላ የተባለችው ሌላ ቃና የሚባል ስፍራ ስላለ ለመለየት ሲባል ነው። ይህ ማለት የኮተኬ ካራና የአየር ጤና ካራ እንደማለት ነው። ገሊላ ደግሞ ጌታ ያደገበት ስፍራ ወይም አቅራቢያ መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም። ከዚህም በመነሳት ለሰርግ ጥሪው የቅርብ ሰው እንደሆነ መረዳት እንችላለን። እናቱ ድንግል ማርያም በዛ አካባቢ የምትታወቅና ለሰርጉ ቤተ ሰዎች የቅርብ ሰው እንደሆነች ታሪኩ ያሳያል። ይህን ማወቅ ታሪኩን በትክክል እንድንረዳ ይጠቅመናል። በእርግጥ ቦታውን ማወቅ በራሱ የታሪኩን አግባብነት እንድናውቅ ካልሆነ በቀር በራሱ መንፈሳዊ ጉዳይ (Theologies) መሆን አይችልም። Theology ያለው ምልክቱ ላይ ነው።
ለ) ቀኑ መች ነው?
በሶስተኛው ቀን የሚለው ብዙ አስተምህሮዎች እንደሚያመለክቱት ከትርጓሜ መፅሐፍ ጨምሮ ጌታ ከተጠመቀበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን ጌታ ከተጠመቀ በኃላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በሲና በረሃ እንዳሳለፈና ከዛ ወዲህ ደግሞ ፊሊጶስ ናትናኤልን ወደ ኢየሱስ እስኪጠራበት ድረስ ሁለት በነገው የሚሉ ቀኖች እናነባለን (ዮሐ 1፥29 1፥35 ተመልከቱ)። በአጠቃላይ አርባ ሁለት ቀኖች በመኖራቸው ከተጠመቀ በኃላ ባለው በሶስተኛወ ቀን ነው ማለት እንዳንችል ይገድቡናል። ታዲያ ይህ ሶስተኛ ቀን የሚያመለክተው መች ነው የምትሉ ከሆነ ናትናኤል ከተጠራ ከቁጥር 44 ላይ ከተፃፈው በነገው በኃላ እንደሆነ ግን ጥርጥር የለውም። ጌታ ናትናኤልን ገና ከዚህ የሚበልጥ ታያለህ ካለው በኃላ ባለው በሶስተኛው ቀን ማለት ነው።
ሐ) የሰርጉ ዓይነት ምን ዐይነት ነበር?
በእስራኤል ባህል የሰርግ ስነ ስርአት ለቀናቶች የሚቆይ ሲሆን ብዙ ማህበረሰብ የሚሳተፍበት ነው። በዚህም ምክንያት የሰርጉ ድምቀት በሚሳተፉት ሰዎች ላይ የተመሰረተ ነው። የተሳካ ከሆነ የሁሉም ተሳታፊ ዘመድ አዝማዝ ክብር ሲሆን በአንፃሩም ሰርጉ ቢበላሽ ወይም ቢደበዝዝ ውርደቱ፣ ሀፍረቱና ተጠያቂነቱ በሰርጉ ለተሳተፉ ሁሉ እንጂ ለባለ ሰርጉ ብቻ አይደለም። የሰርጉን ቦታ እንዳየነው የጌታ እናት ማርያም ሳትጠራ እንደሄደች የምናውቀው ለሰርጉ ቤት የቅርብ ሰው እንደሆነች ስለሚያመለክት ነው። ደግሞ ሰርግ ስላለ ብቻ አይኬድም ጥሪ ወይም ዝምድና ያስፈልጋልና።
'' የኢየሱስ እናት በዚያ ነበረች '' ሲል ታዳሚ ከመሄዱ በፊት በዛ ስለመኖሩዋን ያሳያል። ይህ ማለት በጥሪ ሳይሆን በቅርበት ወይም በአገልግሎት እንደሆነ ለመረዳት ቀላል ነው። የወይን ጠጅ አልቆባቸዋል የሚለው ጥያቄ የሚነግረን ይህንኑ ነው። የቅርብ ተቆርቋሪ እንደነበረችና ድንግል ማርያምም በሰርጉ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት ጌታን እንደጠየቀች ጥርጥር የለውም።
"ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። "
መታደም ከላይ እንደገለፅኩት መጠራትን ያሳያል። የእንግሊዝኛውም መጽሀፍ ቅዱስ የሚነግረንም ይህን ነው (Jesus was called ይላል)። ጌታ በዚህ ጊዜ ሰላሳ ዓመት ስለሞላውና ራሱን ችሎ አገልግሎት ስለጀመረ እንዲሁም ደቀመዛሙርት ስላፈራ ከእናቱ ተለይቶ ብቻውን መጠራት ጀምሯል።
#ምልከታ:-
ብዙ አስተምህሮዎች ጌታ በሰርጉ የተገኘበት ምክንያት ነው የሚሉት
1) ማህበራዊ ጉዳይ (ዝምድና) ስለነበረው ነው የሚሉ አሉ
2) ሰርግ ሊባርክ የሚሉ አሉ
3) ክብሩን ሊገልጥ ነው።
የመጀመሪያውና ቀጥሎ ያሉው ሁለቱም ጥያቄ ያስነሳሉ ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ ጌታ የትም ቦታ ለማህበራዊ ግንኙነቶች ተልእኮ ሲያደርግ አናይም ከመለኮታዊ አጀንዳ ውጪ። ሲቀጥል ሰርግ በተፈጥሮው የተባረከ ስለሆነ የትኛውም ጋብቻ ከርኩሰትነት ወደ ቅዱስነት የሚለወጥ አይደለም (Declaration ግን ሊኖር ይችላል)። ዋናው ነገር የሰርጉ ጥሪ ምልክት በማድረግ መለኮታዊ አጀንዳውን ሊፈፅምና ክብሩን ሊገልጥ ምክንያት ሆኖል። ስለሆነም ጥሪው ጌታ የሄደበትን ጉዳይ ያገናዘበ ሳይሆን ለቤተሰቡ ቅርብ በመሆኑ ነው። ምንም እንኳ ለሰርግ ቢጠራም ጌታ የተንቀሳቀሰው የአባቱን ፍቃድ ለመፈፀም ነው።
=}} (የዮሐንስ ወንጌል 2፥3)
" የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። "
እዚህ ክፍል ላይ ብዙዎችን ሲያጨቃጭቅ የኖሩ ጥያቄዎች አሉ።
1) የጌታ እናት ድንግል ማርያም የወይን ጠጅ ማለቁን እንዴን አወቀች?
2) ለምን ልጅዋን ጠየቀችው?
3) ወሃውን ወደ ወይን ይቀየራል ብላ አምና ነው ወይስ መፍትሄ ይሰጣል ብላ አስባ ነው የጠየቀችው?
እነዚህን ጥያቄዎች በታሪኩ አግባብ ከታዩ ለመመለስ ቀላል ነው። ግን በሃይማኖተኝነት ግለት (ግብዝነት) እዚህ ታሪክ ውስጥ የተደረጉትን በሙሉ መንፈሳዊ አድርጎ በማሰብ ከሆነ የተዛባና ከእግዚአብሔር ሀሳብና እቀድ ውጪ ያደርገናል።
ድንግል ማርያም የወይን ጠጁ እንዳለቀ ለማወቅ በቦታው መሆኗ በቂ ነው። እዛ በመሆንና በማየት የመጣ እውቀት ስለሆነ። መቼም እንዳሁኑ ዘመን አባባል ሳሎን ቅጭ ብላ ጓዳ ያለውን የጠጅ ጋን በመንፈስ አይታው ነው አንልም። ይገርማል የሰርጉን ቤት ጓዳ እንደሞላሽ የእኛንም ቤት ጓዳ ጎብኚ የሚሉ እጅግ ብዙ አሉና። እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ድንግል ማርያም ሁሉንም ነገር ታውቃለች ብለው ያምናሉ ይህ ደግሞ ስህተት ከመሆን ባለፈ በእግዚአብሔር ህልውና ላይ አመፃን ማድረግ ነው። ለዚህ ማመሳከሪያ ጌታ ኢየሱስ በአስራ ሁለት ዓመቱ በጠፋባቸው ጊዜ ዮሴፍና ማርያም ለሶስት ቀን በፍለጋ ባለፉ ነበር።
ልጅዋን የጠየቀችበት ምክንያት ድንግል ማርያም የእምነት ሰው ስለሆነች ነው። መፅሐፍም እንደሚል በልቧ ትጠብቀው እንደነበር ይናገራል። ይህ ደግሞ በልጇ ላይ ያላትን እምነት ያሳያል። ከጽንሰቱ ብስራት ጀምሮ የተከናወነውን ነገር ሁሉ ታውቃለች። የልጇን ማንነት በሚገባ የተነረዳች ከመሆኑም አንፃር የፈለገውን አድርጎም ቢሆን መፍትኤ ይሰጣል ብላ እርግጠኛ ስለነበረች ልጇን ጠይቃለች። '' ይኩነኒ በከመ ትበሌኒ '' ይሁን ይደረግልኝ ማለቷ ብቻ እኮ ስለ እምነቷ ማውራት ከበቂ በላይ ነው።
ጌታ ውሃውን ወደ ወይን ይቀይራል ብላ specifically እውቀት አላት ማለት አንችልም ነገር ግን ቀድሜ እንዳልኩት የልጇን ማንነት ላይ ባለ እምነት ግን ጠይቃለች። ማወቅ ያለብን ጉዳይ ማርያም ይህን ስትል ከማህበራዊ ግዴታን ወይም ከማህበራዊ ችግር ከፍታት የቀረበ ከመሆኑ ባሻገር ልንወስደው አንችልም። ምንም እንኳ እሷ ብትጠይቀውም ጌታ የእሷን ጥያቄ በእሱ መለኮታዊ እቅድ ውስጥ አስገብቶ ምልክት አድርጓል።
ይቀጥላል.............................
Tuesday, 18 December 2018
የጌታ ክብር መገለጥ (ክፍል አንድ)
በዮሐንስ ወንጌል ተከታታይ ጥናት እየተማርኩት ካለው ውስጥ በምዕራፍ ሁለት መጀመሪያ ላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በተለምዶ ወይም በአብዛኛ አጠራር በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት የተደረገውን የጌታ ክብር መገለጥ ላካፍላችሁ በመሻቴ የእግዚአብሔር መንፈስ በረዳኝ መጠን እንዲህ አቀርበዋለው። ወደ ዋናው ሀሳቤ ከመግባቴ በፊት ታሪኩን እንድታነቡ እጋብዛችኅለው።
'' በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ። ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። '' (ዮሐ 2፥1-11)
ይህ ክፍል ብዙ የተባለበት ብዙ መፅሐፍ የተፃፈበት ብዙ ስብከት የተሰበከበት ክፍል ነው። ነገር ግን አብዛኛውን ሰምተን ያደግነው መፅሐፉ ሊናገረን ባሰበው መንገድ አይደለም የሰማነውም፣ ያነበብነውም፣ ያጠናነውም። ለዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል የተለያዩ ርዕሶች ተሰጥተውታል። ለአብነት ያህልም በዋናነት የሚታወቁት የመጀመሪያው ተአምር፣ ቃና ዘገሊላ፣ በእርሱ አመኑ፣ የሚላችሁን አድርጉ፣ የድንግል ማርያም ምልጃ ልንል እንችላለን። በዚህ ታሪክ ውስጥ ብዙ ክንውን ተደርጓል ነገር ግን ታሪኩን የሚያገናኝ ሀሳቡን የሚሰበሰብና የሚጠቀልል ወይም ሁሉንም ድርጊትና ንግግሮችን የሚገዛ አንድ ወሳኝ ግንድ አለ። እርሱም የጌታ ክብር መገለጥ።
ቀድሞ የሆነውን ሰርጉን በምክንያትነት የደቀ መዛሙርቱ ማመን በውጤትነት የጌታ ኢየሱስ ክብር መገለጥ ማዕከልነት በማድረግ የተከናወነ ታሪክ ነው። በዚህ ታሪክ ብቻም አይደለም በአዲስ ኪዳን በዋናነት የጌታን ክብር መገለጥን ነው የሚነግረን ስለሆነም ለፅሁፋችን '' የጌታ ክብር መገለጥ '' የሚል ርዕስ ስጥተነዋል። በዚህ ታሪክ ውስጥ ማንም ይናገር፣ ምንም ይደረግ፣ ማንም ይሳተፍ በዛ የተደረገው ሁሉ የጌታ ክብር ለመግለጥ ነው።
ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት አብዛኛው በዚህ ታሪክ ዙሪያ የተደረጉ አስተምህሮዎች በተሳሳተና የጌታን ክብር መገለጥ በሚሸፍን መልኩ ነው የተላለፉት። ለዚህም አብዛኛው አስተምህሮዎች ርዕሶች ምስክር ናቸው። የአንድ ትምህርት ርዕስ የትምህርቱ ዋና ሀሳብን የሚይዝ ሲሆን በዙሪያው ያለውን ሁኔታ በሙሉ ለርዕሱ ተገዢ ያደርገዋል። በዚህ መልኩ የሚያስተምሩ አስተማሪዎችና መምህራን ይህን ያደረጉት አውቀውም ይሁን ሳያውቁ
ሀ) የጌታ ክብር ለማደብዘዝ
ይህንንም ለማሳካት ሶስት መንገዶችን ወይም ዘዴዎችን ተጠቅመዋል።
1) ርዕስ ሲመርጡ ከገቢር ግስ ይልቅ ተገብሮ ግስ ይጠቀማሉ (they prefer passive rather than active) ድርጊቱን የሚገልፀውን ወይም ድርጊቱን የፈፀመውን አካል በመተው የድርጊቱን ባለቤት ማደብዘዝ/መሸፈን (ከድርጊቱ ማስወጣት ነው) እና ሌላ ነገር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።
ምሳሌ ሀ:-
'' The man kill the Dog.'' ከሚለው ይልቅ '' A Dog is killed.'' በመጀመሪያው ላይ ሰውዬው ውሻውን እንደገደለ ግልፅ ነው። የሰውዬውን ማንነት በድርጊት ተገልጿል። በመሆኑም አድራጊው የታወቀ ነው። በሁለተኛው ውሻው ተገሎ መሞቱን እንጂ ማን እንደገደለው አይገልፅም በዚህ ርዕስ ውስጥ ተናጋሪው አድራጊውን አስወጥቶቷል። ይህ ደግሞ መረጃነቱን ባሳጣት ክፍተት ፈጥሯል። ፍንጭ እንጂ ማስረጃው ደብዝዟል።
ምሳሌ ለ:- '' ኢየሱስ ውሃውን ወይን ጠጅ አደረገው '' ከሚለው ግስ ይልቅ '' ውሃው ወደ ወይን ጠጅ ተለወጠ '' ይሉታል። '' አደረገ '' የሚለው ገቢር ግስ ሲሆን '' ተለወጠን '' በማምጣት ተገብሮ ግስን በመውሰድ ድርጊቱን የፈፀመውን አካል ቸል ይሉታል። ርዕሱ እውነት ይመስላል ግን ኢየሱስን አውጥቶታል።
2) ርዕስ ሲመርጡ ለአድራጊው ማንነት ላይ ትኩረት አለመስጠት። በቃና ዘገሊላ ጌታ ኢየሱስ ካደረገውና ከተገለጠው ክብር ይልቅ ሰርጉ ላይ ማተኮር፣ በሰርጉ የታደሙ ሰዎች ላይ ማነጣጠር፣ የተደረገው ተአምራት ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ፣ የወይኑ መጣፈጥ ላይና ድንግል ማርያም የተናገረችውን ለጥጦ ማየት።
ምሳሌ ሐ:-
የኢየሱስ የመጀመሪያው ምልክት ከሚለው ይልቅ የመጀመሪያወ ምልክት ብቻ በማለት ኢየሱስን ማስወጣት። አዲሱ መደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚለው '' ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ አደረገ '' ይላል። ይህ ሙሉ ነው በዛ ላይ Active ነው። ሙሉ መረጃ መስጠት ይችላል ነገር ግን ኢየሱስን በማውጣት የተፈጠረውን ምልክት ላይ ብቻ ማተኮር። የዚህም ዓላማ ኢየሱስን ማደብዘዝ ነው።
3) ታሪኩን በመቆራረጥ የተለያየ ርዕሶችን መስጠት። 11 ቁጥሮች ያሉት ይህ ታሪክ ብዙ የተቆራረጡ ርዕሶችን በመስጠት ዋና ሀሳብ እንዳይነሳ ማድረግ።
ምሳሌ መ:- የ2000 ዓ.ም የታተመው ሰማንያ አሐዱ መፅሐፍ ቅዱስ ይህን ታሪክ በሶስት ከፋፍሎ ርዕስ ስጥቶታል ግን ሶስቱም ስር ኢየሱስ የለም።
=}} ከቁጥር 1-2 በቃና ዘገሊላ ስለተደረገው ሰርግ ይላል
=}} ከቁጥር 3-5 ስለ እናቱ ምልጃ ይላል
=}} ከቁጥር 6-11 ስለ መጀመሪያ ተአምር ይላል።
መፅሐፍ ቅዱስ ሊነግረን ያለውን በመተው ሃይማኖታዊ ፓለቲካ ፍጆታ ሰበብ (For Denomination Purpose) የገቡ ርዕሶች እንዳሉ ማየት ቀላል ነው። እንዲገባ የተፈለገ ሀሳብ በግድ ተጠምዝዞ ገብቷል። ከእውነት ይልቅ ለብዙ ዘመናት የነበረውን በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውን አስተምህሮ የማስቀጠል አጀንዳ መያዙን መረዳት እንችላለን።
ይቀጥላል................................
Tuesday, 11 December 2018
የያዕቆብ መሰላል
'' ስብሀት ለእግዚአብሔር ወሰማያት ወሰላም ወምድር ስምረቱ ለሰው። ''
ይህን መዝሙር ብዙ ጊዜ ዘምረነው እናውቃለን ነገር ግን የተዘመረበትን ዓላማው አስተውለነዋል ብዬ አላምንም። ይህ ምስጋና መላእክት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በመወለዱ የተነሳ ያቀረቡት ሰማይና ምድር የተገናኙበት ምስጋና ነው። በጌታ የማዳን ስራ በመደነቅ በጠባብ ደረት ተወስኖ ሰው ሆኖ ሲያዩት እልፍ ሰራዊት ወደ ምድር መጡና የሰማይና ምድር መጋጠምን አበሰሩ። በእርሱ መሰላልነት ይወጡና ይገቡ ጀመር።
ይህ አስቀድሞ ያዕቆብ መላእክት ሲመላለሱበት ያየው መሰላል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
'' ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር። '' (ዘፍ 28፥10-13)
አዎ በምድር የተተከለ ወደ ሰማይ የደረሰ እንደ ኢየሱስ ያለ ማንም የለም። ኢየሱስ በመዋህለ ሥጋዌ ምድርን ከመርገጡ በፊት ገና ሳይፀነስ ለእናቱ ምሥራች ከተነገረበት ጊዜና ለዓለም በከፈለው ዋጋ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶ የሞትን ጣር በማጥፋት ድል አድርጎ ከተነሳ እንዲሁም ስፍራ ሊያዘግጅልን ወደ ግርማው ቀኝ በሄደበት እስከ ዕለተ እርገቱ ድረስ የመላእከት ወደ ምድር መውጣትና መግባት ይህን ያረጋግጣል። ማራናታችን ዳግም ሊወስደን ሲመጣም በአእላፍ መላእክት አጀብ እንደሆነም ሌላኛው ማረጋገጫ ነው።
ገና በግርግም ሳለ:-
"ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ። ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ። " (ሉቃ 2፥13-14)የጌታ መወለድ ሰማይና ምድር የተገናኙበት ነው። ሁለቱንም የሚወክል በምድር ለምንኖር ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን መሰለ። ሰማይ ዙፋኑ የሆነው እርሱ በእግዚአብሔር መልክ የሚኖር ለዘመኑ መጀመሪያና ፍፃሜ የሌለው አልፋ ኦሜጋ ፊተኛውና ኋለኛው ሁሉን የፈጠረ የተባረከ አምላክ ነው። ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ።
ምድራዊያን ምድርን ብቻ ነው የነኩት ሊወክሉ የሚችሉት ሰማይ የለም። እግዚአብሔርም ሉአላዊ አምላክ ነውና ክብሩን ለሌላ በፍፁም አሳልፎ የሚሰጥ አይደለም። ሰማይን የሚወክል ከልጁ በቀር ሌላ አላዘጋጀልንም። መሰላል የተባለ ሁሉ ሰማይ አያደርስም። ኢየሱስ እውነተኛ መንገድ ነው። ለሰው ልጅ ሁሉ መሰማሪያ ቅጥር መሄጃ መንገዱ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው።
" ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። " (ዮሐ 14፥6)
በትንሳኤ ጊዜ:-
መላእክት መወለዱን እንዳበሰሩት ሁሉ ትንሳኤውንም የተናገሩት እነርሱ ናቸው። ይህ መላእክት በጌታ ኢየሱስ ላይ ያላቸውን መመላለስ ያስረዳል። (ማቴ 28፥2-6)
በዕርገት ጊዜ:-
ጌታ የመጣበትን ዓላማ የሰውን ልጅ ከኃጡአት ባርነት ነፃ በማውጣት ወደ አባቱ ሲያርግ መላእክት ነበሩ። (ሐዋ 1፥10-11)
ያዕቆብ ያየው መሰላል የተባለው ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሆኑ እነዚህ ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ቢሆንም ጉዳዩን ግልፅ የሚያደርግልን ቃል አለ። እርሱም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ አንደበት የተናገረው ነው። ናትናኤልን አውቅሃለው በማለቱ ባሳየው እምነት የተነሳ ገና ብዙ ነገር ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ እንዳለው። ናትናኤል ሊያየው ከሚገባ የሚበልጥ ነገር አንዱ የኢየሱስን አማናዊ መሰላልነት ነው። ለዚህ ነው ጌታ
" እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው። "(ዮሐ 1፥52)
'' የሰው ልጅ '' ደግሞ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን ኢየሱስን ለማመልከት እንደሆነ በወንጌላቱ በተደጋጋሚ ተነግረዋል። (እነዚህን ጥቅሶች ተመልከቱ ማቴ 16፥13 ሉቃ 2፥48 )
Friday, 7 December 2018
ዋላ
እንዴት ''ዋላ''ችሁ
የጌታ ኢየሱስ ሰላምና ፍቅር በያለንበት ይብዛልን!!!
ተጠማች ነፍሴ ናፍቃህ እንደ ዋላ
የለኝም ዋስትና መድን ካንተ ሌላ
የሕይወት ውሃዬ ፍሰስ በልቤ ላይ
ኢየሱስ ድምፅህን አሰማኝ ከሰማይ
ዋላ በአማርኛ ዲክሽነሪ ላይ እንደተገለፀው ከዱር አራዊት የምትመደብ፣ በበረሀ የምትኖር የፍየል ወገን ነች። መፅሐፍ ቅዳስ ዋላን በእንዲህ መልኩ ያነሳታል በመዝሙር 41፥1-2
'' ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? ''
ዋላ እንደልቧ ሲጠማት በቀላሉ ውሃ ልታገኝ የማትችል የሁልጊዜ ተጠሚ ስትሆን ጥሟን ለማስታገስ ሌት ከቀን ወደ ምንጭ ትዳክራለች። ዋላ ውሃ የምታገኘው ከአዳኟ ተደብቃና ካያትም ሸሽታ ብዙ ዋጋ ከፍላ ነው። አብዛኛውን ኑሮዋንም የምታደርገው በምንጩ ዙሪያ ነው።
ዋላ ለስጋ ጥም እርካታ ውሃ ያስፈልጋታል እኛ ግን ጠጥተን ወደማንጠማበት የእርካታ ጥግ እንዳንደርስ በብዙ መሰናክሎች ተወጥረን እንገኛለን። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማሪያዋ ሴት እንደነገራት
"፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። "
(የዮሐንስ ወንጌል 4: 14)። ወደዚህ ዘላለማዊ እርካታ እንዳንቀርብ ጠላት ዲያብሎስ ብዙ ይታገላል። ዋላ በራሷ ጥረት ከአዳኟ ታመልጣለች እኛ ግን አሳላፊው ጌታ ያለአንዳች ያሳልፈናል። አንዳንዴ የእርሱ ጥበቃ በዝቶም እኛ ግን ራሳችን በራሳችን ላይ እንቅፋት እስከመሆን እንደርሳለን።
እኛም ከዋላ ብዙ የምንማር ይመስለኛል። እንደዋላ መውጣት መውረድ ሳይኖርብን ጌታ በሰራው ስራ ዘላለማዊ ጥጋብ ዘንቦልናል። እርሱ በመስቀል ላይ ተጠማው ብሎ መራራውን ሆምጣጤ ጠጥቶ ለእኛ ግን አንዴ ጣፍጦን ጠጥተነው ዘላለም እረክተን እንድንኖር የሚያስችለንን ፀጋ ሰጥቶናል ስሙ ይቀደስ። ታዲያ በዚህ እርካታ ውስጥ ሆነን የጌታን ድምፅ እንድንሰማ የማይወደውና የማይፈልገው ጠላት እንደሚያገሳ አንበሳ ዙሪያችን ይዞራል። ዋላም በቀላሉ ጠላት ሊይዛት የሚችለው ጥሟን ከምታገኝበት ከምንጩ ስፍራ ሲሆን እኛንም ከዘላለማዊ ምንጭ እንዳንገናኝ ከእርካታችን ትይዩ ሆኖ ይጠብቀናል። ከምናውቀውም ከማናውቀውም ጠላት የሚጠብቅ የማይተኛ፣ የማያንቀላፋው አምላካችን ክብርና ምስጋና አምልኮትና ውዳሴ ለእርሱ ይሁንለት።
እግዚአብሔርን በተጠማነው መጠን እንረካለን። ትናንት ከነበረን እግዚአብሔርን መጠማት ዛሬ ላይ በይበልጥ ሊኖረን ይገባል። ነገ ደግሞ ከዛሬ። እግዚአብሔርን የምናወቀው ልናውቀው በፈለግነው መጠን ነው። ባለን አቅም ቃሉን እየታጠቅን፣ ለቃሉም እየታዘዝን፣ በፀሎትም እየተጋን እንድንኖር የእግዚአብሔር ጸጋ ይርዳን። በሚያስፈልጋችሁም ጊዜ የሚረዳ የእግዚአብሔር ጸጋ አለ ተብሎም እንደተፃፈ በነገሮች ሁሉ ማድረግንም መፈለግንም በእኛ ላይ የሚሰራ አምላክ ያስችለን።
ኢየሱስ
ኢየሱስ የሚለው ስም ትርጉም ሕዝቡን ሁሉ ከኋጢአታቸው የሚያድን አዳኝ ማለት ነው። ስሙ ከማዳን ጋር የተገናኘ ሲሆን አባታችን እግዚአብሔር እንደባለጠግነቱ መጠን ለእኛ በበደላችንና በኋጢአታችን ሙትን ለነበርነው እንድንበት ዘንድ የሰጠን በዚህም ዓለም ደግሞ ለሚመጣውም ዓለም ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ነው።
ስሙ ማትረፊያ ነው። ከዚህ ስም ብቻ የተነሳ መፅሐፍ ቅዱሳችን አንዲህ በማለት ትርፋችንን ይነግረናል።
1) ከዘላለም ፍርድ ያድናል።
"፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል። " (የሐዋርያት ሥራ 10: 43)
2) ከሃጢያት ያድናል።
"፤ ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። " (የማቴዎስ ወንጌል 1: 21)
"፤ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና። " (የሐዋርያት ሥራ 4: 12)
3) የልጀነት ስልጣን ይሰጣል።
"፤ ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ "
(የዮሐንስ ወንጌል 1: 12)
4) ወደ እግዚአብሄር አብ ያቀርባል።
"፤ እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ። " (የዮሐንስ ወንጌል 15: 16)
5) ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ የሆነ ስም ነው፡፡
"፤ በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ "
(ወደ ሮሜ ሰዎች 10: 12)
6) የምንበረከክለት ብቸኛ ስም።
"፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ " (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 10) ስለሆነም ለሌላ ስም ከቶ እንዳንበረከክ ይህ ያስረዳል።
7) ድርጊት መፈፀሚያ።
"፤ እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት። " (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3: 17)
እነዚህ ጥቂቶች ናቸው። ይህ ስም ለእኛ ለክርስቲያኖች የምንመካበት አዝለን ይዘነው የምንሄደው ከብዙ ነገር የምንወጣበት ማምለጫችን ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ማለት በአሁን ሰአት ብዙ ነቃፋን የሚያስገኝ እየሆነ መሄዱ የተለመ ሆኗል።
ብፁህ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የተባሉ አባት ተናገሩት የተባለው ትዝ አለኝ። አንድ ሰካኪ በስብከቱ ውስጥ ኢየሱስ እያለ በተደጋጋሚ በመጥራቱ ወደ እኝህ አባት ቅሬታ ይቀርብበታል። አቡኑም ቅሬታው ምንድነው ብለው ይጠይቃሉ። ቅሪ የተሰኘውም ሰው ይህ ሰው ጌታችን በቁንፅላ ብቻ ኢየሱስ እያል በአንድ ስበከት ውስጥ በተደጋጋሚ ጠራው እንዴት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይልም ድስት እንኳ ሁለት ጆሮ አለው አይደለም እንዴ አባታችን ይላል። እሳቸውም አንተ ሞኝ ድስት ራሱን አይችልም ኢየሱስ የሚለው ስም ግን ብቻውን ኋያል ነው። ያ '' ኢየሱስ '' ነው ጌታችንና መድሃኒታችን አሉትና መለሱት።
ኢየሱስ ከሚለው ስም ጋር በተያያዘ ሁላችንም በየራሳችን የማንረሳው ክስተት ይኖራል ብዬ አስባለው። እኔ ስሙ ከሆነልኝና በሰሙ ካገኘውት መዳንና በረከት ሌላ የማልረሳው አንድ ትወስታ አለኝ።
የዛሬ ዘጠኝ ወይም አስር ዓመት ገደማ ከስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ወጥቼ በዋናው በር ላይ የሜክሲኮ ታክሲ ይዤ መሄዴ ትዝ ይለኛል። አሁን የማላስታውሰው ነገር ግን በወቅቱ ለእኔ ወሳኝ ሆኖብኝ የነበረ ጉዳይ ነበረ። አካሌ ታክሲ ሲሳፈር አእምሮዬ በሀስብ ባህር ተሳፍሮ ጭልጥ አርጎኛል።
ታዲያ በዚህ ሀሳቤን በሙሉ በወሰደው ነገር እልም ካልኩበት ሰመመን ያነቃኝ ገጠመኝ ለእኔ አዲስ ክስተት ነበረ። እንዴትና በምን ሁኔታ ከተሳፈረኩበት ከስድስት ኪሎ አራት ኪሎ ታክሲው እንደደረሰ እንኳን አላወኩም፣ ነገር አንዳች ከተመሰጥኩበት ሀሳብ የሚያነቃ ድምፅ በድንገት በኋይል በጆሮዬ ገባ።
አንድ ረዥም ቀጠን ያለ የቀይ ዳማ ጎልማሳ ከእሱ የወጣ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ተጠምጄ ከነበረው ወሳኝ ሀሳቤ ሁለንተናዊ መነቃቃት በሚፈጥር ሁኔታ ከተሳፈርኩበት የሀሳብ ባህር በድንገት መለሰኝ።
ሰውዬው '' ኢየሱስ ጌታ ነው '' እያለ በተደጋጋሚ ሳያቋርጥ ይናገራል። ሳልፈልግ ከሀሳቤ በመመለሴ ብቻ ሳይሆን የሰውዬው ድምፅ ጉልበት ለጆሮዬ ድንገት የመጣ አደጋ እስኪመስለኝ ድረሰ አስደንግጦኝ ስለነበረ እጅግ ተናድጄ ስለነበረ አፀፋዬን መለስኩለት እንዲህ በማለት
'' ኢየሱስ የጌቶች ጌታ የንጉሶች ንጉስ የአማልክት አምላክ ነው'' ። እናም በወቅቱ አፀፋዬን በመመለሴ ውስጤን አረጋጋው። ልክም እንደሆንኩኝ ይሰማኝ ነበረ። እውነት ነው ኢየሱስ የጌቶች ጌታ የንጉሶች ንጉስ የአማልክት አምላክ ነው ነገር ግን መፅሐፍም እንደሚል ኢየሱስ ጌታ ነው።
"፤ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። "
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 11)
ስለዚህም የእኔ መልስ መሆን ይገባው የነበረ አሜን እንጂ አፀፋ አልነበረም። በወቅቱ በነበረው መናደድ '' ኢየሱስ ጌታ ነው '' የሚለውን በመቃወም የጌቶች ጌታ ማለቴ ልክ አልነበረም። እርሱ ጌታ የሆነው ነው የጌቶች ጌታ። አዎ ምላስም ሁሉ እንደሚል ቃሉ ምላሴ ለዚህ እውነት ህብረት ሊያደርግ ሲገባ የተነገረውን ቃል በመተው ሰውዬውን በመመልከቴ አፀፋ ሰነዘርኩ። ሰውን መመልከት መጨረሻው ጥፋት ነው። የሌላን መቃወም የእኔን ልክ አያረገውም። የሌላን መኮነን የእኔን እውነት አያረጋግጥም። የእሱን በማፍረስ የእኔን አይገነባም።
ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ ነህ። ስምህን ሰምቶ ሞት ይደንግጥ ቀላያትም ይሰንጠቁ አለማመን ይራቅ ተብሎ እንደተፃፈ የስምህ ኋይል ስለገባኝ አመሰግናለው። እርቃንህን ስለእኔ በመስቀል የተቸነከርክ ስምህን በዘመኔ ሁሉ አውጃለው። ኢየሱስ ስምህን ለአዋጅ እንጂ ለሹክሹክታ እንኳ አይመችም።
በጌታ ደስ ይበላችሁ
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ!!!
ፊሊጵ 4፥4
ደስታ ለሁሉም የሰው ልጅ የተሰጠ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሰዎች የደስታቸው ምንጭ ዘመናዊ መኪና፣ አካውንታቸው ውስጥ የተቀመጠ ዳጎስ ያለ ጥሬ ገንዘብ፣ ጥሩ ሥራ፣ ዝና፣ ትልቅ ቤት በዘመናዊ ፈርኒቸሮችና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የተሞላ እንዲሁም ማራኪ ተክለ ሰውነት ለደስታ ቁልፎች እንደሆኑ የሚሰማቸው ብዙዎች ናቸው። ይህ ሁሉ ግን ጊዜያዊ ከመሆናቸውም ባሻገር እውነተኛ ደሰታ መስጠት አይችሉም።
ደስታ ከላይ ከአባታችን ከእግዚአብሔር የሚስጥ በፍፁም ሀሴት የምናገኝበት በምናገኘውና በምናጣው ነገር ላይ ያለተመረኮዘ ነገር ግን ራሱን የቻለ ልዩ መለኮታዊ ሙላት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ሁሌ በጌታ ደስ እንድንሰኝ ያዛል። በትክክል እንደ እግዚአብሔር ቃል ለሚመላለስ ሰው ለዚህ ደስታ ተገዢ ነው። ደስተኞች እንዳንሆን የሚያደርጉንና የሚያስጨንቀንን አንዳች ባለማስቀረት ጌታ ለእያንዳንዳችን ፈንታ ሆኖ ወስዶልናል።
በዚህ እንደ እንግዳና መፃተኛ ሆነን በምንኖርበት ምድር በየትኛውም፣ በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ እንኳ ብንሆን ፈልገን ብናጣ፣ ሽተን ቢቀር፣ ሞክረን ባይሳካ፣ ጠይቀን ብንከለከል፣ ፈልገን ባናገኝ፣ ጠብቀን ባይመጣ፣ በጌታ ያለንን ደስታ የሚያሳጠና ከሆነ That is the question?
የደስታችን ምንጭ ሊሆን የሚገባው ቃሉ እንደሚለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ለዚህም ደሰታችን የተጠበቀ እንዲሆን በሚያሰፈልገን ጊዜ የሚረዳን የእግዚአብሔር ፀጋ አለና። ሐዋርያው ቅዳስ ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በፃፈው መልእክቱ በምዕራፍ 4፥13 ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ይላል። ለሚያስፈልገን ማንኛውም ውጫዊ ነገር (ለምንም ነገር) ውስጣዊ ዝግጁነት ሊኖረን እንደሚገባ ያስገነዝበናል። ኋይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ለምንም ነገር ዝግጁ ነኝ ማለት ይገባናል።
እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ የእርሱ ልጆች ከሆንን ደግሞ የምንመራው በእርሱ መንፈስ ነውና እውነተኛውን
የደስታ እርካታ ወደምናገኝበት መቅረብ አለብን። የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። (1ኛ ዮሐ 3፥1) እግዚአብሔር ለእኛ ፍቅሩን የገለጸው አንድያ ልጁን በመስጠት ነው። ከዚህ በላይ ደግሞ ምንም ስጦታ የለምና ደስታችንን በጌታ ሙሉ እናድርገው። ካነበብኩት አንድ ታሪክ ልንገራችሁ
በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ በአንድ አገር አየር ኋይል ውስጥ የሚሰራ አውሮፕላን አብራሪ ነበረ። ይህ ሰው ብቸኛ አንድ ወንድ ልጁንና ባለቤቱን በሞት የተለዩት ሲሆን በወቅቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት ያበራት የነበረችው አውሮፕላን ተመታ ትወድቃለች እሱም ይሞታል። ታዲያ ሰውዬው በሕይወት እያለ በዓለም በሚታወቁ ሠዓሊያንና ቀራጺያን የተሰሩ እጅግ ውድ ሥዕሎችና በከበሩ ማህድናት የተሰሩ ጌጦችን ይሰበስብ የነበረ ሲሆን ምንም ወራሽ ባለመኖሩ ስሞት እነዚህ ንብረቶቼ በጨረታ ተሽጠው ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይሰጡልኝ ብሎ ስለነበር በጠበቃው አማካኝነት ንብረቶቹ ለጨረታ ይቀርባሉ።
ጨረታውን ለመሳተፍ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍል የተሰበሰቡ ቱጃሮችና ጨረታውን ለመዘገብ የታደሙ ጋዘጠኞች ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ ተሰግስገዋል። የሰውዬው ጠበቃ መድረኩን በመቀበል የሰውዬውን የመጀመሪያ ኑዛዜ አነበበና ከመንግስት ለተመደቡት አጫራች ስፍራውን ለቀቀ። በኑዛዜው መሰረት በቅድሚያ መሸጥ ያለበት የተናዛዡ ብቸኛ ልጅ መልክ የሚያሳይ በእጅ የተሰራ ሥዕል ነበረ የዚህ ሥዕል ሰዓሊውም ሆነ የተሳለው ልጅ ታዋቂ ባለመሆናቸው የተነሳ ጨረታውን የሚሳተፍ ሰው ጠፋ። ሁሉም ፀጥ አለ ሥዕሉንም የሚፈልገ ሰው ጠፋ። ጨረታውን ሊመለከት ከገባ ውስጥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የሟች አገልጋይ የነበረ አንድ ሰው ነበረ። ይህ ሰው የተናዛዡን ሰውዬ ልጅንም ከልጅነቱ ጀምረው ያውቁት ስለነበር ምስሉን በእጁ ቢያስገባ መልካም እንደሆነ አሰበ። አንድም ማንም ሰው ለዚህ ምስል ፍላጎት ስላላሳዩና ሠዓሊምው በማንም የማይታወቅ በመሆኑ፣ አንድም ደግሞ ልጁን ስልሳደጉት ማስታወሻ ይሆናቸው ዘንድና አነስተኛ ዋጋ ቢጠሩ የሚፎካከር አይኖርም ብለው ስላሰቡ እጃቸውን አውጥተው አነስተኛ ዋጋ ይሰጣሉ። ሰውዬውም እንዳሰበው ማንም ምሥሉን ለመግዛት ፍላጎት ሳያሳይ ቀረና ሰውዬው ሥዕሉን አሸነፈ።
በዛው ቅፅበት አጫራቹ ክብራትና ክቡራን ጨረታው ተጠናቋል ብሎ ተናገረ። ሁሉም የሰሙትን ሊያምኑት አልቻሉም ባሉበት ደንዝዘው ቀሩ። አጫራቹም በመቀጠል በኑዛዜው መሰረት የልጁን ሥዕል በጨረታ ያሸነፈ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ለልጁ በተሰጠው ዋጋ ሁሉንም እንደሚወስድ ኑዛዜው ያስገድዳል ብሎ የጨረታውን ማለቅ በያዘው የአጫራች መዶሻ ጠረጴዛው መታ።
ልጁ ያለው ሕይወት አለው።
ደግሜ እላለው ደስ ይበላችሁ።
ይህ ነው የእኛ ደስታ ሊሆን የሚገባው። በዚህ መለኮታዊ እርካታና ደስታ ውስጥ ሁሌም መገኘት እንዲሆንልን እየተመኘው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የእዚአብሔር አብ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።
ሥር ሰዳችሁ
የክርስትና ሕይወት ማደግ የሚጀምረው ወደ ታች ነው። መሰረቱ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ሚናን ይጫወታል። የሚታየው ማንነታችን የሚቆመው በመሰረቱ ነው። አንድ ዛፍ ወይም ትልቅ ሕንጻ መቆሙ የሚመሰረተው በያዘው መሰረት ነው። ክክርስቲያንም እንዲሁ በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ሕይወቱ ሊመሰረት የግድ ይሏል።
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር
'' ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ ቃሌንም ሰምቶ የሚያደርገው፥ ማንን እንዲመስል አሳያችኋለሁ። ቤት ሲሠራ አጥልቆ የቆፈረ በዓለት ላይም የመሠረተ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍም በመጣ ጊዜ ወንዙ ያን ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ ሊያናውጠው አልቻለም። ሰምቶ የማያደርገው ግን ያለ መሠረት በምድር ላይ ቤቱን የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ። '' (ሉቃ 6፥47-49)
ከፍታችን የሚለካው ወደ ታች ባደግንበት መጠን ነው። በቃሉ ተሞልተን ሕይወታችንን ቃሉ እንደሚያዘው ብንኖር ወይም ብንታዘዝ እግዚአብሔርን ደስ እናሰኛለን እኛም አንወድቅም አልጥላችሁም ከቶ አልተዋችሁም ከእጄ መዳፍ ማንም አይወስዳችሁም ብሏልና። በአንፃሩ ደግሞ ካየነው የጠላት ዲያብሎስን ሽንገላ በቃሉ እየተቃወምንና እያሸነፍን እንድንኖር ያስችለናል። ስለሆነም ሥር ሰደን በማደግ ወደ ከፍታ መውጣት በክርስቶስ ትምህርት መሆንን ይጠይቃል።
" ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ። " (ቆላ 2፥7)
በአጭሩ ከዚህ የምንረዳው ሥር በመስደድ የሚመጣ ጉዳይ አለ እነርሱም መታነፅና መጽናት። እንዚህ የሌሉበት ሥር መስደድ ከንቱ ነው። እንደቃሉ ያልሆነ ሥር መስደድ ሰማይ የማያውቀው ነው። ነገር ግን በነዚህ የታነፀ ሥር መስደድ ወደ ላይ የመውጣታችንን አቅም ይወስናል።
ያለን ምርጫ ሁለት ነው ወይ እንደ አረም መሬት ላይ ተንሳፎ በመኖር ነፋስም ሆነ ዝናብም ሲመጣ መርገፍ ወይ እንደ ዛፍ ስር ሰደን በመመስረት ምንም ቢከሰት ባለንበት መጽናት። የሚበልጠውን ቃሉ በግልፅ ነግሮናል በክርስቶስ ትምህርት ራሳችንን አንፀን በማደግ የእግዚብሔር መንግስት አገልጋይ እንድንሆን ኢየሱስ ጸጋና ኋይል ያብዛልን።
ማዳን የፈጣሪ የባሕሪው ገንዘብ ስለ ሆነ በፍጡር መዳን አይቻልም።
"እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።" (ኢሳ 43፥11)
ማዳን የእግዚአብሔር የባሕሪው ገንዘቡ ነው። መላእክትም ሆኑ ሌሎች ፍጥረታት የእግዚአብሔር የባሕሪይ ገንዘብ የሆነውን ማዳን የራሳቸው ሊያደርጉት አይችሉም፤ አይፈልጉምም። ነገር ግን ይህን ማዳን በመላላክ ሊያገለግሉ ይችላሉ። ለምሳሌ:-
እግዚአብሔር ሠለስቱ ደቁቅን (አናንያ አዛርያ ምሳኤል) ከእሳት ዳንኤልን ከተራቡ አናብስት ሊያድናቸው በፈለገ ጊዜ ማዳኑን የፈጸመው በመላእክት ተልእኮ በኩል እንደ ሆነ ከቅዱስ መጽሐፍ እናነባለን።
ሆኖም ይህ ከመከራ ሥጋ የማዳን ሥራ አሁንም የእግዚአብሔር እንጂ የተላከው መልአክ ገንዘብ አልነበረም። ለዚህም ነው ናቡከደነጾር እግዚአብሔር የፈጸመውን የማዳን ሥራ ካየ በኋላ
''...#መልአኩን_የላከ_ከአምላካቸውም_በቀር_ማንንም_አምላክ_እንዳያመልኩ_ለእርሱም_እንዳይሰግዱ_ሰውነታቸውን_አሳልፈው_የሰጡትን_የንጉሡንም_ቃል_የተላለፉትን_በእርሱ #የታመኑትን_ባሪያዎቹን_ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ። '' ሲል የማዳኑን ባለቤት የሆነውን እግዚአብሔርን ያመሰገነው። (ዳን 3፥2)
ዳንኤልንም ዳርዮስ፣ " የሕያው አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ፥ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን? " ሲል በጠየቀው ጊዜ ለዳርዮስ በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና በአንተም ፊት ደግሞ ንጉሥ ሆይ አልበደልሁምና #አምላኬ_መልእኩን_ልኮ_የአንበሶቹን_አፍ_ዘጋ እነርሱም አልጎዱኝም (ዳን 6፥20-22) ሲል ያዳነውን እግዚአብሔርን በሚገባ ክብር አክብሮታል።
ከመከራ ሥጋ መዳንን በተመለከተ ይህን ሁሉ ካየን፣ ከመከራ ነፍስ መዳን (ከኋጢአትና በኋጢአት ምክንያት ከመጣብን ፍዳ መዳን) እንዴት በፍጡራን ሊፈጸምና ሊሰጥ ይችላል? የሚል ጥያቄ ከባድ አይሆንብንም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን በተመለከተ የተናገረውን ከዚህ እንመልከት።
''ወኢያንሥአ ለነ ሊቀ ካህናት እመላእክት ወኢ እም ኀይላት እለ እሙንት ይቀውሙ ዐውደ መንበሩ አላ አሐዱ ለሊሁ ወረደ ወተሠገወ እምህላዌነ ወኮነነ ሊቀ ካህናት ወአዕረገ በእንቲአነ ሥጋሁ መሥዋዕት ለአቡሁ በአብጽሐነ ሎቱ በዘቦተ ሐመ''
ትርጉም
" ዙፋኑን ከብበው ከሚቆሙ ከመላእክት ከኀይላትም ወገን ሊቀ ካህናት አልሾመልንም። እርሱ አንዱ ወደዚህ ዓለም ወርዶ ባሕሪያችንን ብሕርይ አድርጎ ሊቀ ካህናት (አስታራቂ) ሆነን እንጂ ስለ እኛም ሥጋውን መሥዋዕት አድርጎ ወደ አባቱ አቀረበ፤ በታመመበት በሥጋው ለእርሱ ገንዘብ ለመሆን አበቃን ''
ከዚህ ሁሉ ማስረጃ የምናስተውለው ነጥብ ቢኖር፣ መጸሐፍ ቅዱስም ሆነ የአባቶች ትምህርት በመላእክት የተፈጸመ ወይም የሚፈጸም ከኋጢአት ሰውን የማዳን ሥራ ፈጽሞ የሌለ መሆኑን ነው። ስለዚህ ክርስቲያኖች ሁሉ መላእክትን ያከበርን መስሏቸው ከመላእክት መዳንን በመፈለግ እግዚአብሔርን እንዳያስቆጡና ራሳቸውንም ከእውነተኛው የመዳን መንገድ እንዳያወጡ በክርስቶስ ፍቅር እንመክራለን።
በአሁን ሰአት የብዙዎችን ጥያቄ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ሀሳብ እየመለሰና እያስተማረ ከሚገኘው በመጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር የተጻፈው ምርጥ መጽሐፍ ከሆነው '' መዳን በሌላ በማንም የለም '' ከሚለው ከገጽ 55-56 የተወሰደ። መጽሐፉን በመግዛትና በማንበብ እንድትጠቀሙበት በጌታ ፍቅር ጋበዝኳችሁ።
በሥራ መዳን
መዳን በሥራ ነው።
ነገር ግን በማን ሥራ?
እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በቃሉ ከፈጠረ በኋላ የሰው ልጅ በእጁ አበጀው ይህ ማለት እርሱ ሥራ ሰርቷል ለማለት ሙሉ ድፍረት ይሰጠናል። እንዲሁም ደግሞ አዳም ትዕዛዝ ከተላለፈ በኋላ ዳግም ሥራ በመስራት የቁርበትን ልብስ አለበሰው። የሰውማ ሥራ ራሱን እንኳ የማይሸፍን ከየበለስ ቅጠሎች ሰፍቶ ግልድም ማድረግ ነው (ዘፍ 3:፥7)። የእግዚአብሔር ልብስ ግን ማንነትን የሚሸፍን፣ ነውርን የሚደብቅ፣ እርግማንን የሚያርቅ ነው። ይህን ልብስ እግዚአብሔር ዝም ብሎ ከየትም አላመጣውም ይልቁንም ለሁለተኛ ጊዜ ስራ በመስራት ዳግም በእጁ ጣልቃ ገብነት ነው። እግዚአብሔር ስለ ሰው ስራ መስራት የጀመረው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አይደለም ከፍጥረቱ ጀምሮ ነው ማዳኑም እንዲሁ። በአሮጌው ኪዳን እንደተፃፈ
" እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም " (ኢሳ 43፥11) ያለው የሰው ልጅም ሆነ ሌላ የነፍስ ድህነትን መስጠት የሚችል ማንም ስለሌለ ነው።
እንዲሁም በአዲሱም ኪዳን መጽሐፍ ቅዱሳችን ይህን ይደግመዋል። አይደለም አንድያ ልጁ ላይ በጨከነበት በዚህ በጌታ ኢየሱስ ጸጋ ዘመን በዚያኛውም ስለ መሲሑ መምጣት በተነገረበት በጥላው ዘመንም የሚያድን አልነበረም። እግዚአብሔር እንዴት ልጁን ኢየሱስ ላይ ጨክኖ የማዳንን መንገድ በሌላ ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል?
አዎ እግዚአብሔር ያዘጋጀው የመዳን መንገድ ሥራ ነው ነገር ግን በማን የተባለ እንደሆነ በኢየሱስ ሥራ ብቻ ነው ይለናል መጽሐፋችን።
Saturday, 1 December 2018
የሚመካ በጌታ ይመካ!
'' የሚመካ በጌታ ይመካ'' (2ኛ ቆሮ 10፥17)
ትላንት የነበረህ ነገር ዛሬ አይኖርህም። ማንም ባለበት መቀጠል እንዳይችል የተፈጥሮ ግዴታ ነው። ትናንት ላይመለስ እንደሄደ ሁሉ ዛሬም ትናንት መባሉ አይቀሬ ነውና በዛሬው ማንነትህም ላይ ራስህን አታቁም። በነበረውና ባለው በሚኖረውም አልፋ ኦሜጋ በሆነው በእግዚአብሔር ተማመን። እርሱ ከፍታና ዝቅታ የሚታዘዙለት ሁሉን ማድረግ የሚችል በኋይሉ ብዛት በችሎቱም ብርታት እንድ ስንኳ የማይታጣው፣ ከመንፈሱ የማይሰፍር ወደ ላይ ብትወጣ እርሱ በዚያ አለ፣ ወደ ታች ብትወርድ እርሱ በዚያ አለና ከእርሱ እይታ አትወጣም። እርሱ የማያንቀላፉ ቸልታ የሌለበት ተመልካች ነውና እርሱን ተመካ።
ችግር ቢመጣ ብለህ ተጠንቅቀህ ይሆናል ነገር ግን የተጠነከክለት ነገር በራሱ ከፈራከው ወጥመድ አያስመልጥክምና አትመካ። የቱንም ያህል የጥንቃቄ ሰው ብትሆን ከምታውቀውም ከማታውቀውም፣ ካስተዋልከውም ካላስተዋልከውም የጠበቀህ እርሱ ብቻ ነው። አይተህ የተሻገርከውም ሳታይ የተሻገርከውም እግዚአብሔር ፈቅዶልህ ነውና በጥበቃው እምነት ይኑርህ ያ ነውና እውነተኛ ትምክህት።
የእነ እንትና ዘመድ ነኝ ብለህ ራስህን የተሻለ አማራጭ እንዳለው ሰው አድርገህ አትቁጠር። ከሰው መዛመድ ማምለጫ አይደለም ይልቅ እግዚአብሔርን በልጁ በኢየሱስ ተወዳጀው። ገና ችግር ሳይመጣ በተጠባባቂነት የያዝከው የሰው መከታ ካለ አራግፈው ሰው የጌታ ጸጋ ካልረዳው በቀር እንኳን ለአንተ ለራሱም አይሆን። ስለ አንተ ማንም ከእግዚአብሔር ፊት የሚቆምልህ የለም ከኢየሱስ በቀር። አንተን ያለ ኢየሱስ አየህ ማለት ፍፁም በደለኛና ሞት የሚገባህ ነህ። በሕይወት ዘመንህ ሁሉ በኢየሱስ መሆንህን ለአፍታ እንኳ አትርሳው። ትምክህትህ ይህ ነው።
የፈጠረህ በዓላማ ነውና የምትኖረውም በተፈጠርክበት ዓላማ ይሁን። በዓላም የፈጠረህ እርሱ ስትቆሽሽም የሚያነፃ እርሱ ነው። አፈጣጠርህንም አነፃፅህንም ያውቅበታል። መፍጠር የእርሱ እንደሆነ ሁሉ ማዳንም ገንዘቡ ነው። እነ እከሌ የቱንም ያህል በእርሱ ፊት ሞገስ ቢኖራቸውም እነሱ እንኳ በራሳቸው በፊቱ መሆን አይችሉምና በሰው አትመካ። መጽሐፍ እንደሚል '' መላእክት ስንፍና ይከሳቸዋል ሰማያትም በፊትህ ንጽሐን አይደሉም '' እኛማ እንዴት እናድፍ ይሆን???
ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል? እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ! (ኢዮ 25፥4-6)
ወዳጄ ትታይበት ዘንድ የተፈቀደልህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ማንንም አዳኝ አድርገህ አትመካ። መዳን በኢየሱስ ብቻ ነውና በዚህ ተመካ።
Friday, 30 November 2018
ወንጌል ያንፃልም ያፈርሳልም
" የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን " (2ኛ ቆሮ 10፥5)
ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልን በመታዘዝ መገንባት ያለብንን እንገነባለን አመፅን ደግሞ በዛው ልክ እናፈርሳለን፣ የሰውን ሀሳብ፣ የስጋና ደም ምክክርን በመቃወም እንገለብጣለን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንፈፅማለን። እንደ ሰው አሰራር ወንጌልን የሚሸፍንም ሆነ የሚጋርድ እናፈርሳለን። መጋረጃም ቢሆን እንቀዳለን፣ እንጨት፣ ድንጋይ ኮብልስቶን ቢሆን እንፈልጣለን፣ መቆፈር ያለብን ድረስ ሳንታክት እንቆፍራለን መገለጥ ያለበትን እውነት ሁሉ እንገልጣለን። ወንጌል ያፈርሳል፣ ያወድማል፣ ይበቀላል፣ ይቆርጣል፣ ያስወግዳል፣ ይለያል፣ ገፍቶ ይጥላል ደስ የሚለው ግን በአንፃሩ ደግሞ '' ይገነባል'' ።
አንድ የሚታወቅ የመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንመልከት። በዚህ ታሪክ መጀመሪያ ክርስቶስን እናያለን፣ በታሪኩ ውስጥም ክርስቶስን እንመለከታለን፣ በመጨረሻም እንዲሁ ክርስቶስን እናገኛለን። በታሩኩ ተዋረድ ሙሉ ክርስቶስ ይታያል። (በታሪኩ መጀመሪያ መሀል መጨረሻም ኢየሱስ ነው።) በውስጡ active እርሱ ብቻ ነው። ሲጀምር በራሱ ሲሰራም በራሱ አፍርሶም ሲገነባ ራሱ ነው።
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ ጌታ አምስት ነገሮችን አፍርሶ አምስት ነገሮችን ሲገነባ እናነባለን። ታሪኩን ስንዳስሰው ከአንዱ እርከን ወደ ሌላኛው እረከን ሲሸጋገር ክርስቶስ በነዚያ ሁሉ ውስጥ ባለመጥፋት አለ። በአጭሩ ከዚህ ታሪክ የምናገኘው ከክርስቶስ ጋር ትብብር ያለው ነገር ብቻ ነው ሲቆም የምናገኘው አላስፈላጊ ነገሮች ተቆርጠው ሲጣሉ እናነባለን። በስተመጨረሻም እርሱን ብቻ አናገኘዋለን።
ታሪኩን የምናገኘው በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አራት (በተለመደው አነጋገር የሳምራዊቷ ሴት ታሪክ) ሲሆን ፈርሰው የተገነቡትን በአጭሩ እንመልከት።
1) ሕዝባዊ ማንነት (በሕዝብና በሕዝብ መካከል ያለውን ግድግዳ)
2) የአባቶች ታሪክ፣ ወግና ቅርፅ (የተወረሰ ፀረ ወንጌል)
3) የግል ማንነት
4) የአምልኮ ስፍራ
5) መንፈሳዊ እይታ
ዝርዝር ሀሳብ:- በቅድሚያ ሙሉውን ታሪክ አንብቡት
1) ሕዝባዊ ማንነት በሕዝብና በሕዝብ መካከል ያለውን ግድግዳ
" በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት። "
(ዮሐ 4፥4)
ግድ ሆነበት የሚለው የታሪኩ ጀማሬ ነው። በጂኦግራፊካል አቀማመጥ ብንመለከት በሰማሪያ ሊያልፍ ኢየሱስ የሚያስገድደው ነገር አልነበረም። አይሁድ የሰማሪያን ሕዝብ ላለማየት መንገድ አርዝሞ ይሄዳል እንጂ በዚያ አያልፉም ነበር ምክንያቱም በሰፈሩ ማለፍ በራሱ ያረክሳል ብለው ስለሚያምኑ። ሰማሪያ በአጭሩ የአይሁድ ሕዝብ ጠላት ተደርገው ነው የሚወሰዱት የማንነታቸው ጠላት።
ጌታ ግን ሰማርይ ለመሄድ ባልተለመደ መንገድ ሄዶአል። ሰማርያን ለመርገጥ በአይሁድ ሀጢአት ተደርጎ ስለሚታሰብ እንኳን ግድ ለማስኬድ አይደለም ጭራሽ ለማለፍ አይጠቀሙበትም። ትልቅ የሕዝብ ግድግዳ ነበር። ሁለቱን ለይቶ የያዘ የሕዝብ ማንነት ጥያቄ። ስለዚህ ጌታ ይህን አመለካከት በመጣስ በስፍራው ከ60 ኪሎ ሜትር በላይ ለአንዲት ሴት ግድ ብሎት በመሄድና በመገኘት የነበረውን ልዩነት አፈረሰው። በአይሁድና በሰማርያ ያለውን የሕዝብን ልዩነት በማፍረስ አንድነትን ገነባ።
አንዱ የክራስቶስ ስራ ሁለት አንፃራዊ ውጤት አለው አንድም ማፍረስ ነው አንድም መገንባት ነው። በመካከላቸው የነበረው ጥል መሲሁን ሸፍኖ ነበር ነገር ግን ሁለቱም ተስፋ አድርገው የሚጠብቁት እርሱን ነበር። ተስፋቸው እንኳ አንድ አላረጋቸውም ነበር።
ጌታ ኢየሱስ ጊዜ ለመቀነስ አይደለም በዛ ግድ ብሎት የሄደው መለኮታዊ ተልእኮ (Divine Mission) ነበረው። የሕዝቡን አንድነት የመገንባት ዓላማ ነበረው ማለት በሙሉነት እንችላለን ምክንያቱም እርሱ ያለ ዓላማ ወይም ያለ እቅድ አንድ እርምጃ አይጓዝምና።
ፍርስራሽ አንድ ግንባታ አንድ አትሉም?
2) የአባቶች ታሪክና ቅርፅ የወረስነውን/ፀረ ወንጌል
ጌታ ኢየሱስ ሳምራዊቷ ሴት ወደ ጉድጓዱ እንደመጣች ወደ '' ውሃ አጠጪኝ '' ጥያቄ ገባና ተልእኮውን መፈፀም ጀመረ። (click መሆኗ ነው) ይህ ጥያቄ ወደ ተፈለገው መነጋገር እንዲያመጣ አስጀማሪ ሆና የተደረገች መጠይቅ ናት። (አንድ አናፂ መዶሻ ጥሎ አቀብሉኝ እንደማለቱ ነው) ሳምራዊቷ ግን የመለሰችው ተገቢውን ሳይሆን በሁለቱ ሕዝብ መካከል ያለውን ልዩነት የሚያሳይ ነው። መልሱ ኢየሱስ ከሚፈልገው ጥያቄ ጋር አልተገጣጠመም።
'' አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና። " (ዮሐ 4፥9)
ጌታም ሁለት ነገር እንደማታውቅ ነገራት
1) የእግዚአብሔር ስጦታ
1) ውሃ አጠጪኝ ያለሽ ማን መሆኑንስ
ይህን ብታውቂ አጠጣኝ ብለሽ ራስሽ ትጠይቀው ነበር። እርሱ ውሃን የፈጠረ ውሃ ፍለጋ አልመጣም ለዚህም የእሱ ጥማት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር:-
"ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።" (ዮሐ 4፥34)
ከዚህ በኃላ ነበር መፍረስ የሚገባው ሌላኛው አጀንዳ የተነሳው።
" በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል አለችው። " (ዮሐ 4፥12)
ብዙ ዘመን የተቆጠረውን የአባቶቻቸውን ትውፊት አመጣች። #አባቶቻችን #ቤተሰቦቻቸው #ከብቶቻቸው ከዚህ ጠጡ እኛም እስካሁን ከአንድ ሺ ዓመት በላይ ጠብቀነዋል (ባይፃፍም አባባሏ ወገኛ ነው) የእኛም ዘመን መልክ ይህን ተላብሷል በተለይ በሀገራችን ኢትዮጵያ። ፉከራና ቀረርቶ በዝቷል። ከወንጌል ይልቅ ወግና ስርአት ነግሷል። ከንቱ ትምክህት ተንሰራፍቷል። እንደነዚህ ያሉ መንፈሳዊ ሽፋን ያላቸው ተቃውሞች ለጌታም ተደጋግመውበታል። አይሁድ ኢየሱስን የሚጋፉት በአባቶች ስም ነበርና። አንተ '' ከእከሌ '' ትበልጣለህን እያሉ ነበር ነገር የሚፈልጉት (ዮሐ 8፥53 ተመልከቱ)። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የሚሳነው የለምና ይህንን ከንቱ መታበይ ፍርስርሱን አወጣው። እንዲህ በማለት:-
ኢየሱስም መልሶ። ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። (ዮሐ 4፥13-14)
የአባቶቻቸው ጉድጓድ የሚሰጠው ውሃ ሲጠጣ ያረካ ይሆን ይሆናል ነገር ግን ጊዜአዊ እርካታ ስጋን እንጂ የነፍስ ጥያቄን ሊመልስ አይችልም። የነፍስ መልስ ያለው ጌታ ኢየሱስ ጋር ብቻ ነው። የሚልቀው ወንጌል መጥቶ ሳለ ይህን የሚጋፋ ወግና ስርአት ቆርጦ መጣል ነው እንጂ።
ፍርስራሽ ሁለት አትሉም?
3) የግል ማንነት
አሁን ጉዳዩ ወደ ተልእኮው እየገባ ነው። ርቀት ከነበረው ወይም ከሕዝብ፣ ታሪክ፣ ትውፊትና ወግ ወጥቶ ጉዳዩ ወደ ግለኝነት መጣ። የነበረው ውይይት ውጫዊ ይዘት ነበረው፤ ውጪውን ጠርጎ ወደ ውስጥ ገባ። የተመካችበት ሁሉ ገደል ከተተው። ኢየሱስ ሲናገር የነበራት፣ አለኝ ብላ የተመካችበት ሁሉ ቀሎ አገኘችው። እጅግ በሚገርም ፍጥነት የነበራትን የሚያስተው እርካታ ፍለጋ ውስጥ ገባች። እንዲህም አለች:-
" ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው። " (ዮሐ 4፥15)
የዓለሙ ቤዛ አለኝ የምትለውን የሚያስጥል፥ ይጠቅመኛል የምትለውን አቅልሎ የዘላለም በረከት የሚሰጥ ጌታ ነው ስሙ ብሩክ ይሁን።
ይህች ሴት 3 መሰረታዊች ችግሮች ነበሩባት።
ሀ) ሳምራዊነት:- ከላይ በመጀመሪያ የተገለፀው ሕዝባዊ ግለላ። ከአይሁድ ጋር የማትተባበር። ከተናቁ ሕዝብ ወገን በመሆኗ ያለባት ችግር ነው።
ለ) የጋብቻ ችግር:- ለአምስት ጊዜ ያህል ባል ሞቶባታል። ምን ያህል በማህበረሰቡ ተፅህኖ ሊደርስባት እንደሚችል መገመት ቀላል ነው።
ሐ) ሴትነት:- በአይሁድ ልማድ አንድ ወንድ ከሴት ጋር ብቻቸውን ማውራት ያልተለመደና እንደ ነውር የሚቆጠር ነው። ሴትን የማግለል ልማድ እጅግ ክልክል ነበር ለዚህም '' ሴትን ሕግ ከምታስተምር መጽሐፉን አቃጥለው '' የሚል የአይሁድ አክራሪነት አባባል አለ የሚባለው። ይህን ማሳያ ቀጥሎ ታሪኩን ስናነብ ግልፅ ይሆንልናል።
"በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን። ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም። ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም።"(ዮሐ 4፥27)
በመሆኑም ጌታ እጅግ መልካም ነው ይህን የሴትነት አነሳነትን ከእርሷ ጋር በመሆን አፈረሰው። ሴትን በተመለከተ በትምህርት ሳይሆን በተግባር ከልማድ ወጥቶ ከሴቷ ጋር በመቆም ናደው። ማንነቷ መገንባት ጀመረ። ጌታን አግኝታ ወደ ከፍታ ጉዞ ጀመረች። አዎ ኢየሱስ ሁለንተና ቀዳሽ ነው። አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ብላ ንግግር የጀመረችው የጌታ የማንነት ፀዳል በልቦናዋ መብራት ጀመረና '' አንተ ነብይ እንደሆንህ አያለው አለችው ''
ፍርስራሽ ሶስት አትሉም?
4) የአምልኮ ስፍራችን
ስግደትና ስርአተ አምልኮ ለመፈፀም ብዙ ሰው ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ነበር። በአሮጌው ኪዳን የአምልኮ ቦታ ውስንነት ነበርና (ሐዋ 8፥27 እና ዮሐ 12፥20 ተመልከቱ)።
ጌታ ኢየሱስ ከሴቲቱ ለመጣለት ጥያቄ:-
" አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም። ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው። " (ዮሐ 4፥20)እርሱ ግን ከእንግዲህ የሚቀደስ ሰው እንጂ ቦታ እንዳልሆነ በግልፅ መናገር ጀመረ።
ገሪዛንም ሆነ የኢየሩሳሌም የነበረውን የአምልኮ ቦታነት አፈረሰው። በአንድ ላይ ሁለቱንም አእምሮዋ ውስጥ የተቋጠረውን ገመድ ፈታው። የእውነተኛ የሕያው አምልኮ ምንነት ተናገረ:-
" እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። " (ዮሐ 4፥24)
እግዚአብሔርን ለማምለክ መድከም ቀረ። ጋራና ቁልቁለት፣ ዳገትና አቀበት፤ ሜዳና ተራራ፣ ወንዝና ውቂያኖስ፣ ባህርና የብስ መንከራተት ቀረ። ለወሰኑ ድንበር ለመገኘቱ አጥር የሌለው፣ ሰማይንም ምድርንም ከቦ የሰፈረው አምላክ በእውነት (በእርሱ መገኘት በማመን) በመንፈስ (ሁለንተናዊ ራስን በመስጠት) እንደሚመለክ አበሰረና የነበረውን አፈረሰው።
አንድ መዝሙር ትዝ አለኝ:-
ባንተ መንፈስ የተነካ
ቦታ አይመርጥም የማምለኪያ
ይዘምራል በሄደበት
አያስችለው የሆንክለት።
ፈረሰ መባል ያንሰዋል።
ፍርስራሽ አራት አትሉም?
5) ስለ መንፈሳዊነት ያለንን እይታ
ዘመን ተሻጋሪ በተለይ ለተዛባ አስተምህሮ ለተጋለጠ የሚያሳርፍ ወሳኝ ጥያቄዎች።
=}አሁን የት እናምልክ? ሁሉም ቦታ!
=}መች እናምልክ? ሁሌም በሁሉ!
=}እንዴት እናምልክ? በእውነትና በመንፈስ!
=}በምን ሕይወት እናምልክ? በክርስቶስ በዳነ ሕይወት።
ሴቲቱ ውስጧ የነበሩት ሁሉ ፈራርሰውባት ግንባታው ሊጠናቀቅ አንድ ነገር ብቻ መስማት ቀርቷታል። ውስጧ ከነበረው መሲህና ከምታየው ኢየሱስ ጋር ይበልጥ ተቀራረበች። ይጠጌ አይነኬ ደርሳለች ማግኘቷ ግን አይቀርም።
'' ሴቲቱ። ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። (ዮሐ 4፥25) አሁን የምትሰማው የዘላለም ሕይወትን የሚያሰገኝ ደሰታ፣ ለዘመናት የጠበቀችው ይነገራት ዘንድ የጓጓችለት ሕያው ዜና።
'' ኢየሱስ። የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት። '' (ዮሐ 4፥26)
መስማት ያለባትን የምስራች ሰማች ከያዕቆብ ጉድጓድ ልትቀዳ የመጣችው ከኢየሱስ ቀድታ እንስራዋን ጥላ ሄደች። ያ እንስራ መጣል ያለበት፣ መተው ያለበት፣ መራቅ ያለበት ከንቱ የአባቶችን ወግ ይመስላል። ያ እንስራ በመንፈሳዊ ሽፋን የተሸፈነ ሃይማኖታዊ ከንቱ ስርአትን ይመስላል። ያ እንስራ ኢየሱስ ሊሸፍን ወይም ሊጋራ ያለን ከንቱ ትውፊት ይመስላል። እረ ወገኖች ይቆርጥላችሁ ዘንድ የሚረዳ ጸጋ አይለያችሁ። አሜን።
እሷም ሕይወት አግኝታ እንስራዋን ጥላ ሄደች እኔም መፃፌን ጨርሼ ጌታዬን በሁሉ አመስግኜ ወደ መኝታዬ አመራሁ።
መልካም አዳር።
ሼር።
Monday, 1 October 2018
በባሪያ ዋጋ
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን የከፈው ዋጋ እጅግ ውድ ነው። ይህም ፍቅሩን ያሳያል። እርሱ ስለወደደን ስለእኛ ራሱን አዋረደ ዝቅም አለ። ፍቅርን በዝቅታ ያስተማረ ሆኖም ያሳየ እንደ ጌታ ማንም የለም። ያ እስራኤልን ነፃ ያወጣል ተብሎ በቤተመንግስ የተጠበቀው ጌታ ከመንበሩ በመውረድ በከብቶች በረት ተገኘ። ሐዋርያው ጳውሎስ የጌታ ነገር ቢደንቀው እንዲህ አለ:-
እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። (ፊልጵ 2፥6-8)
ሰው አማራጭ በማጣቱ ያለ ፍላጎቱ ዝቅ ብሎ ሊኖር ይችላል ነገር ግን እንደ ጌታ ወዶና ፈቅዶ ዝቅ የሚል ማን አለ? ፍቅር ያላሸነፈው ዝቅታ፣ ፍቅር ያልገዛው ዝቅታ፣ፍቅር ያላንበረከከው ዝቅታ ከንቱ ነው። እርሱ ግን......
በፍቅር ተስቦ ወረደ ለእኛ ሲል
የፍቅሩን ትርጓሜ ገለፀው በመስቀል
ለእኛ ያላረገው ከቶ ምን አለና
አፋችን ዝም አይበል እናቅርብ ምሰጋና። ..... ተብሎ የተዘመረለትም ለዚህ ነው።
ጌታ ኢየሱስ ስለ እኔን እናንተ የዝቅታውን ጣሪያ ነካ። አምላክ ሆኖ ሳለ በባሪያ ዋጋ ተሸጠ። በሙሴ መፅሐፍ እንደምናነበው የአንድ ባሪያ መስፈሪያ ወይም መተመኛ ዋጋ ሠላሳ ብር ነው። ለዚያውም በበሬ ለተወጋ ባሪያ የተተመነ የባሪያ ዋጋ።
" በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታቸው ይስጥ፥ በሬውም ይወገር። " (ዘጸ 21፥32)
ሰይጣን ወደ ልቡ ሹክ ያለውና ጌታን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ከሰቃዮች ጋር የተስማማውም በዚህ ዋጋ ነው።
" ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት። " (ማቴ 26፥15)
እኛ አይደለም ራሳችንን ያለንን ነገር (ቁስ) እንኳ ዝቅ አድርገው ሲገምቱብን አንወድም እርሱ ግን በበሬ በተወጋ ባሪያ ሚዛን አስቀመጡት። ዋጋ የማይተመንለት ሂሳብ አወጡለት። ስፍር የሌለውን እርሱ ስለእኛ እጅግ በመዋረድ ዛሬ እኛን እርሱ ባለበት በከፍታ ላይ አስቀመጠን። ጌታ ሆይ እጅግ ተመስገን ስላንተ ማውራት እንድወድ ስላደረከኝ። ስላንተ በእያንዳንዱ ዛሬ ብመሰክር አልጠግብም ይህን መፈለግንም ማደረግንም በእኔ ያኖርክ አባቴ ዘላለም ክበርልኝ።
ምክር:-
1) "ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። " (ገላ 5፥13)
2) " አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ። " (1ኛ ጴጥ 2፥16)
Tuesday, 18 September 2018
አንድ መካከለኛ
" አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። "
(1ኛ ጢሞ 2፥5)
(1ኛ ጢሞ 2፥5)
ጽድቅ ሆኖልናል!
" ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 64፥6)
(ትንቢተ ኢሳይያስ 64፥6)
Tuesday, 4 September 2018
አዲስ ፍጥረት
እውነተኛ ክርስቲያኖች እምነታቸውን በክርስቶስ ያደረጉና የደህንነታቸውም ብቸኛ መንገድ ህግን መፈፀም ሳይሆን በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆኑ እንደሆኑ ሐዋርያው ጳውሎስ ይናገራል (ገላ 6፥15) እና (2ኛ ቆሮ 5፥17)
አዲስ ማለት ፍፁም የተለወጠ ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ይለውጣል (ፊሊጵ 3፥21) እንጂ አያሻሽልም። ይህ መለወጥ መሰረታዊና ከመቅፅበት የሚሆን ምስጢራዊና የማይመረመር መለኮታዊ ስራ ነው። በሰው ካልኩሌሽን የማይሆን በመደመርና በመቀነስ የማይመጣ፣ ጥናትና ምርምር በማድረግ የማይደረስበት፣ የስጋና ደም ምክክር የሌለበት፣ ከሰው እጅ የፀዳ ነው። በምሳሌ ለመግለፅ ያህል:- ከዚህ በፊት አንድ ሰው ሃያ(20) ጃምቦ ድራፍት ይጠጣ ከነበረና በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ አዲስ ማንነት ሲመጣ መጠጣቱን ያቆማል እንጂ ቀንሶ አምስት(5) ጃንቦ ድራፍት ወደመጠጣት ይመጣል ማለት አይደለም። በክርስቶስ አዲስ መሆን ማለት ያ አሮጌውን ሰው አስወግዶ አዲሱን መንፈሳዊ ሰውነት መልበስ ነው።
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐ 3፥3 ላይ
" እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። "
እንዳለው በዚህ ዳግም ልደት ወይም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን የግድ ነው።
ተፈጥሮአዊ ማንነትን ትተን የነፍሳችንን አቅጣጫ በመቀየር ክርስቶስን ወደ መምሰል ሕይወት ማቅናት ይኖርብናል። በዚህ ለውጥ ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምፅ እንሰማ ዘንድ አዲስ ጆሮ ይሰጠናል (ከምትሰሙት ተጠበቁ ስሚል ቃሉ)፣ እግሮቻችን በቀናው ጎዳና ቃሉን ለመፈፀም ይራመዳሉ፣ ከሕግ በታች ሳይሆን ዓለምን በሞላውና ባጥለቀለቀው በክርስቶስ ፀጋ በመደገፍ እንደ ቃሉ በሕይወት በመኖር የኋላችንን እየረሳን ወደ ፊት መዘርጋት ወደ ፊት.........
በመለወጥ ውስጥ ባለ ሕይወት እንደ እግዚአብሔር ቃል ልንገለጥ ይገባናል። ከእኛ የሚጠበቀው ለዚህ ዓለም የማይመች ወይም የማይስማማ በመሆን አዲስ ፍጥረት መሆናችንን በመግለጥ ለሌሎች መትረፍ ይጠበቅብናል።
በእኛ ውስጥ መፈለግንም ማድረግም የሚሰራ ቅዱስ አባታችን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ስም በሚያስፈልገን ጊዜ የሚረዳንን ፀጋ ያብዛልን።
Monday, 3 September 2018
ሰባቱ ''እኔ''ዎች
ብርሃን ሁሉን እንዲያሳይ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ሁሉ ይጠቀምበት ዘንድ የሰጠው ፀጋ ነው። አልታይ ያለንን ወይም ለእይታ አዳጋች የሆነብንን ነገር ብርሃን በዓይናችን እንድናይ ዋናውን ሚና ይጫወታል። እግዚአብሔር አባታችን እኛን ከመፍጠሩ አስቀድሞ በሰማይና በምድር ላይ አስቀድሞ የፈጠረው ነገር ቢኖር ብርሃን ነው። " እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ። "
(ዘፍ 1፥3) ለዚህም የሰው ልጅ መልካሙ ነገሮችን በሙሉ በብርሃን ይመስለዋል፡፡ ነገር ግን እርሱን እንድንረዳውና እንድናውቀው የልቦናችንን ዓይኖቻች ለማብራት አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ የዓለም ብርሃን አድርጎ ላከልን።
በተፈጥሮ ፀጋ ካገኘነው ብርሃናት (ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ መብራት፣ እሳት፣ ወዘተ) ተቃራኒ የሆነ ጨለማ ስላለው እነዚህ ብርሃናት ጊዜያዊ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ከፀሐይ የሚገኝ ብርሃን ጊዜያዊ እንጂ ቋሚና አስተማማኝ ስላልሆነ አንድ ጊዜ ይበራል ሌላ ጊዜ ደግሞ ይጠፋል፡፡ ምክንያቱም የፀሐይ ብርሃን በቀን በርቶ በሌሊት ጨለማ ይጋርደዋልና በቀንም ደመና ይከልለዋልና፡፡ በተፈጥሮ ሂደቶች የሚገኙት ብርሃን ሁሉ ተቃራኒ ሁኔታ ስላላቸው እውነተኛ ብርሃን ሊባሉ አይችልም።
እግዚአብሔር አምላክ ሙሴን እንዲህ አለው።
በምስክሩ መጋረጃ ውጭ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ያሰናዳው፤ ለዘላለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን። በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያሰናዳቸው። (ዘሌ 24፥3-4)
ይህ በጨለመ ጊዜ እንዲበራ የታዘዘው ብርሃን የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃንነት የሚያሳይ ሲሆን በጨለማ ለነበርን ለእኝ የበራልን እውነተኛ ብርሃን ነው። መፅሐፍም እንደሚል " ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ " (ኤፌ 5፥8) ። የመቅረዙ መብራት የጨለማው ጊዜ እስከሚልቅ ድረስ እንደማይጠፋ ሁሉ የጌታም ብርሃንነት የማይጠፉና ፍፁም የሆነ ዘላለማዊ ነው። እርሱ ጨለማን ያሸነፈ ለሁሉ የሚያበራ ለዓለም የሚበቃ የማያቋርጥ ስፍራና ጊዜ የማይወስነው የማይጠልቅ ፀሐይ ነው።
መቅረዙ ዘይት የሚይዝና ብርሃን ማብሪያ ያሉት ሰባት ዘንግ ሲኖረው በሰባቱም ቀዳዳዎች ብርሃን ያለማቋረጥ ሌሊቱን በሙሉ ያበራል። ሰባት ቁጥር በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአንድን ነገር ፍፁምነት ወይም ሙሉነት ያሳያል። በበደልና በኋጢአታችን ሙታን በነበርን ጊዜ፣ በሞት ጥላ ውስጥ ሆነን ጨለማ ውጦን ሳለ ለእኛ '' እኔ '' ብሎ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ተፅፈው የምናገኛቸውን የክርስቶስ ኢየሱስ ሰባቱ እኔዎች በጥላነት ያሳያል።
እነዚህ እኔዎች ፍፁም ናቸው። ጨለማ ከቶ የማይችላቸው ተወዳዳሪም ተገዳዳሪም ብሎም ምትክና ተወካይ የሌላቸው ፍፁምና የፀኑ የጌታና የጌታ እኔዎች ናቸው። ይህን ማለት የሚቻለው ከጌታ በቀር ማንም የለም። የመቅረዙ መብራት በጨለማ ወይም በሌሊት እንደማይጠፋ ሁሉ የጌታም እኔዎች በጨለማ ለነበርነው የመጣልን ዘላለማዊ ብርሃን ናቸው። ፀንተን የመቆማችን ምስጢር።
አዎ እውነተኛ ብርሃን ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ በፍቃዱ አሳልፎ የሰጠ የናዝሬቱ ኢየሱስ። አለ ዛሬም የፅድቅ ፀሐይ ባለማቋረጥ የሚያበራ በማያልፍ የሕይወት ኋይል በግርማው ቀኝ የተቀመጠው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ። ፀሐይ በሚበራባት ዓለም እኔ ነኝ እውነተኛ ብርሃን ብሎ የመጣ። በሚያልፍ ብርሃን ውስጥ እንመላለስ ለነበርን ለእኛ የማያልፍ ብርሃን ሆኖ የመጣ። ቀን በርቶልን ማታ የሚጨልምብን በብልጭ ድርግም ውስጥ ለነበርን ለእኛ ዘላለማዊ እውነተኛ ብርሃን የሆነልን ኢየሱስ ስሙ ብሩክ ይሁን።
ታዲያ በእርሱ ብርሃንነት እኛን ልጆቹን የዓለም ብርሃን አደረገን። '' እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ'' ብሏልና (ማቴ 5:14)። ጨረቃ ከፀሐይ ብርሃን ወስዳ እንደምታበራ ሁሉ እኛም በእርሱ ብርሃንነት እናበራለን። የመቅረዙ ዘይቱ ሲሞላ ክሩ በመንደድ ያበራል። ያለ ዘይቱ መቅረዙ አይበራም። ፀጋና እውነትን ተሞልቶ በእኛ ያደረው የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የምክርንና የኋይል መንፈስ፣ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራ የኢየሱስ መንፈስ፣ መንፈስ ቅዱስን እንድናበራ ያደርገናል። በተራራ ያለች ከተማ ብርሃኗ ልትሰወር እንደማይቻላት ሁሉ እኛም የጌታን ብርሃንነት በዓለም ላይ በማብራት በጨለማ ላሉት መፍትሄ ልንሆን ይገባል።
ሰዎች እንቅፋት ሊመታቸው ይችላል ብላችሁ የውጪ መብራት አብርታችሁ ሊሆን ይችላል በጨለማ ውስጥ ያለን ሰው ግን ከመውደቅ አያድነውም። የተፈጥሮ መብራት ምናልባት ከውጪ ወደ ቤት ሊያስገባን ይችል ይሆናል ነገር ግን ከድቅድቅ ጨለማ (ከኋጢአት) ወደ የማይጨልም የነፍስ ብርሃን ግን አያደርሰንም። የውስጥን ጨለማ የገፈፈ የነፍስን ዐይን የገለጠ ብርሃን ኢየሱስ ብቻ ነው። ስሙ ይቀደስ።
ወደ አንድ ታሪክ ልውሰዳችሁ። የተፈጥሮ ብርሃን ብለን ከገለፅናቸው ብርሃን ውስጥ አንዱ እሳት ነው። ይህ የተፈጥሮ ብርሃን እና እውነተኛ ብርሃን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ተገናኝተው ነበረ። ኢየሱስ ለስቅላት በአይሁድ እጅ ተይዞ ሳለ ጴጥሮስ እስከ ሊቀካህት ግቢ ድረስ ተከትሎት ለጨለማው ከተለኮሰው እሳት አጠገብ ነበረ። እሳቱ ውስጥ ከነበረው ብርሃን ይልቅ ኢየሱስ እጅግ የሚልቅ ብርሃን ሆኖ ሳለ ጴጥሮስ የክርስቶስን ብርሃንነት በጊዜው ሊገልጥ አልቻለም። ያ የእሳት ብርሃን አሳይቷቸው አንተ ከእርሱ ወገን አይደለህምን? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የዓለም ብርሃን አጠገቡ ቆሞ እርሱን በወቅቱ ሊገልጠው አልቻለም። ለከባድ ፀፀት ዳረገውም።
ከዚህ እጅግ ብዙ መማር አለብን። የእግዚአብሔር ዓላማ የጴጥሮስን ድካም ለመንገር ብቻ ሳይሆን እንድንማርበት ዘንዳ ነው። ወይ አርቴፊሻል ብርሃን ወይ የኢየሱስን ብርሃን አብርተን መኖር? በየትኛውም ሁኔታ ብንሆን እውነተኛውን ብርሃን መምረጥ ይሁንልን። በዚህ ዓለም እኛ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ቃል '' ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ '' እንደሚል በተገኘንበት ቦታ በመንገዳችን ሁሉ በትንሳሄው ብርሃን ደምቀን፣ በሕይወት እንጀራችን ብርሃን ፍንትው ብለን፣ በመልካሙ እረኛ ብርሃን ተመርተን፣ በወይኑ ግንዳችን ብርሃን አድገን፣ በፅድቅ በራችን ብርሃን ገብተን፣ እንደ ብርሃን ልጆች እንመላለስ (ኤፌ 5፥10)። አሜን።
Thursday, 16 August 2018
የጽድቅ መንገድ
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ከመምጣቱ አስቀድሞ እውነተኛ የጽድቅ መንገድ አልታወቀም ነበር፡፡ ነገር ግን ዛሬ ሰማጣዊ አባታችን እግዚአብሔር እውነተኛውን የጽድቅ መንገድ አሳየን፡፡ ይኽውም የጽድቅ መንገድ የተባለ አንድ ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ከሱ በቀር ሌላ ወደ ሰማያዊ አባታችን ወደ እግዚአብሔር የሚወስድ የለም፡፡ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ የእውነትና የሕይወት መንገድ ነኝ በኔ በኩል ካልሆነ በቀር አንድም ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎ ተናግሮዋል፡፡(ዮሐ 14÷6)ስለዚህ እኛ ሁላችን ይህንን የማያሳስት እውነተኛውን የጽድቅ መንገድ ክርስቶስን ብቻ ይዘን ከሄድን ዘወትር እየናፈቅን አባታችን ሆይ እያልን ከምንጠራው ከሰማያዊ አባታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ሰማያዊ ሀገራችን ወደ መንግስተ ሰማያት እንደርሳለን፤ ዳግም በስራችን እንጸድቃለን መንግስተ ሰማያት እንገባለን ብለን አንመካም፤ የምንጸድቅበት ሃይማኔታችን ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ እናንት ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደኔ ኑ እኔም አሳርፋችኃለሁ ቀምበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ›› ብሏል (ማቴ 11÷58)፡፡ እንዲህም ማለቱ በእኔ ጽኑ ሲል ነው፡፡
ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ጽድቅ በሃይማኖት ብቻ እንዲገኝ ስራ በመስራት እንዳይገኝ በጻፋቸው መልእክቶች ሁሉ ያስተምረናል፡፡ ‹‹ ሰው ስራ ሳይሰራ በሃይማኖት ብቻ እንዲጸድቅ እንውቃለን ›› ብሏል፡፡ (ሮሜ 3÷28) ከዚህም ቀጥሎ በ4ኛው ምዕራፍ በ4ኛውና በ5ኛው ቁጥር የሚሰራ ሰው ዋጋው አይቆጠርለትም እንዲያው እንደሚገባው ሰራ ይባላል እንጂ፡፡ የማይሰራ ግን ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ በእግዚአብሔር ቢያምን ማመኑ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል ብሏል፡፡ ደግሞ ይልቁንም በጣም የሚያስረዳ በኤፌሶን መልእክቱ ‹‹ አምነን በጸጋው ድነናልና እናንተም የዳናችሁ በእግዚአብሔር ቸርነት ነው እንጂ በስራችሁ አይደለም ማንም የሚመካ እንዳይኖር ›› ብሏል (ኤፌ 2÷8-9) ዳግም ወደ ገላትያ ሰዎች በጻፈው በ2ኛው ምዕራፍ በ21ው ቁጥር ‹‹ የእግዚአብሔርን ጸጋ አልክድም የኦሪትን ስራ በመስራት የሚጸድቅ ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ ለከንቱ የሞተ ነዋ ›› ብሎ ተናግሮአል፡፡ ይህም ሰው ሁሉ በስራው እንዳይጸድቅ በእግዚአብሔር ጸጋና በክርስቶስ ሞት እንዲጸድቅ ያስረዳል፡፡ ክርስቶስ መሞቱ ሰው በስራው መጽደቅ የማይችል ስለ ሆነ ነው፡፡
ምንጭ:- የኢት/ኣ/ተ/ቤ/ክ '' የቤተ ክርስቲያን ጸሎት '' ከሚለው መጽሐፍ ከገጽ 93 የተገኘ።
Tuesday, 14 August 2018
ከፍተኛ በዓል
ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ (መዝ 81፥2-3)
በዓለማችን ብዙ ዓይነት በዓላት አሉ ደግሞም ይከበራሉ። ነገር ግን ሁሉም ታላላቅ ወይም ከፍተኛ በዓላት አይደሉም። በክርስቲያኖች ዘንድ እጅግ የላቀ በዓል አለ እርሱንም ሁልጊዜ በልባቸው ይዘውት ይዞራሉ። ይህም በዓል እግዚአብሔር በልጁ በጌታ ኢየሱስ ደም የተነሳ የሁላችንንም በደልና ኋጢአት ይቅር ያለበት ነው።
መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር በክርስቶስ መስዋህትነት የእግዚአብሔር ማዳን የጀመረው ወይም የታቀደው በመለኮት ጉባኤ ከዓለም ፍጥረት በፊት ሲሆን (ራእ 13፥8 እና 1ኛ ጴጥ 1፥18-21) በማስመለጥ ተምሳሌነቱ የታየው የእስራኤል ህዝብ ዓለምን ከምትወክለው ከግብፅ ባርነት አስወጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲያስገባ ነው። በመጨረሻም ይህ ማዳን ህያው የሆነው/ የተገለጠው በቀራኒዬ መስቀል ላይ የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ቅዱስ ደሙን ሲያፈስ ነው።
እስራኤላዊያን ለብዙ ዘመናት ከነበሩበት ባርነት እግዚአብሔር በራሱ የጊዜ ሰሌዳ ቀጥሮ የሚያወጣበት ቀን አመጣ። ይህ ቀን ለግብፅ ቤት የሀዘን፤ ለእስራኤል ቤት የምህረት ቀን ነበር። እግዚአብሔር በአንድ ሌሊት ሁለት ስራ ሰራ። አንዱም ህዝቡን ከግብፅ አወጣ አንድም ደግሞ ግብፅን በመቅሰፍት መታ።
ለአንዱ ሞት
ለአንዱ ነፃነት
በአንዱ ሌሊት
ታዲያ በግብፅ የሚኖሩ እስራኤላውያን መቅሰፍቱ ባለፈ ጊዜ እንዳያገኛቸው እግዚአብሔር እንዲያደርጉት ያዘዛቸው አንድ ነገር ነበር። ነውር የሌለበትን የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ወስደው እንዲያርዱ፤ ከደምም ወስደው በሚገቡበት ቤት መቃኑንና ጉበኑን እንዲቀቡት ነበር። ደሙ በጉበኑና በመቃኑ ያለ ሰው መቅሰፍቱ ያልፈው ነበር። ደሙ በመቃኑና በጉበኑ የሌለ የግብፅ ቤት ግን መቅሰፍቱ ያገኘው ነበር።
እግዚአብሔር ይህን ብቻ አይደለም ለእስራኤል ያደረገው '' በዚያም ቀን እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ከሠራዊታቸው ጋር ከግብፅ ምድር አወጣ። '' (ዘጸ 12፥51) መውጣታቸውን ተከትሎ ምርኮ ሊያደርግ ከኋላ የመጣውን እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጠው መፍትሄ የፈርኣንን ሰራዊት ዋጣቸው።
ለአንዱ መንገድ
ለሌላው ሞገድ
ከዚህም የተነሳ ሙሴና የእስራኤል ህዝብ ለእግዚአብሔር እንዲህ ብለው ዘመሩ
'' በዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ። በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ። ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፥ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ። እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው። '' (ዘፀ 15፥1-3)
እስራኤል ይህን የዘመሩት እግዚአብሔር ያደረገላቸው ትልቅ ስራ ስለነበረ ነው። ይህንን ነብየ እግዚአብሔር ዳዊት በመግቢያ ባለው መዝሙር እንደምናነበው በከፍተኛ በዓላችን ለእግዚአብሔቅ ዘምሩ ከግብፅ ባርነት መውጣታችን ይህ ለእስራኤል ስርአቱ ነውና ብሏል። (መዝ 81፥5)። አዎ ለእስራኤል እንደ ፋሲካ ያለ ከፍተኛ በዓል የለም። ለእኛ ለክርስቲያንስ?
እግዚአብሔር ነውር የሌለበት በግና ፍየል ሰውተው በመቃንና ጉበን ላይ እንዲቀቡ ያዘዘው ደም ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ደም ያመለከተ ነበር። የእግዚአብሔር በግ የሆነው ክርስቶስ ለእኛ መስዋዕት ሆኖ ደሙን አፍስሶ ከነበርንበት ጨለማ ነፃ መውጣታችን ወደሚደነቅ ብርሃን መምጣታችንን ከሚናገሩ ምሳሌ ዋንኛው ነው ማለት ይቻላል። የኤፊሶን መልእክት ፀሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው በበደልና በኋጢአታችን ሙታን የነበርን እኛን ክርስቶስ ባፈሰሰው ደም እንዲሁ በፀጋው ሕይወት ሰጠን ስሙ ይባረክ።
ዛሬ እኛ ክርስቲያኖች የቤታችን መቃንና ጉበን ላይ የበግና የፍየል ደም አንቀባም። ይልቁን በልባችን መቃንና ጉበን ላይ የጌታ ኢየሱስን ደም እረጭተናል በመሆኑም ከደሙ ኋይል የተነሳ የእግዚአብሔር ቁጣ ልክ የእስራኤልን ቤት ደሙን እያየ እንዳለፈ ሁሉ የእኛም የዘላለም መቅሰፍት ከእኛ አልፏል።
ዓመት እየጠበቅነው የምናከብረው በዓል ሳይሆን በእያንዳንዱ ዛሬ በተሰጠን የቀን እድል ማዳኑን እያወራን ወደ ፊት የምንዘረጋበት የዘላለም በዓል። ይህ በዓል በፍፁም በሌላ የማይተካና የማይደበዝዝ ሳያቋርጥ እስከ ወዲያኛው እጅግ በልባችን የታተመ ከፍተኛ በዓላችን ነው። በዓል ስል ስርአት አይደለም መለኮታዊ ሙላት እንጂ። ዓለም የማይሰጠን በጌታ ብቻ የሆነ ፍፁም ሰላም፣ መውጣት የሌለበት ፍፁም እረፍት፣ ሀዘን የሌለበት ፍፁም ደስታ፣ ግብዝነት የማያውቀው ፍፁም ፍቅር እረ ስሙ ይባረክ። ማን ይሄን ይሰጣል???
Wednesday, 25 July 2018
የጽድቅ ልብስ
ለሰው ልጅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሚባሉት ጉዳዮች መካከል ልብስና መጠለያ ናቸው። እኛም እነዚህን ነገሮች ከገሀዱ ዓለም ራሳችንን የምንሸፍንበት ዋንኛ መጠቀሚዎቻችን ናቸው። ሰዎች ሁላችንም ስንባል ሳንሸፈን መኖር አንችልም። በህይወት ዘመናችን በሙሉ በሚያስብል ሁኔታ በሚሸፍነን ውስጥ ተከልለን የምንኖር ጥገኞች ነን።
የመጀመሪያዎቹ ፍጥረታት የሆኑትን አዳምና ሔዋንን ብንመለከት በኋጢአት ከወደቁ በኋላ ክፉንና ደጉን በመለየታቸው ራሳቸውን የሚሸፍን የኮባ ቅጠል እንደለበሱና ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚያስፈልገውን የሚያውቅ ቸር ነውና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በጥላነት የሚያሳየውን የበግ ቁርበት አድርጎላቸው በሚበልጠው እንዳለበሳቸውና እንደሸፈናቸው መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
በብሉይ ኪዳን የሰውን በደል መርምሮ በማወቅ የሚታወቀው የዳዊት ልጅ ጠቢቡ ሰለሞን ነው። ስለ ሰለሞን ሁላችንም ከልጅነታችን ጀምሮ የምናውቀው በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተፃፈ አንድ ታሪክ አለ። (1ኛ ነገ 3፥16-28) ሰለሞን እንዴት አድርጎ ሁለቱን ሴቶች እንደመረመረና ሐሰተኛዋን ከእውነተኛይቱ እንደለየና እውነቱን እንዳጋለጠ ብሎም ጉዳዩንም እስራኤል ሁሉ እንደሰሙ ይታወቃል።
አብዛኞቻችን ማጋለጥ ብቻ እውነት የሚመሰለን እንኖር ይሆናል ነገር ግን መሸፈንም እውነት ነው። መፅሐፍ እንዲህ ይላል
የእግዚአብሔር ክብር ነገርን መሰወር ነው፤ የነገሥታት ክብር ግን ነገርን መመርመር ነው።
ምሳ 25፥2
እግዚአብሔር ሸፋኝ አምላክ ነው። የአደባባይ ነውራችንን በመሸፈን በጉዋዳ የሚገስፅ መልካም አባት። እግዚአብሔር የእኛ ነውር በአደባባይ እንዲጋለጥ አይወድም ለዚህም እኛ ከሰዎች ጋር እርስ በእርስ ባለን ግንኙነቶች ችግር እንኳ ቢፈጠር እንደ ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 18፥15 መሰረት ወንድምህ ቢበድልህ በመጀመሪያ ብቻህን ውቀሰው ይላል። ይህ የሚያሳየው ምን ያህል እግዚአብሔር ነውራችንን ለመሸፈን እንደሚፈልግ ነው። በሌላ በኩል ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ (ገላ 6፥1) ይላል ታዲያ ምን ያህል ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ እንደሆነ ማሰብ አያዳግትም። መሸፈን ትኩረት የሚያስፈልገው ወሳኝ ጉዳይ ነው።
የሰው ልጅ ህልውና የሚቀጥለው በመሸፈን ውስጥ ነው። መዝሙረኛው ንጉስ ዳዊት ያልተሰራ አካሌን ዐይኖች አዩኝ ብሏል። ያልተሰራ ማንነታችንን እግዚአብሔር ሸፍኖን ነው የሚሰራን። አንድ ህንፃ ሲገነባ በለያዩ ምክንያቶች ዙሪያቸው ተሸፍነው ግንባታቸው ይከናወናል። ግንባታውን የሚቆጣጠረው መሃንዲስ ወይም ኢንጅነር የሚሰራውን ህንፃ መጨረሻ እያወቀው ነው መሰረት ጥሎ እስከ መጨረሻው ግንባታውን የሚያከናውነው። በውጭ የሚያየው ግን ህንፃው አልቆ ካላየው መጨረሻው አያውቀውም። አቤት እግዚአብሔር እጅግ መልካም አባት እኮ ነው። ጋርዶን ይሰራናል ስሙ ይባረክ።
እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው ምድሪቱን በከበበው በልጁ ክቡር ደም እንድንሸፈን ይፈልጋል። አዎ እርሱ ዓለምን በፍቅር ካጥለቀለቀው የክርስቶስ ደም ተሸፍነን እኛን ቀጥታ ሳይሆን በጌታ ኢየሱስ በኩል እንድንታይ ይሻል። ብቸኛው አርነት መውጫ ልጁ ነውና። ታዲይ በዚህ በገሀዱ ዓለም እንዴት እንሸፈን ብትሉ መፅሐፍ ቅዱሳችን በተደጋጋሚ የፅድቅ ልብሳችን የሆነውን ኢየሱስን ለብሰን እንድንመላለስ ያሳስባል።
ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት
ሮሜ 13፥14
እግዚአብሔር አምላክ ፍቅር ነው። ፍቅሩም የዓለምን ኋጢአት በልጁ ደም ሸፍኖ የሚያኖር ደግ አባት ነው። እርሱ በራሱ ፍቅር ተመስርቶ የሚኖር አፍቃሪ አምላክ ነው። ፍቅር የሆነው እርሱ ደግሞ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ብሎ በመፅሐፍ ነግሮናል በ1ኛ ጴጥ 4፥8። ከሁሉም ፍርድ እንድንድን የዘላለም ጠላታችን ከሆነው የወንድሞች ከሳሽ እንዲያፍር ያልተሸፈነ ማንነት አለን ብላችሁ የምታስቡ ፍፁም በሆነ መፀፀት ከኋጢአት ሁሉ በሚያድነው በጌታዬ ኢየሱስ ደም ሰውነታችሁን አጥባችሁ አዲሱን ልብሳችሁን ክርስቶስ ኢየሱስን ልበሱት። እግዚአብሔር የትናንት አይደለም የቅድሙን ማንነታችሁን አያይም ይልቁንም የአሁኑን ልባችሁን ነውና የሚያየው ደስ ይበላችሁ።
ምክር
ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
ኤፌ 4፥22-24
Monday, 23 July 2018
ቅዱሱ መስዋዕት
እስራኤልን ከአራት መቶ ሰላሳ ዓመት በኋላ እግዚአብሔር ከግብፅ ባርነት እንዲያወጣቸው ያቀረበው መስዋት አንድ ነው (ዘፀ 12፥40 ጀምሮ)። ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ ሌላ አርባ ዓመት የበረሀ ጉዞ ከፊታቸው አለ። ለዛውም እጅግ አስቸጋሪ መንገድ። በረሀው የሚወክለው ይህን ዲያቢሎስ የሚገዛውን ዓለም ሲሆን የቀረበው መስዋት ደግሞ ጥላነቱ ጌታ ኢየሱስን ነው።
ሙሴና አሮን እንደታዘዙት መስዋቱን ካቀረቡ በኋላ በዚያው ቀን እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ከነሰራዊቶቻቸው ከግብፅ ምድር አወጣ። ከግብፅ ባርነት ቀንበር ነፃ አወጣ። ከፈታኝ የአርባ ዓመታት ጉዞ በኋላ ወደ ተስፋይቱ ምድር ገቡ።
የሰው ልጅ ከነበረበት የኋጢአት ግዞት ወይም ከሞት ባርነት ግን ነፃ የሚያወጣው አንድ እውነተኛ ቅዱስ መስዋት ያስፈልገዋል። ከአዳምና ሔዋን መተላለፍ ጀምሮ የሰው ልጅ በዚህ እስራት ውስጥ ነበረ። ነገር ግን እስራኤልን ከግብፅ ባርነት እንዳወጣው የሰው ልጅንም ከዚህ የሚያወጣ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የተወደደ የመአዛ ሽታ ቅዱስ መስዋት መታረድ አለበት። ይህም መስዋት የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ከኋጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን የመሰለው የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው።
ኢየሱስ ለዓለም የተሰዋ ሕዝቡንም ከሞት ባርነት ነጻ ያወጣ የነበረብንን ኩንኔ ያስቀረ። በደሙ ማስተሰርያ ይሰማን የነበረውን በደለኝነት ከላያችን ያነሳ ቅዱስ መስዋት ነው። እግዚአብሔር እስራኤልን መና ከሰማይ እያወረደ ሲራቡ እያበላ፣ ሲጠሙ ከዓለት ላይ ውሃ እያፈለቀ ጥማቸውን ቆረጠ። እኛ ግን ዛሬ በነገሮች ሁሉ በድካማችን የሚራራልን ሊቀካህናታችን፣ ተበልቶ ዳግም የሚያስርበውን ሳይሆን፣ የበረከት መና ሳይሆን የሕይወት እንጀራችን፣ ከአለቱ ፈልቆ እስራኤላዊያን ዳግም እንደተጠሙት ሳይሆን የሕይወት ውሃ የናዝሬቱ ጌታ ለእኛ ሰጠን።
እስራኤልም (የብሉይ ኪዳን ሕዝብ) እኛም (የአዲሱ ኪዳን ሕዝብ) የተሰጠን ከሰማይ ነው ልዩነቱ እነሱ የተሰጣቸው ከሰጪው የታዘዘላቸውን በረከት ሲሆን እኛ ግን ሰጪውን ነው፣ ምንጩን ነው ስሙ ይቀደስ። የበረከቱ እንጀራ ጊዜአዊ ነው የእኛ ግን ዘላለማዊ ነው።
የእስራኤል ህዝብ ተስፋይቱን ምድር ወርሰውም ለኋጢአት በየጊዜው ለእግዚአብሔር መስዋታቸውን ይሰዋሉ እኛ ግን በአንዱ መድሃኒት የዛሬ 2010 ዓመት የፈሰሰው ደም አሁንም ትኩስ ነው። አንዴ ለዘላለም ባፈሰሰው ደም ዘላለም ይቅር እያስባለ የሚኖር ቅዱስ መስዋት ነው። መፅሐፍም እንደሚል የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኋጢአት ሁሉ ያነጻል (1ኛ ዮሐ 1፥7)። ከዚህ ላይ ሌላ ለኋጢአት የሚቀርብ መስዋት የለም። ይህ ደም ለዘላለም በቂ ነው። እግዚአብሔር በኋጢአት ምክንያት እኛን ይቀጣ የነበረውን ፍርድ ሁሉ ጌታ መስቀል ከፍሎታል። ምንም ዓይነት ጌታ ለኋጢአት ያልከፈለው ዋጋ የለም።
ከምንም በላይ እጅግ ደስ ሊለን የሚገባው እግዚአብሔርን ያመኑ እስራኤላዊያን ተስፋ ያደረጉትን ምድር ከነአንን አገኙ እኛ ግን " በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤(የዮሐንስ ወንጌል 3: 36) ነው የተባለነው። እዳችንን ከፍሎ ወሰደን። ኢየሱስ ለኋጢአታችን ሞቶ ለጽድቃችን ከሙታን መካከል ተነሳ እኛንም በእርሱ የምናምን ሕያዋን አደረገን። አሁን በማያልፍ የሕይወት ኋይል በግርማው ቀኝ ባለበት በዚያ ስፍራችን ሆነ። በዚህም እጅግ ደስ ይበለን።
ዛሬም የኢየሱስ ደም ከኋጢአት ያነጻል።
ዛሬም የናዝሬቱ ጌታ ያድናል።
ዛሬም ሊቀካህናታችን በድካማችን ይራራል።
ዛሬም ኢየሱስ አልተወንም።
የእምነት ስሌት
ፒስቲስ በግሪክ ቋንቋ እምነት ማለት ሲሆን ትርጉሙም ሙሉ የልብ መሰጠት፣ በጥልቀት የተያዘ ከአመክንዮ ኋይል በላይ የሆነውን እግዚአብሔርን ማመን ማለት ነው። ከአህምሮአዊ እውቀት ወይም አቀባበል በላይ ማለት ነው። ፒስቲስ የመወሰን ትርጉምም አለው። የዚህ የፒስቲስ እምነት ያለው አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር እውነት መሆኑን ጥልቅ በሆነ የልብ መሰጠት በመግባባት የተቀበለና በልበ ሙሉነት የሚጠብቅ ወይም እንደሆነ አድርጎ የደመደመ ሰው ማለት ነው።
የዕብራዊያን ፀሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። (ወደ ዕብራውያን 11: 1) ይላል። የዚህ ዓይነት እምነት ለእግዚአብሔር መንግስት የተገባና ለመንግስቱም የመገበያያ ገንዘብ ነው።
ሰማያዊው ሀገር አሁን ባይታየንም ሀገር ሲሆን መገበያያውም እምነት ነው። በዚህ ዓለም ገንዘብ ሳይኖረን አንድ ነገር መግዛት እንደማንችል ሁሉ ካለእምነት ከሰማያዊ መንግስት ንጉስ ጋር ግንኙነት አይኖረንም ማለት ነው። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ተብሎ እንደተፃፈ።
የማታምነውን ነገር ለመቀበል አትችልም የማትጠባበቀውንም ነገር ለማየት አትችልም። ታዲያ ይህ እምነት የሚገበያየው ተስፋ ባደረገው ላይ በሚኖረው እምነት ነው። የሰው ልጅ በተፈጥሮ አንድን ነገር በመገመት (predict በማድረግ ወይም ይሆናል በሚል) አውጥቶና አውርዶ ስለ አንድ ነገር ይወስናል። እምነት ያለው ሰው ግን ግምትን አይጠቀምም ይልቁንም እንደሚሆን ቆጥሮ በዛ ጉዳይ ላይ ይወስናል እንጂ። እግዚአብሔር ያደርገዋል የሚል የእምነት ገንዘብ መጠን አለው።
ሙሴ በንጉስ ፈርዖን ቤት እንደ ልዑል አድጎ ነገር ግን መፅሐፍ እንደሚል በእምነት ስሌት ልጅ መባልን አልፈለገም።
ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤ ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።
ዕብ 11፥24-26
እምነት ያለው ሰው በሚያየው ሳይሆን በሚያምነው ይኖራል። ሙሴ መጨረሻውን በእምነት አይቶ ጊዜአዊ ጥቅሙን ተው። አዎ ሙሴ እምነቱ ገንዘብ ሆነለት አሻግሮ መመልከት ስለቻለ መግዛት ያለበትን ገዛ። በምድር ላይ በሚያየውን ሳይሆን በእግዚአብሔር እውነተኛነት በእርሱም የተስፋ ቃሎች ላይ የተመሰረተ እምነት የነበረው ለእግዚአብሔር መንግስት የመግዛት አቅም እንዲኖረው አደረገ። እምነት ያሰላል!!!
ኖህንም ብንመለከት
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
ዕብ 11፥7
እግዚአብሔር መርከብ እንዲሰራ ሲያዘው ኖህ አንድም የዝናብ ጠብታ ሳያይ ነው መርከብ የሰራው። በጠራራ ፀሐይ መርከብ ሲሰራ ያዩት ሁሉ እንደ እብድ ሳይቆጥሩትም አልቀሩ። እንኳን መርከብ ይቅርና ዝናብ ይዘንባል ብለህ ተማምነህ ዣንጥላ ይዘህ ሲያዩህ እንደታመምክ ሊቆጥሩህ ይችላሉ። ኖህ እነሱ የማያውቁትን እሱ በእርግጠኝነት አውቋል። ምክንያቱም እምነቱ ተስፋ የሚያደርገውን እውነት በእምነት ስሌት አስልቶ ገዝቶት ነበረና። እምነት ያሰላል።
በብዙ ችግር ውስጥ ያላችሁ፣ ተስፋ የምታደርጉት የማይመስል ለሆነባችሁ፣ በይሆናልና አይሆንም መካከል ውስጥ ለተቀመጣችሁ፣ አሁን በዓለም በምታዩት ነገር ተወስዳችሁ ብሩኩ ተስፋችንን የዘነጋችሁ እምነት ያሰላል። በማስላት ወደሚገኝ ክብር የሚያመጣ በእምነት መገበያያ ገንዘብ እንያዝ አላለው። በድጋሚ እምነት ያሰላል።
ደግሞም በኑሮአችሁ ሰልፍ በዝቶባችሁ ላላችሁ፣ አንዳች ነገር እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቃችሁ መልስ በመጠበቅ ላይ ላላችሁ፣ በእግዚአብሔር በረከት ላይ ሳይሆን በበረከቱ አምላክ፣ በበረከቱ ሰጭ፣ ወይም በበረከቱ ምንጭ እግዚአበሔር ላይ ባለ እምነት ላላችሁ ይህ የመንግስቱ መገበያያ ገንዘብ እንዳይባክን ፀንታችሁ እንድትቆዩ እያሳሰብኩ በእምነት የገዛችሁት ይሆናል፣ በእርግጥ እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ያደርገዋል። በእምነት አስልታችሁ በያዛችሁት ተስፋ እንድትፀኑም ምክሬ ነው። በእምነት ማስላት መኖራችሁን ቀጥሉበት አላለው።
እምነት ያሰላል!!!
ይህን መልእክተ እኔ ፃፍኩት እናንተም አንብባችሁ ሼር በማድረግ ሌሎች እንዲማሩበት እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር እጠይቃለው። ቪዲዮውን መመልከት አይርሱ። እኔ ተባርኬበታለው እናንተንም ይጠቅም ዘንድ እነሆ ጋበዝኳችሁ። ለመጠቀምም ለመጥቀምም ሆናችሁ ትመለከቱት ደግሞም የእግዚአብሔር ቃል ሊነግረን በፈለገው መጠን መረዳት ይሆንላችሁም ዘንድ ፀሎቴ ነው።
የዕብራዊያን ፀሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። (ወደ ዕብራውያን 11: 1) ይላል። የዚህ ዓይነት እምነት ለእግዚአብሔር መንግስት የተገባና ለመንግስቱም የመገበያያ ገንዘብ ነው።
ሰማያዊው ሀገር አሁን ባይታየንም ሀገር ሲሆን መገበያያውም እምነት ነው። በዚህ ዓለም ገንዘብ ሳይኖረን አንድ ነገር መግዛት እንደማንችል ሁሉ ካለእምነት ከሰማያዊ መንግስት ንጉስ ጋር ግንኙነት አይኖረንም ማለት ነው። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ተብሎ እንደተፃፈ።
የማታምነውን ነገር ለመቀበል አትችልም የማትጠባበቀውንም ነገር ለማየት አትችልም። ታዲያ ይህ እምነት የሚገበያየው ተስፋ ባደረገው ላይ በሚኖረው እምነት ነው። የሰው ልጅ በተፈጥሮ አንድን ነገር በመገመት (predict በማድረግ ወይም ይሆናል በሚል) አውጥቶና አውርዶ ስለ አንድ ነገር ይወስናል። እምነት ያለው ሰው ግን ግምትን አይጠቀምም ይልቁንም እንደሚሆን ቆጥሮ በዛ ጉዳይ ላይ ይወስናል እንጂ። እግዚአብሔር ያደርገዋል የሚል የእምነት ገንዘብ መጠን አለው።
ሙሴ በንጉስ ፈርዖን ቤት እንደ ልዑል አድጎ ነገር ግን መፅሐፍ እንደሚል በእምነት ስሌት ልጅ መባልን አልፈለገም።
ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤ ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።
ዕብ 11፥24-26
እምነት ያለው ሰው በሚያየው ሳይሆን በሚያምነው ይኖራል። ሙሴ መጨረሻውን በእምነት አይቶ ጊዜአዊ ጥቅሙን ተው። አዎ ሙሴ እምነቱ ገንዘብ ሆነለት አሻግሮ መመልከት ስለቻለ መግዛት ያለበትን ገዛ። በምድር ላይ በሚያየውን ሳይሆን በእግዚአብሔር እውነተኛነት በእርሱም የተስፋ ቃሎች ላይ የተመሰረተ እምነት የነበረው ለእግዚአብሔር መንግስት የመግዛት አቅም እንዲኖረው አደረገ። እምነት ያሰላል!!!
ኖህንም ብንመለከት
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
ዕብ 11፥7
እግዚአብሔር መርከብ እንዲሰራ ሲያዘው ኖህ አንድም የዝናብ ጠብታ ሳያይ ነው መርከብ የሰራው። በጠራራ ፀሐይ መርከብ ሲሰራ ያዩት ሁሉ እንደ እብድ ሳይቆጥሩትም አልቀሩ። እንኳን መርከብ ይቅርና ዝናብ ይዘንባል ብለህ ተማምነህ ዣንጥላ ይዘህ ሲያዩህ እንደታመምክ ሊቆጥሩህ ይችላሉ። ኖህ እነሱ የማያውቁትን እሱ በእርግጠኝነት አውቋል። ምክንያቱም እምነቱ ተስፋ የሚያደርገውን እውነት በእምነት ስሌት አስልቶ ገዝቶት ነበረና። እምነት ያሰላል።
በብዙ ችግር ውስጥ ያላችሁ፣ ተስፋ የምታደርጉት የማይመስል ለሆነባችሁ፣ በይሆናልና አይሆንም መካከል ውስጥ ለተቀመጣችሁ፣ አሁን በዓለም በምታዩት ነገር ተወስዳችሁ ብሩኩ ተስፋችንን የዘነጋችሁ እምነት ያሰላል። በማስላት ወደሚገኝ ክብር የሚያመጣ በእምነት መገበያያ ገንዘብ እንያዝ አላለው። በድጋሚ እምነት ያሰላል።
ደግሞም በኑሮአችሁ ሰልፍ በዝቶባችሁ ላላችሁ፣ አንዳች ነገር እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቃችሁ መልስ በመጠበቅ ላይ ላላችሁ፣ በእግዚአብሔር በረከት ላይ ሳይሆን በበረከቱ አምላክ፣ በበረከቱ ሰጭ፣ ወይም በበረከቱ ምንጭ እግዚአበሔር ላይ ባለ እምነት ላላችሁ ይህ የመንግስቱ መገበያያ ገንዘብ እንዳይባክን ፀንታችሁ እንድትቆዩ እያሳሰብኩ በእምነት የገዛችሁት ይሆናል፣ በእርግጥ እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ያደርገዋል። በእምነት አስልታችሁ በያዛችሁት ተስፋ እንድትፀኑም ምክሬ ነው። በእምነት ማስላት መኖራችሁን ቀጥሉበት አላለው።
እምነት ያሰላል!!!
ይህን መልእክተ እኔ ፃፍኩት እናንተም አንብባችሁ ሼር በማድረግ ሌሎች እንዲማሩበት እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር እጠይቃለው። ቪዲዮውን መመልከት አይርሱ። እኔ ተባርኬበታለው እናንተንም ይጠቅም ዘንድ እነሆ ጋበዝኳችሁ። ለመጠቀምም ለመጥቀምም ሆናችሁ ትመለከቱት ደግሞም የእግዚአብሔር ቃል ሊነግረን በፈለገው መጠን መረዳት ይሆንላችሁም ዘንድ ፀሎቴ ነው።
አጽናኑ
'' አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ። ''
ኢሳ 4፥1
በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምናነበው እስራኤል በባቢሎን ለሰባ ዓመታት በምርኮ ስትወድቅ ከፍተኛ መንፈሳዊ ክስረት ደርሶባታል። በዚህም ምክንያት በንጉስ ሰለሞን በከበሩ ድንጋዮች የተሰራው ቤተመቅደስ በባቢሎናዊያን በመቃጠሉ መቅደስ አልባ ለመሆን ችለዋል። የእግዚአብሔር ታቦትም ተማረከ፣ ብዙ መጻህፍትም በእሳቱ ተቃጠሉ። ሌሎችም ክስረቶች ደርሶባቸው ነበር እናም የደረሰባቸውን መከራና የነፃነት እጦት ምክንያት ተስፋ ወደ መቁረጥ በመድረስ
'' መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ''
(ትንቢተ ኢሳይያስ 40: 27) በማለት አጉረመረሙ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሰሚ ነው ታምፆበትም ይሰማል። እርሱ ታማኝ እረኛ ነው ሕዝቡን አልተወም አጽናኝ ነብያትን በመላክ ሕዝቡን ያጽናና ነበር። ከላይ ከጠቀስነው ከኢሳያስ ምዕራፍ አርባ በኋላ የነበሩት ትንቢቶች ስለ ነፃ አውጪው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሲህነት ነው። እስራኤልም መሲሁን በተስፋ ይጠብቁት ነበር። ነገር ግን መፅሐፍ እንደሚል
'' የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። '' (የዮሐንስ ወንጌል 1: 11)
ዛሬ በዘመናችን የሰው ልጅ በልዩ ልዩ ምርኮ ውስጥ ወድቋል መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ ለኋጢአት ሞቶ ደግሞም እኛኑን ስለማፅደቅ በመነሳት የምስራች እየተነገረ ባለበት በዚህ ዘመንም የሰው ልጅ በሌሎች ነገሮች ተማርኳል። ዘመኑ በቴክኖሎጂ የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰበት በመሆኑ ሰዎች በቀላሉ መረጃ የሚያገኙበት ዘመን ላይ እንገኛለን።
ከዚህም የተነሳ ራሱንና አጠገቡ ያለውን በመዘንጋት የሩቁን የመረጃ ዜናዎች በመስማትና በማንበብ ተጠምዶአል። አብዛኞቹ የመረጃ መገናኛ አውታሮች ትኩረት የሚስብ ትኩስ ዜና ካጡ ስራ የሰሩ አይመስላቸውም። መልካሙን እየተዉ የጭንቀት ወሬ ለማግኘት የሚያነፈንፉ ብዙዎች ናቸው። አንድ አደጋ ወይም ጦርነት ወይም አንዳች እልቂት ያለበት መረጃ ካገኙ ሁሉም ያንኑ ክፉ ወሬ እንደ በግ ሲያመነዥጉት ይሰነብታሉ። የሚያጽናናም ሆነ የሚያንጽ ወሬ የሚነገርበት ወይም የሚነበብበት የመረጃ አውታሮች እጅግ ጥቂት ናቸው።
አሁን ሁላችንም ማለት በሚቻል ሁኔት በሞባይል ስልካችን ኢንተርኔትን በመጠቀም ለመረጃ ቅርብ ነን። በተለይ በFacebook። ወደዚህ መንደር የገባን እንደሆን ብዙ አሉባልታ ያለበት ዜና እንደአሸን የፈላ ነው። ድሮ ሐሜት አለ ተብሎ የምንሰማው ቡና ሲጠጣ ነበር አሁን ግን በፈረደበት በFacebook ሆኗል። በግለሰቦች ደረጃ የነበረው ሐሜትና ውሸት አድጎ ብሔራዊ ብሎም ኢንተርናሽናል አድርገነዋል። በጣም የሚገርመው በፊት ብና እየተጠጣ ያለ ክፍያ የሚወራው ወሬ ዛሬ ላይ ኢንተርኔት ለመጠቀም ገንዘብ አውጥተን ካርድ በመግዛት በጀተኛ ሐሜተኞች ሆነናል።
ስለ ሰዎች ክፋትና በደል ብዙ የሚፃፍበት ነገር ግን ስለ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ጥቂት መፃፍ የሚያሰተችበት ዘመን ላይ ነን። ስለ ሰዎች ማንነት ለሰዓታት እናወራለን ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱስ ይዘን አንድ ምዕራፍ ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ መነጋገር አቅቶናል።
የአንድን የእግር ኳስ ብድን ተጫዋቾች በሙሉ ከነመለያ ቁጥራቸው ሸምድደን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የተነገሩበትን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ግን አንብበን የማናውቅ እንኖራለን።
እግዚአብሔር ፈቅዶለት ጸጋውም አስችሎት ጥቂት የሚፅፈውን ወይም የሚመሰክር ሲመጣ የሀሰት ስም በመለጠፍ የተፃፈው አጀንዳ ተረስቶ ወደ ሰውዬው ማንነት Divert ያደርጋል። የጉብዝናዬ ወራት ሳያልፍ ፈጣሪዬን ላስብ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ቃል ያዘነበለን ሰው በመከፋፈልና በማሳት ወደ ፀብና ትችት እንዲያደላ የምናደርገው ለምንድነው?
በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር አንድ ጊዜ አንድ የራሴን ፎቶ በዚሁ የFacebook Wall ላይ ለጠፍኩኝ እናም የሚያውቁኝ ሁሉ የተለመደውን Like አልፎ አለፎም Comment አደረጉ በሚቀጥለው ቀን ግን አንድ የእግዚአብሔር ቃል ከነጥቅሱ ለጠፍኩኝ እነዛ Likeዎች ድራሻቸው ጠፋ ምክንያቱም ከእኔ ባሻገር ያለውን መልእክት መመልከት ስላልቻሉ። ከላይ የጠቀስኩት መከፋፈል ያመጣው መዘዝ መሆኑ ነው።
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አራት ቁጥር ስድስት ላይ በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙዎች ናቸው ይላል። ብዙዎች ለዚህ ለሚያልፈው ዓለም ሳይሆን ከጌታ ጋር ዘላለም የምንኖርበትን መንገድ ማወቅ ይሻሉ። እርስ በእርሳችን በፍቅር እንደ እግዚአብሔር ቃል ካልተገሳጸጽን፣ ተስፋ የቆረጠውን ካላጽናናን እንዴት የጌታ ፍቅር ገባን ልንል እንችላለን?
በዚህ ቃል ተጽናኑ (1ኛ ተሰ 4፥18)
እግዚአብሔር በልጁ በክርሰቶሰ ኢየሱስ ያመንን ሁላችን እርስ በራሳችን እንድንጽናና ይፈልጋል። እንድንደጋገፍ አንዱ ለሌላው አበርታች እንድንሆን ይሻል። ታዲይ ምንድነው የምንጠብቀው? ጥፋት ያለበት አንድ ሰው ቢገኝ ቃሉ እንደሚያዘው በየዋሃት መንገድ ማቅናት አንድም እሱን ለመጥቀም አንድም እኛም እንዳንሰናከል ለምን እንደ ቃሉ አንሆንም?
አጽናኙ ለዘላለም ከእኛ ጋር ነው።
(ዮሐ 14፥15-16፣ ዮሐ 14፥26፣ ዮሐ 15፥26)
የሚያጽናናን የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ተልኮልን ለእርሱ እንዳንገዛ አዚም ያደረገብን ማን ነው? መሲሁ ክርስቶስ ስለእኛ መስዋህት ሆኖልን የእኛ መዘናጋት ጤነኝነት አይደለም። ለእስራኤል የተላኩት የምርኮ ዘመን ነብያትን ነው ለእኛ ግን ታላቅ አጽናኝ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። እጅግ እድለኞች ነን። መጽናናት ይሁንልን።
ይህንን ፅሁፍ ላነበባችሁ በሙሉ አንዳችን ለአንዳችን መኖር ይገባልና በሰው ልብ ውስጥ ጥላሸት ከምንቀባ አንድ የእግዚአብሔር ቃል ተናግረን ሰውን አጽናንተን በብሩኩ ተስፋችን በጌታ ኢየሱስ ላይ ባለ እምነት እንዲኖር የሁልጊዜ ኑሮአችን እናድርግ እላለው። የማንችል ነን ብላችሁ ለመሞከር በፍርሃት ያላችሁ አዎ ሁላችን አንችልም ነገር ግን የሚያስችል ፀጋ በሚያስፈልገን ጊዜ ይሰጠናልና። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚል '' ሰው በኋይሉ አይበረታምና '' በራሳችን ሳይሆን በፀጋው ላይ በመውደቅ የሚገኝ አገልግሎት ይኖረን ዘንድ ሰዓቱ አሁን ነው። አረፈደም ዘመኑ ካመጣው መንፈሳዊ ክስረት እንውጣ።
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የእግዚአብሐር አብ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ህብረት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።
ሼር
የሚታይ እምነት
በእግዚአብሔር ቅዱስ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት የውስጥን ከሚያውቀው ከእርሱ በቀር ማንም ሊይውቅ አይችልም። እርሱ ዓይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል የሚያበሩ ልብና ኩላሊትን የሚመረምሩ፣ ስለ ሰዎች ሊነገረው የማይገባ ሁሉን የሚያውቅ ከልባችን ይልቅ ታላቅ የሆነ እርሱ ብቻ ነው። ሰው ስራን ወይም ውጫዊ የሆነውን ድርጊት ብቻ ያያል እርሱ ግን የልባችንን ያውቃል። ቃላት ሳንተነፍስ መልስ የሚሰጥ ቸር እረኛ ነው።
እምነት በስራ ይገለጣል ነገር ግን በስራ መገለጡ የሚጠቅመው መልሶ ራሳችንን ወይም በዘንዳችን ያሉትን ሰዎች ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለ እኛ ለማወቅ ብሎ የሚፈትነን ነገር የለም። እርሱ አስቀድሞ አውቆናልና። ይልቅስ እምነታችን እንዲታይ የሚፈለግበት ምክንያት ከላይ የጠቀስኩት የራሳችንን እምነት ጥንካሬ እንድንፈትሽ ወይም የእምነታችንን አነሳሳሽ ምክንያት በእኛ እንዲገለጥ እና ለሌሎች ምሳሌ እንድንሆን ነው።
አብርሃም ልጁን ይስሀቅን እንዲሰዋ እግዚአብሔር ሲያዘው እግዚአብሔር አብርሃም በእምነት እንደሚታዘዝ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም። ኢዮብን ሰይጣን እንዲፈትነው እግዚአብሔር የፈቀደው የኢዮብን መታመን ሳያውቅ ቀርቶም አይደለም። ነገር ግን እነዚህ ሁለቱ የእምነት ሰዎች በእግዚአብሐር ላይ ምን ያህል እንደተደገፉ ራሳቸው አያውቁም ነበረ። ሰይጣን ኢዮብን ስለባረከው ነው እግዚአብሔርን የተከተለው በማለት ከሰሰና ተፈቀደለት። ተፈተነም ብዙ ነገሩን አጣ ነገር ግን ኢዮብ በበረከቶቹ ላይ ሳይሆን በበረከቶቹ አምላክ እምነት እንዳለው እርሱም አወቀ እኛም ይኧው እየተማርንበት እንገኛለን። የሚታይ እምነት አሳየ።
በማርቆሰ ወንጌል ምዕራፍ ሁለት ከቁጥር አንድ እስከ አምስት ድረስ ያለውን ብንመለከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን በማየት ኋጢአት ሲያስተሰርይ እናነባለን።
ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ። በደጅ ያለው ስፍራም እስኪጠባቸው ድረስ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ቃሉንም ይነግራቸው ነበር። አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት። ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡ፥ ነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን። አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።
(ማር 2፥1-5 )
የማርቆስ ወንጌል ክርስቶስን እንደ አገልጋይ አድርጎ የሚያሳይ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። በዚህ ምዕራፍ ውስጥም በአንድ ቤት ውስጥ እንዴት ባለ ትህትናና ዝቅታ ጌታ ኢየሱስ ያስተምር እንደነበር ያሳያል። እነዚህ አራት ሰዎች እርሱ ያገለግል ወደ ነበረበት ቤት ሲመጡ መግቢያ መንገድ ባለመኖሩ አልተመለሱም። እርሱን እንጂ እርሱ ከገባበት ቤት ጋር ጉዳያቸውን አላዛመዱም፣ ግድግዳ አልዳበሱም፣ የገባበትን መንገድ የረገጠውን መሬት አላሉም፣ ኋጢአተኛ የሚያስፈልገው መድሃኒት እርሱ ኢየሱስ ጋር ብቻ ሲደርስ እንደሆነ አምነዋል። ማድረስ የነበረባቸው አካል ጋር አደረሱት ተፈወሰም። የሚከተሉትን ደቀ መዛሙርትን እንኳ ጥሩልኝ አላሉም ምክንያቱም ኋጢአት ሊነፃ የሚችለው በጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው ስሙ ይቀደስ። የሚታይ እምነት ይሏል ይህ ነው።
ጌታ ኢየሱስ ጋር ለመድረስ ማድረግ ያለባቸውን አደረጉ በሩ ቢጨናነቅም ጣራ አንስተው ከላይ ወደ ታች ሽባውን አስገቡት እርሱም ስራቸውን ሳይሆን እምነታቸውን በማየት የሽባውን ልጁ ኋጢአት ይቅር አለ። አዎ እኛ የአራቱን ሰዎች ስራ ላይ ትኩረት እናደርግ ይሆናል እርሱ ግን እምነትን ያያል። እኛ ልፋታቸውን አይተን ክንፈረ እንመጥ ይሆናል ነገር ግን እርሱ የመጡበትን ዓላማ ያውቃል።
እነዚህ አራት ሰዎች ተሸክመው በማምጣት ኋጢአተኛውን ከመድሃኒቱ ጋር አገናኙ። ዛሬ ላይ የክርስቶስ ኢየሱስ ነን እያሉ መንገድ የዘጉ ብዙዎች አሉ። በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባላቸው እምነት ሳይሆን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ወይም ስርአት ተመርኩዘው እነሱም ሳይደርሱ ሰውንም ተሸክመው ሳያደርሱ በር ዘግተው የተቀመጡ ብዙዎች አሉ። እኛስ የቱ ጋር ነን? ራሳችንን እንፈትሽ።
አብዛኛው ህዝብ እረፍት ፍለጋ ሲባዝን እያዩት የተስፋውን ቃል ከመንገር ይልቅ በሃይማኖታዊ ካባ ሽፋን በሁከት ድምፅ እያሸበሩ ከመድሃኒቱ ጋር እንዳይገናኝ ታክል የሆኑ ብዙዎች አሉ። እኛስ የቱ ጋር ነን?
እርሱ ሁሉ አዋቂ ነው። አሁን እንኳ ይህን እየፃፍኩ እናንተም እያነበባችሁ በምን ዓይነት ልብ እንዳለን ያውቃል። ተሽክሙ ጣራ አንሰተው ነድለውም በሽተኛን ወደ መድሃኒቱ የሚያመጡበት ባለበት ስፍራ እንኳ ተቃዋሚዎች ነበሩ። ኋጢአትህ ተሰረየችልህ ስላለው ስለምን እንዲህ ያለ ስድብ ይሳደባል ነበር ያሉት። ዛሬም በማያልፍ የሕይወት ኋይል በግርማው ቀኝ የተቀመጠውን ጌታ ጋር ሰዎች እንዲደርሱ ሰዎችን መሸከም አለብን። የሚታይ እምነት ይኑረን እርሱ አሁንም የልባችንን ያያል። አዎ
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።
(ዕብ 13፥8)
በእርሱ ዘንድ የሚታይ እምነት ይጨምርልን። የጌታ ኢየሱስ ሰላምና ፍቅር ይብዛላችሁ። አሜን።
ያ ሰው
ያ ሰው እኔ ነኝ የበደልኩትኝ
ያ ሰው ኢየሱስ ነው እኔን ያዳነኝ
እኔ:-
ንጉስ ዳዊት ኣሪዮንን ካስገደለ በኋላ እግዚአብሔር በናታን በኩል ተናገረው ላደረገውም ኋጢአትን የመሸፈን ስራ ለራስህ ብዙ ሰጥቼ ሳለ አንተ ግን አልበቃህ ብሎ የሰውን ወሰድክ። ላደረከውም ክፉ ስራ ሌላ የበደል ካባ ደረብክ፣ የሰጠውህ አንሶም ከሆነ እጨምርልህ ነበር ነገር ግን አልጠየከኝም ብሎ ዳዊትን ወቀሰው። ሁለተኛ ሳሙኤል ምዕራፍ አስራ ሁለት ከቁጥር 1-7 እንዲህ ይላል:-
እግዚአብሔርም ናታንን ወደ ዳዊት ላከ ወደ እርሱም መጥቶ አለው። በአንድ ከተማ አንዱ ባለጠጋ አንዱም ድሀ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ። ባለጠጋውም እጅግ ብዙ በግና ላም ነበረው። ለድሀው ግን ከገዛት አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፤ አሳደጋትም ከልጆቹም ጋር በእርሱ ዘንድ አደገች፤ እንጀራውንም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥ በብብቱም ትተኛ ነበር፥ እንደ ልጁም ነበረች። ወደ ባለጠጋውም እንግዳ በመጣ ጊዜ ከበጉና ከላሙ ወስዶ ለዚያ ወደ እርሱ ለመጣው እንግዳ ያዘጋጅለት ዘንድ ሳሳ፤ የዚያንም የድሀውን ሰው በግ ወስዶ ለዚያ ለመጣው ሰው አዘጋጀ። ዳዊትም በዚያ ሰው ላይ እጅግ ተቈጥቶ ናታንን። ሕያው እግዚአብሔርን! ይህን ያደረገ ሰው የሞት ልጅ ነው። ይህን አድርጎአልና፥ አላዘነምና ስለ አንዲቱ በግ አራት ይመልስ አለው። ናታንም ዳዊትን አለው። #ያ_ሰው_አንተ_ነህ።
አዎ ያ ሰው አንተ ነህ አለው። በራሱ ላይ የፈረደ በሰው ሲሆን በደሉ የገባው ራሱን በጉዳዩ ውስጥ ሳይመለከት በሰው ውስጥ ሲሆን የነገሩን ታላቅነት ተረዳ ፈረደም። እግዚአብሔር በምሳሌ ንጉስ ዳዊትን ገሰፀው። እኔም በዚህ የታሪክ ክፍል ብዙ ተማርኩ ጉዳዩን ወደ ራሴ አመጣሁት። እኔስ ብሆን ብዬ ራሴን በዚህ ታሪክ ውስጥ አገኘው።
ያ ሰው እኔ ነኝ። ሁሉ ተሰጥቶኝ፣ የጎደለብኝ ሳይኖር በክቡር የክርስቶስ ደም ተገዝቼ፣ ውድ ዋጋ ወጥቶብኝ ሳለ ነገር ግን እኔ በበደሌና በኋጢአቴ ሙታን ነበርኩኝ፣ የሥጋዬንና የልቡናዬን ፈቃድ እያደረኩ በሥጋ ምኞት በፊት እኖር ነበር፣ ከፍጥረቴ ጀምሮ የቁጣ ልጅም ነበርኩ። በአለመታዘዝ ጠንቅ የጠፋው፣ በዓለም ተወስጄ ከእግዚአብሔርም ክብር ጎድዬ ከመንፈሱ እርቄ የምኖር ተቅበዥባዥ ነበርኩ። መንፈሳዊ ካባ ደርቤ፣ ለሚያየኝ አማኝ መስዬ፣ የራሴን የመዳን መንገድ ፈፅሜ ቤዛዬ ላይ ደርቤ፣ ከበደልና ከኩነኔ የሚያነፃውን ክቡር ደሙን አክፋፍቼ የነበረ፣ አዎ ያ ሰው እኔ ነኝ። ነገር ግን.........
ኢየሱስ:-
በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት። በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው። ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ኢየሱስ። ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።
ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።
እርሱ ግን። #ያዳነኝ_ያ_ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
ዮሐ 5፥2-11
አዎ ጌታ ኢየሱስ በድካሜ የሚራራ መልካሙ እረኛዬ፣ የዓለምን ኋጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፣ ክብሩን እንደመነጠቅ ሳይቆጥር ከዙፋኑ ወርዶ እንደ እኔ ሰው ሆኖ፣ ከባዱን ሸክሜን ሊሸከም፣ ስለ ኋጢአቴ ልከፍለው የሚገባውን የመስቀል ሞት ስለእኔ ሊሞት፣ የእኔን መራራ ፅዋ ሊጠጣ ራሱን አሳልፎ የሰጠው የእኔ አዳኝ፣ የዓለም ቤዛ ያዳነኝ ያ ሰው ኢየሱስ ነው።
ሰው የለኝም ብሎ የነበረው ድውዩም እውነተኛውን ኋጢአት የሌለበት፣ ነውር የማያውቀው፣ ስለ እኛ የመጣውን ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ አገኘው ዳነም። ዛሬም እኔ ከዘመናት በፊት በከፈለልኝ ውድ ዋጋ ድኛለው። በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው ቤዛነት በኩል በፀጋው ሕያው ሆኛለው። እረ እኔስ ሰው አለኝ። የዘላለም ሊቀካህኔ ኢየሱስ፣ በእኔና በእግዚአብሔር መካከል ያለ መካከለኛዬ፣ እረ እኔስ ሰው አለኝ።
ማሳሰቢያ:-
ይህን ፅሁፍ ላነበባችሁ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን ሳትዘነጉ መሆን ይኖርበታል።
የጌታ ፀጋና ሰላም ለሁላችን ይብዛልን አሜን።
ቆራሌው
ከልጅነታችን ጀምሮ የቆራሌን ድምፅ በመስማት አድገናል። ገና ከሩቅ ሆኖ '' ቁራሌው አሮጌ ጫማ ያለው '' እያለ ሲጮህ ሰምተናል። አንዳንዴ ጠብቁት ተብለን አልያም ሲመጣ ጥሩን ተብለን የቆራሌውን ድምፅ ለመስማት ጆሮዎቻችንን አንግበን የጠበቅንበት ጊዜአትም አሉ።
ቆራሌው ሰዎች የተጠቀሙበትን አሮጌ እቃ በየሰፈሩና በየመንደሩ በመግባት እየሰበሰበ በርካሽ ዋጋ የሚገዛ እግረ ቀጭን ሰው ነው። ይጠቅመኛል ያለውን እቃ እየመረጠ የሚስማማውን ዋጋ በመጥራት ይደራደራል። ቆራሌው ከሚደራደርበት መንገድ አንዱ የሚገዛውን እቃ ማጣጣል ነው። የማይጠቅም አድርጎ ወይም በጣም የተጎዳ በማድረግ በሚፈልገው ዋጋ ለመግዛት የሚጠቀምበት ስትራቴጂ ነው።
ሻጭም ስለገዛ እቃው የነበረውን ግምት ወይም ዋጋ በማሳነስ በቀላሉ ለቆራሌው በአነስተኛ ዋጋ ይሸጣል። የሰው ልጅም አእምሮው ትንሽ ያረገውን ነገር ለመተው አይቸገርም። የማይጠቀምበትን እቃዎች በሙሉ እንደ ቅራቅንቦ በመቁጠር አሳልፎ የባለቤትነት መብት ለቆራለው ይሰጠዋል።
የሰው ልጅ በክርስትና ሕይወቱ የሚፈትኑት ሶስት ነገሮች አሉ። እነዚህ በሕይወቱ ሁሉ ጠላቶቹ የነበሩና አሁንም ድረስ ያሉ የዘላለም ጠላቶቹ ናቸው።
1) ሀሰተኛ የሀሰት አባት ዲያቢሎስ
2) ይህ የምንኖርበት ዓለም
3) ተሸክመን የምንዞረው ስጋችን ወይም የሰጋ ሰሜት ናቸው።
እኛ ሰዎች ከፍተኛ ውጊያ የምናደርገው አእምሮአችን ውስጥ ነው። እነዚህ ከላይ ያየናቸው ደግሞ ሀሳባችንና እንቅስቃሴአችንን በመቆጣጠር ሰው ከተፈጠረበት ዓላማ ውጪ እንድንሆን ያደርጉናል። ከእውነት ይልቅ በምናየውና በአእምሮአችን የእውቀት ደረጃ መጠን ብቻ ነገሮችን እንድናይ ይገፋፉናል። ሶስቱም በጌታ ያለውን ሰላም እንዳንይዝ፣ እረፍት እንዳይሰማን፣ ንስሀ እንዳንገባ በመከላከል የሚያጠቁን የፅድቅ ጠላቶቻችን ናቸው።
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ።
ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።
ሮሜ 8፥5-8
ይህ ያልተቤዠው ስጋችን ከቀድሞው ጠላት ዲያብሎስ ምክር በመቀበልና በክፉ ከተያዘው ከዚህ ከአሁኑ ዓለም በሚያየውና በሚሰማው እየተታለለ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን እንቅፋት ይሆንብናል። ወደ እግዚአብሔር ፍፁም ሙላት እንዳንደርስ የሚጎትት የሞት ሀሳብ ወደ ልባችን ሹክ የሚል እንቅፋት ነው። የበደለኝነት ስሜት እንዲሰማን በማድረግ ከእግዚአብሔር ይቅርታ እንዳንጠይቅ በደላችን በደልን ከሚያነፃ ከክርስቶስ ደም የላቀ እንዲመስለን የሚያደርግ የክፉት ሽኩሽክታ ነው።
ይህ የስጋ ስሜት የሚሰማው ድምፅ አለ የወቃሽ ድምፅ። እንደ ቆራሌው አሮጌውን ማንነት የሚያስታውስና ወደ ኋላ የሚጎትት ድምፅ። ልክ እንደ ቆራሌው የመግዣ ስትራቴጂ ያጣጥልሃል፣ ለራስህ ያለህን ዋጋ እንዳታስተውል የኋጢአትህን መአት ያዥጎደጉድልሃል፣ ራስህን በመውቀስ የኩነኔ ስሜት እንዲሰማህ ያደርግሃል፣ ስለአንተ የፈሰሰ ደም እንዳለ ያስረሳሃል፣ ኋጢአትህ የማይነፃ እስኪመስልህ ድረስ ዋጋ ቢስ ያደርግሃል፣ በሕይወትህ ተስፋ በማስቆረጥ የፅድቅ ወጋገንን ይሸፍንብሃል፣ የኢየሱስ ክብር ደም ከኋጢአት ሁሉ እንደሚያነፃ ከህሊናህ ውስጥ ይሰውራል።
'' አንተ እኮ እንዲ አድርገሃል እንዴት ንስሀ ትገባለህ ''
'' የአንተ በደልማ ይቅርታ አያሰጥም ''
'' አሁን አንተ ነህ ክርስቲያን የምትሆነው '' በማለት ይወቅሳል። ነገር ግን መፅሐፍ እንደሚል
ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?
ዕብ 9፥14
ከምን ያህል የሞተ ስራ ህሊንችንን የሚያነፃ የኢየሱስ ደም ብቃት እንዳለው ይናገራል። ከየትኛውም በደልና ኋጢአት የሚያነፃ ውድ ደም አለ። ለዚህም ነው የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኋጢአት ሁሉ ያነፃል ተብሎ የተፃፈው።
ስለዚህ ተወዳጆች ኢየሱስ የሞተው ስለኋጢአታችን ነው። እርሱ ህሊናን ከሞተ ስራ ያነፃል። መንፈሳዊ ቆራሌው የሚለውን አትስሙ። እርሱ ሊሰርቅ ሊያርድ እንጂ ስለሌላ አልመጣምና '' ቆራሌው በደለኛ ስሜት ያለው '' ሲላችሁ በኢየሱስ ስም ተቃወሙት። ክፉውን ተቃወሙት እርሱም ከእናንተ ዘንድ ይሸሻል ተብሎ ተፅፏልና።
የቱንም ያህል በደል ቢኖርብን ሁሌ ለጥቅማችን የሚጠራን ድምፅ አለ። በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ ይከተሉኝማል እንዳለ ጌታ ይህን ድምፅ ብቻ መስማት ይሁንልን። እናንተ ደካሞች ሸከማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለው የሚል ብርቱ ድምፅ አለ።
አሮጌ እቃ የሚገዛው እግረ ቀጭኑ ቆራሌው አሮጌዎቹን ሰብስቦ ጥቂትም ቢሆን ብር ከፍሎ ይሄዳል ይሄኛው መንፈሳዊ ቆራሌ ግን ያለመታከት የሚሰራ ኩነኔ ወይም የባሰ የበደለኝነት ስሜት ጨምሮ የሚሄድ አፍዝ አደንግዝ የዘላለም ጠላታችን ነው። ራሳችንን በማርከስ አእምሮችንን አንስጥ፣ አንገዛለት አላለው። ይህን እንድናደርግ በሚያስፈልገን ጊዜ ሁሉ የሚረዳን የእግዚአብሔር ፀጋ ሁላችንንም ይርዳን አሜን።
የማንቂያ ደውል (wake up call)
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።
ሮሜ 6፥23
ኩነኔ የለበት በክርስቶስ ላለ
እዳው በአንዱ ጌታ ስለተከፈለ
በፅድቅ ልንኖር ለኋጢአት ሞተናል
ማህተሙን ይዘን ማንስ ይከሰናል
የበጉ ደም ነክቶን ማን ይቋቋመናል።
ሌላ አንድ የለም
ዶሮ ታርዳ በብልት በብልት አስራ ሁለታ ቦታ ከመገነጣጠሏ በፊት አንድ ዶሮ ተብላ እንደምትጠራ ሁሉ የዚህ ፅሁፍ ርዕስም አንድ ራሱን የቻለ መልእክት ያለው ሲሆን እንደ ዶሮ ብልት ስንገነጣጥለው ሶስት ራሳቸውን የቻሉ ወሳኝና ቆራጥ መልእክት አዘል ያነገቡ ርዕሶች ይወጡታል። እነሱም
ሌላ \
አንድ } አትኩሮት የሚሹ ወሳኝ ጉዳዮች
የለም /
ሌላ
ሌላ የሚለው ቃል በአብዛኛው የሚያተኩረው አማራጭ ስለሆነ ጉዳይ ነው። '' ሌላ '' ያለበት ዐረፍተ ነገር የአንድን ድርጊት ውስንነት ወይም ገደብ የለሽነት በጉልህ የሚያሳይ ቁርጥ ያለ ውሳኔን ያመለክታል። ለምሳሌ ያህል ሰይጣን ''ሌላ'' በሚለው ቃል መፅሐፍ ቅዱስ ሲገልፀው እንዲህ ይላል
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤
ዮሐ 10:፥10
በዚህ ቃል ውስጥ የሰይጣን ዓላም በግልጽ ተቀምጧል። ሰይጣን በእኛ ላይ ከዚህ ውጪ ምንም ዓይነት ተልዕኮ የለውም። ሊያጫውትህ፣ ሊያዝናናህ፣ ሊያዳብርህ፣ ወይም በሕይወትህ የምትፈልገውን ሊሰጥህ አይመጣም። እሱ ሌባ ነው ይሰርቃል፣ ያርዳል፣ ያጠፋል ሌላ ተግባርም ሆነ ምግባር የለውም። ስለ ሰይጣን ከዚህ ውጪ የተረዳ ሰው ካለ '' ሌላ '' የሚለው ወሳኝ ቃል አመለካከቱን ቆርጦ ይጥለዋል ምክንያቱም የጌታ ቃል እጅግ ግልፅ በሆነ መልኩ ተናግሯልና።
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ '' ሌላ '' በሚለው ቃል ጋር አያይዞ ከብዙ በጥቂቱ በእንዲህ ይገልፀዋል።
መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።
ሐዋ 4፥12
እዚህ ጋር መፅሐፍ ቅዱሳችን በአፅንዎት እንደገለፀው የመዳን ብቸኛ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ ሌላን ሁለት ጊዜ ተጠቅሞበታል፣ አንድም ከኢየሱስ ውጪ የመዳን ጉዳይ ታሳቢ እንዳላይደለና በማንም ሊሆን እንደማይችል፣ አንድም ሌላ ከእርሱ ውጪ እኛ ልንጠቀምበት የሚገባ ስም እንደሌለ። በአጭሩ ከእርሱ ውጪ አዳኝ እንደሌለ '' ሌላ '' የሚለው ቃል ይገልፅልናል። ኢየሱስ ክርስቶስ አማራጭ የሌለው ብቸኛ ምርጫ ነው። አዎ ኢየሱስ ብቸኛ አዳኝ፣ ኢየሱስ ብቸኛ ቤዛ ነው።
ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
1ኛ ቆሮ 3:፥11
ማብራራት በማይጠይቅ ሁኔታ እዚህ ጋርም መፅሐፍ ቅዱሳችን '' ሌላ '' በሚል ቃል አዘል ኢየሱስን ምርጫ የለሽ ብቸኛ ጉዳያችን እንደሆነ ዳግም በአትኩሮት ገልፆታል።
ታዲያ ከእኛ ምን ይጠበቃል? መፅሐፉ ስለእኛም '' ሌላን '' ተጠቅሞ እንዲህ ይለናል
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤
ዮሐ 10፥1
ኢየሱስ ራሱን ብቸኛ ከሰማይ የመጣ እውነተኛ መንገድ መሆኑን በተለያየ ምሳሌዎች ነግሮናል። ለዚህም እርሱን ብቻ መንገድ አርገን ሕይወታችንን ማቅናት አለብን። በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሎናል። ከእርሱ ውጪ መንገድ አደላድለን ከሆነ መንገዳችንን ማቅናት ይኖርብናል። ወንበዴነታችንን ወደነው ካልሆነ በቀር ብቸኛ መንገዳችን የቃሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
'' ሌላ '' የሚለው ቃል ከኢየሱስ ውጪ እንዳናይ፣ እንዳናስብ፣ እንዳንመለከት፣ እንዳንሻም ያሳስባል።
አንድ
በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቁጥርን ወይም ብዛት ለማመልከት ከተጠቀሰበት ዓላማ ውጪ መንገድን፣ ሁኔታን፣ ትዕዛዝን፣ ፍቃድን ወይም የእግዚአብሔር ሀሳብ በግልፅ ከማስቀመጥ አንፃር '' አንድ '' ተብሎ በተነገረባቸው ቦታዎች ሁሉ እግዚአብሔር በቃሉ ምን ያህል ሊያሳስበን እንደፈለገ በቀላሉ መረዳት እንችላለን። አንድ የሚለው ቃል የሚያሳየው ከምርጫ ውጪ የሆነን ነገር በብቸኛነት የሚያጠቁም ወይም የሚያሳይ ወሳኝ ቃል ነው።
ይህ ''አንድ'' የሚለው ቃል በሕይወታችን ውስጥ ትርጉም የሚሰጥና ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር የሚያግባባን መሰረታዊ ቃል ነው። መፅሐፍ እንደሚል በአንዱ መተላለፍ ኋጢአት በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ነገሰ ሞትንም አስከተለ ነገር ግን በአንዱ በኢየሱስ መታዘዝ ሕይወት ሆነልን (ሮሜ 5፥12-17)።
ሰው ከኋጢአትና ከዘላለም ሞት እንዲድን እግዚአብሔር ያዘጋጀው የመዳን መንገድ አንድ ልጁ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው እንደ ዮሐንስ ወንጌል 14፥6 መሰረት። በሌላ በኩል
ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤
1ኛ ጢሞ 1፥15
ከዚህ የምንረዳው ማንም ከኢየሱስ በቀር የእኛን ኋጢአት ሊያስቀር ወደዚህ ዓለም የመጣ እንደሌለ ነው። የዓለምን ኋጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ተገለጠ የተባለለት እርሱ ብቻ ነው። ለዚህም በተደጋጋሚ ክርስቶስን በብቸኛነት '' አንድ '' በማለት ይገልፀዋል። ለምሳሌ ያህል:-
=}} አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ (2ኛቆሮ 5፥14)
=}} ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሰጠ (ማር 10፥45/1ኛ ጢሞ 2፥6)
መፅሐፍ ቅዱሳችን '' አንድ '' ሲል ሌላ እንደሌለ ልንረዳ ይገባል። እኛን በተመለከተ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል
ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥
ሮሜ 3:፥11
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
ሮሜ 3፥23
ሁሉ የሚለው ቃል ውስጥ አንድ እንኳ መምዘዝ አንችልም መፅሐፉ በድግግሞሽ በማሳሰብ ዘግቶታል። ሁሉም የሰው ዘር በሙሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ክቡር ደም መቤዥት አስፈልጎታል። ከእግዚአብሔር ክብር ጎድለን የነበርነውን እርሱ መልሶልናል። ከኋጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን የመሰለው ጌታችን ኢየሱስ በመካል የነበረውን የጥል ግድግዳ ያፈረሰ እርሱ ብቻ ነው። ይህንንም መፅሐፍ ሲናገር
አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
1ኛ ጢሞ 2፥5
ቃሉ በአፅንሆት እንደገለፀው በመካከል ያለው አንድ ብቻ ነው እዚህ መካከለኛ ላይ መጨመርም ሆነ ከተጠቀሰው መካከለኛ ሌላ መፈለግ አይቻልም። ሰው ያሻውን ይጨምር ይሆናል በእግዚብሔር ዘንድ ግን ተቀባይነት የለውም።
አንድ ጌታ ኢየሱስ አለኝ ክርስቶስ አለኝ
ነፍሴን ነፍሱ ያደረገልኝ የሚዋጋልኝ
ማይፈታ ምይተሜ ነው ደሙ
ከፍ ላርገው አርማዬ ነው ስሙ
የለም
ይህ ቃል በአጭሩ የሚያስረዳው ከላይ ካየናቸው ሁለት ወሳኝ ጉዳዮች ውጪ ሌላ እንደሌለ ነው። አዎ ሌላ አንድ የለም። መፅሐፉ ካስቀመጠልን መዳኛ ውጪ ሌላ አንድስ እንኳ የለም። ትርፉ ጉንጭ ማልፋት እንጂ ።
መዳን ከኢየሱስ ውጪ በሌላ በአንድስ እንኳ የለም (ሐዋ 4፥12)። እርሱ ብቸኛ መዳኛ ነው። ከእርሱ ሌላ አምባ የለም ማንም የለም ማንንም አላውቅም ይላል እግዚአብሔር እኛስ?
እኔ በበኩላ
የለም ሌላ ስም ሌላ መዳኝ
ከሰማይ በታች መተማመኛ
ከቤዛዬ፣ በድካሜ ከሚራራልኝ ሊቀካህኔ፣ ደሙ ዘላለም ከሚያነፃ ከኢየሱስ ውጪ ሌላ አንድ የለም ብያለው። እናንተስ?
እግዚአብሔር ሁሌም መልካም ነው
በመልካም ሁኔታ ውስጥ ሆነን እግዚአብሔርን ማመስገን ተለማምደን ይሆናል ችግር ወይም መከራ ውስጥ ገብተን ግን ብዙ ጊዜ ማመስገን ይከብደናል። ችግር ወይም መከራ የእግዚአብሔርን መልካምነት አያጎድልም። እርሱ ሁልጊዜ ከመልካምነት አይጎድልም ስሙ ብሩክ ይሁን።
እግዚአብሔር በእምነት እንድናድግ በፈተና ውስጥ ያሳልፈናል። እምነት ደግሞ ካልተፈተነ ብርታቱ ወይም ጥንካሬው አይታወቅም። ወርቅ በእሳት ካልተፈተነ እንዲል መፅሐፍ ቅዱሳችን የሰው ልጅም እንዲሁ ነው። እርሱ በትንሹ ሲፈትነን ለትልቁ እያዘጋጀን እንደሆነ መዘንጋት የለብንም። በፈተና ውስጥ በእምነት እንድናድግ እንጂ እንድንወድቅ ከቶ አይፈልግም። ይልቁንስ በእርሱ አብልጠን እንድንደገፍ ወይም እንድናምን በፈተና ውስጥ ያስተምረናል።
ታዲያ እግዚአብሔር እኛን እየፈተነ ባለበት ሁኔት ውስጥ ሆነን መልካሙነቱ መናገር የምንችልበት እምነት አለን ወይ? ብለን ራሳችንን መጠየቅ ብልህነት ነው። ይህን ካደረግን በእውነት እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ዓላማ እውን ሆኗል ማለት ነው።
ኢዮብ የነበረውን አጥቶ፣ ጤናው ተቃውሶ ሰውነቱ በቁስል ሲወረር ሚስቱ እግዚአብሔርን እርገምና ሙት ባለችው ጊዜ የመለሰው መልስ ለእግዚአብሔር የሚገባው ምስጋና ነበር።
ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን? አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።
ኢዮ 2፥10
አዎ ብዙ መልካም ነገሮች ተቀብለን በአንድ ትንሽ ጊዜአዊ ችግር ምክንያት እግዚአብሔርን ከማማረር የሚጠብቅ የእርሱ ጸጋ ሁላችንንም ይርዳ። በተሰጠን በረከት ላይ ሳይሆን በበረከቱ አምላክ ላይ ልበ ሙሉ እምነት ይኑረን። ኢዮብ የነበረውን ሳይሆን ሰጪውን አሻግሮ ተመልክቷል። እምነቱም በእርሱ ላይ ብቻ ነበረ። በነዛ ሁሉ ችግሮች ውስጥ ሆኖ እንኳ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ነው ያለው። በችግር ውስጥ ሆኖ ባረከ። ኢዮብ በችግሩ ኋይለኛነት ሳይሆን እምነቱን ባሳረፈበት አምላክ ኋይል ተማርኳል። አንድ ደስ የሚለኝ አባባል አለ:-
'' ለእግዚአብሔር የችግርህን ታላቅነት አትንገር
ለችግርህ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ንገረው ''
እግዚአብሔር ሲሰጥም ሲነፍግም ትክክል ነው መልካምም ነው። የማይጠቅመንን ነገር በመከልከል ይጠብቀናል የሚያስፈልገንን ነገር ሳንነግረው የሚያውቅ እርሱ በራሱ የጊዜ ሰሌዳ ያከናውንልናል ይሰጠንማል። አዎ እግዚአብሔር መልካም ነው።
ችግርን ለጥቅማችን ያመጣዋል ከችግር መውጫንም እርሱ ያዘጋል እግዚአብሔር እጅግ መልካም ነው።
እግዚአብሔር በእምነት እንድናድግ በፈተና ውስጥ ያሳልፈናል። እምነት ደግሞ ካልተፈተነ ብርታቱ ወይም ጥንካሬው አይታወቅም። ወርቅ በእሳት ካልተፈተነ እንዲል መፅሐፍ ቅዱሳችን የሰው ልጅም እንዲሁ ነው። እርሱ በትንሹ ሲፈትነን ለትልቁ እያዘጋጀን እንደሆነ መዘንጋት የለብንም። በፈተና ውስጥ በእምነት እንድናድግ እንጂ እንድንወድቅ ከቶ አይፈልግም። ይልቁንስ በእርሱ አብልጠን እንድንደገፍ ወይም እንድናምን በፈተና ውስጥ ያስተምረናል።
ታዲያ እግዚአብሔር እኛን እየፈተነ ባለበት ሁኔት ውስጥ ሆነን መልካሙነቱ መናገር የምንችልበት እምነት አለን ወይ? ብለን ራሳችንን መጠየቅ ብልህነት ነው። ይህን ካደረግን በእውነት እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ዓላማ እውን ሆኗል ማለት ነው።
ኢዮብ የነበረውን አጥቶ፣ ጤናው ተቃውሶ ሰውነቱ በቁስል ሲወረር ሚስቱ እግዚአብሔርን እርገምና ሙት ባለችው ጊዜ የመለሰው መልስ ለእግዚአብሔር የሚገባው ምስጋና ነበር።
ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን? አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።
ኢዮ 2፥10
አዎ ብዙ መልካም ነገሮች ተቀብለን በአንድ ትንሽ ጊዜአዊ ችግር ምክንያት እግዚአብሔርን ከማማረር የሚጠብቅ የእርሱ ጸጋ ሁላችንንም ይርዳ። በተሰጠን በረከት ላይ ሳይሆን በበረከቱ አምላክ ላይ ልበ ሙሉ እምነት ይኑረን። ኢዮብ የነበረውን ሳይሆን ሰጪውን አሻግሮ ተመልክቷል። እምነቱም በእርሱ ላይ ብቻ ነበረ። በነዛ ሁሉ ችግሮች ውስጥ ሆኖ እንኳ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ነው ያለው። በችግር ውስጥ ሆኖ ባረከ። ኢዮብ በችግሩ ኋይለኛነት ሳይሆን እምነቱን ባሳረፈበት አምላክ ኋይል ተማርኳል። አንድ ደስ የሚለኝ አባባል አለ:-
'' ለእግዚአብሔር የችግርህን ታላቅነት አትንገር
ለችግርህ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ንገረው ''
እግዚአብሔር ሲሰጥም ሲነፍግም ትክክል ነው መልካምም ነው። የማይጠቅመንን ነገር በመከልከል ይጠብቀናል የሚያስፈልገንን ነገር ሳንነግረው የሚያውቅ እርሱ በራሱ የጊዜ ሰሌዳ ያከናውንልናል ይሰጠንማል። አዎ እግዚአብሔር መልካም ነው።
ችግርን ለጥቅማችን ያመጣዋል ከችግር መውጫንም እርሱ ያዘጋል እግዚአብሔር እጅግ መልካም ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)