Sunday, 28 August 2022

ከጸሎት እስከ ጸሎት 

 


 

እንደተጠመቀ ከወንዝ እንደወጣ

የምወደው ልጄ የሚል ድምፅ መጣ

ልብሱ እንደረጠበ ገና ሳይደራርቅ

ጌታዬ ጸልዮ ሆነ ተአምር ድንቅ

ሰማይ ተከፈተ ታይቶ የማይታውቅ 

ተልዕኮን በጸሎት ጀምሮ የዘጋ

ይተጋ ነበረ መሽቶ እስኪነጋ

ማዳኑን ሲፈፅም እንኳ በመስቀል ላይ

አላቋረጠውም ወደ አብ መጸለይ 

ጎኑ እየተወጋ እየፈሰሰው ደም

አባቱን ማናገር እርሱ አላቋረጠም 

ውሃ ጥም ያልገታው 

ሆምጣጤ ያላስቆመው

አባቱ ሲጨክን መጣራት ያልተወው 

ለሰቀሉት ሰዎች ፈፅሞ የራራው

ኢየሱስ ብቻ ነው

ሕይወቱን በትጋት ፍፁም አደረገው

በፀሎት ጀምሮ በፀሎት ጨረሰው


ተፃፈ:- ዛሬ

No comments:

Post a Comment