ትዕግሥት :- ይቅር ባይ፣ ልበሰፊ ፣ ቻይ ፣ትሁት የሆነ የጠባይ መለያ ነው።
ከሰው ጋር ከግንኙነት ነፃ በማንሆንበት በዚህች ዓለም ስንኖር አስፈላጊ ነገር ከሆኑት መካከል አንዱ ትልቁ ትዕግሥት ነው። በዚች ምድር ሰፊውን የሕይወታችንን ክፍልንም የሚይዘው ነገር ደግሞ ግንኙነት ነው። ታዲያ በዚህ ሰፊ ግንኙነት ውስጥ ከሚያስፈልገን ነገር አንዱ ይህ ትዕግሥት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ትዕግሥታቸው ከሚጠቀስላቸው ሰዎች አንዱ ደግሞ በሁላችንም ህሊና ውስጥ የሚመጣው ኢዩብ ነው።
''ወንድሞች ሆይ የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነብያትን ተመልከቱ። እነሆ፥ በትዕግስት የጸኑት ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዩብ እንደታገሰ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደፈፀመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።'' (ያዕ 5፥10-11)
በዚህ ቃል መሠረት፥ ከላይ እንደገለፅኩትም ኢዩብ በትዕግሥቱ በሁላችንም ህሊና የማይጠፋና ለብዙ ጊዜያትም በምሳሌነት ሲነሳ የምናውቀው ቢሆንም ኢዩብ በታገሠው ትዕግሥት ከብጹዓን ቢመደብም ድካም ( ስንፍና ) ግን ነበረበት
'' ከዚያም በኋላ ኢዩብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ። ..................'' (ኢዩ 3፥1 ጀምሮ) ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ቃል ሲተላለፍ እና የነበረውን ፅናት ስፍራ አስለቅቆታል።
'' ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመስግንሃለሁ፤ሥራህ ድንቅ ነው፣ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።'' (መዝ 138፥14) የሚለውን ዘነጋና ሞቱን ተመኘ መፈጠሩንም ረገመ። በብዙ ችግር ውስጥ ቢሆንም ግን የትዕግሥት ልኩ ታየ።
ሰ
ትዕግሥት ካደረግን ሊመጣ (ሊፈፀም) የሚችል ታላቅ ኋጢአት ሁሉ በድል የምናልፍበት አቅም እናገኛል። በትዕግሥት ውስጥ በመቆየታችን ለችግራችን የሚሆን የመፍትኤ ሀሳብ ይበዛልናል በመሆኑም ተቻኩለን ከምናደርጋቸው ድርጊቶች ይልቅ በዝግታ አስበን የምናገኘው መፍትሄ የተሻለ ነው።
ማንም እንኳ ኢዮብ ታጋሽ መሆኑን የተመሰከረለት ቢሆንም እንደውም ''ትዕሥት እንደ ኢዮብ ስጠን'' እየተባለ ሲነገር ብንሰማም በእሱ ላይ መቆም እንደሌለብን እሙን ነው ምክንያቱም ኢዩብ ከታገሠው ትዕግሥት የሚልቅ ወይም ከኢዩብ አልፈን ልናወራለት፣ ልንመሰክርለት፣ ልንመለከተው እንዲሁም ልናስተውለው የሚገባን ሌላ ታጋሽ አለን። ሌላ ልናወራለት የሌለ የትዕግሥት ጥግ አለን። ኋጢያት የማያውቀው ወደር የሌለው የትዕግሥት ምሳሌ አለን።
'' ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋይ የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋሪያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤ '' (ዕብ 3፥1) ተብሎ እንደተፃፈ፥ ስለ ትዕግሥት ስናስብ ከኢዩብ የሚበልጠውን የኢየሱስ ክርስቶስን ትዕግሥት መርሳት የሌለብን።
(የመልእክቴም ዋና ሀሳብ ይህ ነው) ስለ ሁላችን ኃጢአት ሳይገባው መከራን ሲቀበል፣ በሌለበት በደል ሲከሰስ በሸላቾች እንደሚታረድ በግ ዝም ሲል፣ በቁስሉ ቁስላችንን ሲያክም፣ በቀራኒዮ በደሙ ሲዋጀን፣ በእርጥብ እንጨት ላይ በችንካር ሲሰቃይ፣ በተጠማው አንጀቱ ሆምጣጤ ሲጠጣ፣ እንደ ወንበዴ በመስቀል ሲሰቀል፣ በበደልና በኋጢአታችን ሙታን የነበርነውን ጽድቃችንም የመርገም ጨርቅ የሆነብን ስለእያንዳንዳችን ሞታችንን በሞቱ በትዕግሥት ሲሽር ከእግዚአብሔር ያጣነውን ልጅነት አስገኘን። ይህም የኢየሱስ ፍቅር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ያሳየናል እንድም አፀፋ ሳይመልስ ሁሉ ታግሶ መዳናችንን ፈፅሞልናል።
'' የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቁጠሩ '' (2ኛ ጴጥ 3፥15)
ሰለዚህም ዩሐንስ በፍጥሞ ደሴት ሳለ '' መከራውንና መንግስቱን የኢየሱስ ክርስቶስን ትዕግሥት የምካፈል'' እንዳለው ልንካፈለው የሚገባን የትዕግሥት ጥግ ከኢዩብ የላቀውን፣ አልፈን የማናወራለትን የኢየሱስን ትዕግሥት ሊሆን ይገባል።
ደዊት 2008 የምህረት ዓመት የተፃፈ
No comments:
Post a Comment