የኢየሱስ የክብሩ ወንጌል የሚሰበከው ወንጌሉ ራሱ በሚሰጠው አቅምና ጸጋ ነው። አሁን አሁን እያየን ያለነው ከጸጋው ውጪ በውሸትና በማስመሰል ወንጌል እንሰራለን የሚሉ መበራከታቸው ነው። ወንጌል ቀጥተኛ መንገድ ይፈልጋል ይህም ኢየሱስን ብቻውን በመግለጥ በጨለማ ላሉት ብርሃን እንዲበራላቸው ወንጌሉ ራሱ የሚጠይቀውን መንገድ መከተል። ሐዋርያት በእጃቸው የተቀበሉትን ይህን ቅዱስ ወንጌል ያበዙት በቀጥተኛ መንገድ እስከ ሕይወት መስዋህትነት በመክፈል ነው። በዚህ ሁሉ ግን ወንጌልን ለጥቅማቸውና በግል ፍላጎታቸው ተነድተው እንዳላገለገሉ ለማንም ግልፅ ነው። ለዛም ነው የሕይወት መስዋህተንት ያስከፈላቸው።
እንደዘመኑ አገልጋዬች ቢሆኑ በአይሁድ መቅደስ ገብተው ራሱን በመሰዋት ለዓለም ያበረከተውን ቅዱሱን ደም በማክፋፋት የኮርማና የበግ ጠቦት መስዋህት እያቀረቡ፣ አይሁድ እንዳይከፋው ኢየሱስ በበረት የተወለደ የዮሴፍ ልጅ ነው እያሉ ወንጌልን እንሰብካለን ቢሉ ዛሬ ላይ ንጹህ ወንጌል ባላየን ነበር።
ሰሞኑን በዚህ '' ለአገልግሎት ነው '' በሚል ካባ የተሸፈኑ የተወሰኑ አገልጋዬች የኢየሱስን ብቸኛ የአዲስ ኪዳን መካከለኝነትንና ሊቀካህንነት ዝቅ በማድረግ ፍጡራንን በእርሱ ቦታ በመተካት ወደ ሚነገርበት አገልግሎት ፈቀቅ የማለታቸው ሚስጢር ይህ ስጋና ደም የፈጠረው የማምለጫና ማታለያ መንገዳቸው '' ለአገልግሎት ነው '' የሚል ከባድ የዓለም መንገድ ነው።
ኢየሱስ በእነሱ አባባል ለጊዜው ብቸኛ መድኃኒት አይደለም። ሌሎች ፍጡራንና መላእክት በእርሱ ቦታ ተተክተው ወንጌል ተሸቃቅጦ ይሰበካል፣ የሚያገለግሉት ሕዝብም እንዳይከፋው መዝሙርና ምስጋና ይቀርብላቸውል ለምን? መልሳቸው '' ለአገልግሎት ሲባል ነው ''።
ሁላችት የተዋጀነበትን ቅዱስ ደም ወደ ጎን በመተው መጽሐፍ ቅዱሳችንም በግልፅና በብቸኝነት የነገረንን (የኢሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል) የሚለውን ችላ በማለት እልፍ መንገድ እንዳለ ወደሚነገርበት ምኩራብ መግባት ይህም የፈረደበት '' ለአገልግሎት ነው '' የሚል ታፔላ ነው።
ቦታና ጊዜ የማይወሰንለት በእውነትና በመንፈስ የሚመለከው ጌታ እግዚአብሔርን በሁሉም ስፍራ ሆኖ ፀሎትንና ምስጋናን የሚቀበል ሆኖ ሳለ ከሞቱ በኃላ ወደ ሚዘምርላቸው እንዲሁም እንዲማልዱ ወደ ሚፀለይላቸውና ለእግዚአብሔር የሚደረገውን አምልኮታዊ ስርአት አንዳች ነገር ሳይቀነስባቸው ተጋርተው ወደሚሰጣቸው ድንኳን መግባት ብልሃት የተፈጠረው ይህ '' ለአገልግሎት ነው '' የሚል አመክንዬ ነው።
ኢየሱስ የሚለውን ስም ብቻውን መጠራት የለበትም ድስት እንኳ ሁለት ጆሮ አለው ብለው ከሚያስቡ ጋር ገብተው ''ኢየሱስ'' ላለማለት ወልድ ብለው መናገር መጀመራቸውን ሳይ ለአገልግሎት ነው? ብዬ ለማሰብ ሞከርኩ በረገጡት ጫማ ራሴን ከትቼ ለማየት ተጣጣርኩ ግን ሊዋጥልኝ አልቻለም። ወልድ ማለት በራሱ ችግር አለው እያልኩ አይደለም ግን ወልድ ያሉት ኢየሱስ ላለማለት እንደሆነ በግልፅ ሳላየው ነው።
የግድ ለመመሳሰል ዮሐንስ አፈወርቅ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እያሉ ጥሩ ጥሩ የሚመስሉ አባባሎችን እየተጠቀሙ ተሀድሶአዊያንን ላለማስከፋት፣ ተቀባይነት ለማግኘት ኦርቶዶክሳዊያንን ማስደሰት ደግሞም እግዚአብሔርንም ላለመበደል በሚደረግ ፍልሚያ ውስጥ እንዳሉ የተረዱት አልመሰለኝም።
ከእግዚአብሔር በላይ ይራራሉ ከሚባሉት ከሰው አልፈው ሰይጣንን ከሚያሞነኩስና ከእግዚአበሔር ጋር ሊያስታርቁ ከሚወዱት ጋር ኢየሱስን እንዴት ባለ መንገድ ሊሰብኩት እንደፈለጉ አልገባኝም። ሰው የጎረቤቱን ቤት ሰርቶ ነው እንዴ የራሱን የሚሰራው? ምናለ ብትተዋቸው? የተሀድሶ አገልግሎት በሁለት እግሮቹ እንዳይቆምና ያስተማረቻቸውን አቅፋ ረዥም ርቀት እንዳትጓዝ ካደረጉት አንዱ ምክንያት ሌላ ቤት ላይ ተታኮ የሚደረገው እንቅስቃሴ ነው። እስከ መቼ ነው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ጫንቃ ተላቆ ይህን አገልግሎት ለማስፋት አንድነት የማይፈጠው?
እረ ስንቱን ልናገር በጌታ.......... በጣም ከገረመኝ ነገር አንዳንዶች በዚህ መንገድ ብዙ ዓመት ያስቆጠሩና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለረዥም ዓመት ተቀጥረው ያሉ ዋጋ እየከፈሉ እንደሆነ የሚናገሩት ነገር። በዚህ መንገድ የሚከፈል ዋጋ እኔ ሊታየኝ አልቻለም ቅዱሱ መጽሐፍም ይህንን አካሄድ ሲደግፍም ሆነ ሲያበረታታ አላየሁም አልሰማሁም። ዋጋ አለን ካሉም እንደኔ እንደኔ ደሞዛቸውን ይቁጠሩ ደግሞስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብቻ ለምን ታያቸው? ይህ አካሄድ ለምን መስጂድ አይሰራም? ጂሆቫ ጋርና ካቶሊክ ቤተ እምነት ውስጥስ ለምን አይሞክሩትም?
ነገ የምናፍርበትንና የማያዋጣንን መንገድ ዛሬ አንጠቀም!
No comments:
Post a Comment