Sunday, 28 August 2022

ከጸሎት እስከ ጸሎት 

 


 

እንደተጠመቀ ከወንዝ እንደወጣ

የምወደው ልጄ የሚል ድምፅ መጣ

ልብሱ እንደረጠበ ገና ሳይደራርቅ

ጌታዬ ጸልዮ ሆነ ተአምር ድንቅ

ሰማይ ተከፈተ ታይቶ የማይታውቅ 

ተልዕኮን በጸሎት ጀምሮ የዘጋ

ይተጋ ነበረ መሽቶ እስኪነጋ

ማዳኑን ሲፈፅም እንኳ በመስቀል ላይ

አላቋረጠውም ወደ አብ መጸለይ 

ጎኑ እየተወጋ እየፈሰሰው ደም

አባቱን ማናገር እርሱ አላቋረጠም 

ውሃ ጥም ያልገታው 

ሆምጣጤ ያላስቆመው

አባቱ ሲጨክን መጣራት ያልተወው 

ለሰቀሉት ሰዎች ፈፅሞ የራራው

ኢየሱስ ብቻ ነው

ሕይወቱን በትጋት ፍፁም አደረገው

በፀሎት ጀምሮ በፀሎት ጨረሰው


ተፃፈ:- ዛሬ

እንኳን መረብ ጾም አደረ!

 



ሌሊቱን በሙሉ ስንደክም አደርን

ምንም ነገር ሳንይዝ እንዲሁ ባከንን 

ነገር ግን ጌታዬ አንተ ካለህበት

መረቡ ይሞላል ቃልህን ስታዝበት


እንኳን ለፍተን አደርን እንኳን መረብ ጾም አደረ

ዓሣው ተትረፍርፎ እስኪቀደድ ድረስ መች እናጠምድ ነበረ

አንተን የታዘዘ በረከቱ ይበዛል

ባዶ እጁን ቢያድርም ሞልቶለት ይውላል 


ከምንም ከሁሉም ትበልጥብኛለህ 

ያለኝን አስጥሎ ያስከትላል ስምህ 

ሳልበላው ሳልሸጠው ያጠመድኩትን 

አስትቶኛል ስራህ ገዝቶታል ልቤን 


ተፃፈ :- ዛሬ

ቀላል ነው!!!

 



ግጥም

ኃጢአት ለከበደው 

መሸከም ላቃተው

ቀንበሩ የለዘበ ሸክሙ የቀለለ

ፍፁም የሚያሳርፍ ወደኔ ኑ ያለ

ለሁሉ የሚያስብ አሸካሚ አለ 

ተፃፈ:- ዛሬ

መሸክም ሁሌም አለ ግን ጥያቄው የተሸከምነው ምንድነው የሚለው ነው? 

እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። (ማቴ 11፥28-30)