የተሀድሶ ቤተክርስቲያን የተነሳባትን ነፋስ ንጹዉን ወንጌል ሰባኪነቷን ጥላሸት የሚቀቡባት ላይ እንደ ቃሉ የሆነ አጸፋዊ መልስ ልትሰጥ ይገባል። በእርግጥ በየአጥቢያው የተደረጉ እንቅስቃሴዎችና የማጽኛ ፕሮግራሞች እንደነበሩ ባውቅም በቂ ነው ብዬ አላስብም። ስለሆነም በሰሞኑ የወንጌል እንቅሳቃሴን የመረበሽ ተግባርን በተመለከተ በጉባኤያት ብቻ ሳይሆን በዚህ ስሟንና ተግባሯን እያቀለሉ በሚያሰራጩቧት በማህበራዊ ሚዲያ ምዕመኗቿም ጭምር ተሀድሶአዊውን የወንጌል እንቅስቃሴን የተከበረውን ስሟንና ስራዋን ኢየሱስን በመስበክና በስሙ የሚመጣውን ማንኛውንም ተግዳሮት ተጋፍጣ በወንጌል እንቅስቃሴ ፊታውራሪ ልንሆን ይገባል።
የዳንበትን ቅዱስን ወንጌል ያለ ሽቀጣ የሰማንበትን ብዙ የሕይወት መስዋህትነት የተከፈለበትን የከበረው የወንጌል እንቅስቃሴ ዛሬ ላይ በተወሰኑ በአገልግሎቱ ውስጥ በነበሩ ሰዎች በግል ባላቸው ፍላጎትና ችግር የተነሳ ወዳልተገባ ስም ማጥፋትና አገልግሎቱን ወደ ማርከስ እንዲሁም ወደ ማቃለል እንቅስቃሴ ውስጥ እንደገቡ የአደባባይ ሚስጢር ነው። ለእነዚህ ሰዎች ምህረትን እየለመንን ለአገልግሎቱ ደግሞ ብርታት እንዲጨምር መትጋት ይኖርብናል። ስደትና ወታወክ(መበታተን) ሲፈጥር የምናውቀው ወደ ተሻለ አገልግሎት ነውና (ሐዋ 8) አንፍራ።
እናም ይህ መጥፎና አደገኛ ወደ እያንዳንዱ ማህበረ ምዕመናን ቤት እየገባ በተለይም ከቅርብ ጊዜአት ወዲህ ለወንጌል ልባቸውን ከፍተው መሰራት ለጀመሩ ወንድምና እህቶች ልባቸው በብዙ ስለተጎዳና ስለተከፈለ ቤተክርስቲያናትም ሆነ ልጆችዋ እንዲሁም በዚህ የወንጌል እንቅስቃሴ ቃሉን በመስማት ያተረፋችሁ በሙሉ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ከፍ ብሎ የተነሳውን የሰውን ሀሳብ በማፍረስና ለክርስቶስ ኢየሱስ መታዘዝም አእምሮን ሁሉ ወደሚማርክ ዘመቻ ከሁላችሁ እጅግ የማንስ እኔ እንድትገቡ ላነቃ እወዳለው።
ወንጌልን ከየትኛው ጊዜ በበለጠ ሊሰበክ ይገባዋል እግዚአብሔርም በነገር ሁሉ በእርግጥ ይረዳናል። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። (ዕብራውያን 4፥16)
No comments:
Post a Comment