ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌ 2፥4-5
Thursday, 25 April 2019
መካከለኝነቱ አላበቃም።
አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤ (1ኛ ጢሞ 2፥5-6)
መታረቃችን በሞቱ
መዳናችን በሕይወቱ
ኢየሱስ የማዳንን ስራ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ፈፅሟል ነገር ግን ዛሬም ድረስ ህያው ነው። የዛሬ 2011 ዓመት የተሰራው ስራ አሁንም ትኩስነቱ እንዳለ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር መታረቃችን በኢየሱስ ሞት አንድ ጊዜ የተጠናቀቀና የተፈጸመ ቢሆንም መካከለኛነቱ ግን ዛሬም ድረስ ነው ወደፊትም ይኖራል።
በእርግጥ ክርስቶስ ኢየሱሰ ዛሬ ስለመታረቃችን አንዳች የሚያደርገው ስራ የለም። በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ያለው ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ቀደሙት የብሉይ ካህናት ዕለት ዕለት ስለ በደልና ስለ ኃጢአት የሚሆን ማናቸውንም ዓይነት መስዋዕት አያቀርብም። ለመስቀል ሞት ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታልና። ስለዚህ የክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ የተጠናቀቀ ነው ማለት ነው። ይህ ማለት መካከለኝነቱ ተጠናቋል ማለት ነውን? አይደለም!!! መጽሐፍ እንዲህ ይላል
" ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን " (ሮሜ 5፥10)
መታረቃችን በሞቱ መዳናችን ግን በሕይወቱ ነው። ለመታረቃችን መካከለኛ የነበረው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ለሰዎች መዳን መካከለኛ ነው።
ሐዋርያው ሲናገር ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት። (ዕብ 8፥1-2)
በዚህ በማያልፍ ሕይወት ኃይል በመልከ ጸዲቅ ሹመት የዘላለም ሊቀ ካህን በሆነበት ሰማያዊ አገልግሎቱ ነው ሰዎች የሚድኑት። የማዳኑ ስራው ከማያልፈው ሕይወቱና በግርማው ዙፋን ቀኝ ካለው ሰማያዊ አገልግሎቱ ጋር የተወዳጀና የተቆራኘ መሆኑ ግልፅ ነው።
አሁንም ሐዋርያው በዚህ ከሰማያዊ አገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ሲመሰክር " ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። " (ዕብ 7፥25) ያለውም ለዚህ ነው።
ሰማይ ስሚ
ምድርም አድምጪ
ትናንት ያዳነን
ዛሬም ነገም የሚያድን ኢየሱስ ብቻ ነው።
"ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። " (ዕብ 13፥8)
Saturday, 6 April 2019
መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት
መጽሐፍ እንደሚል " እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። " (ሮሜ 10፥17) በዚህ መሰረት ካለመስማት የሚጀምር እምነት እንደሌለ እንረዳለን። የወለዱንን ወላጆች ወይም ያሳደጉንን ሰዎች ሃይማኖት በመከተል ልናድግ እንችል ይሆናል ነገር ግን በማስተዋል የእድሜ ክልል ስንደርስ ስለምናምነው እምነት በቂ የሆነ እውቀት ያስፈልገናል። የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ቀጥሎም በማወቅ እምነት እንደሚጀምር ቃሉ በግልፅ ይናገራል። በዘፈቀደ የሚኖር እምነት በእግዚአብሔር ላይ ያለ እምነት ሊሆን አይችልም።
የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት ወደ ጎን ያደረገ ክርስትና ሊኖር አይችልም '' ገንዘብ ላደረገው ሰው፣ እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው '' (ምሳሌ 16፥22)። ጥያቄው ግን '' እውቀት ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም ሳይሆን የያዝነው እውቀት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ወይስ ባህላዊ የአባቶች ወግ ወይስ ስርአት? '' የሚለው ነው። በመሰረቱ እውቀት ሁሉ እውነት አይደለም። ከ2000/ከ3000 ዓመት በላይ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣም ሆነ ትላንት የገበየነው እውቀት፣ የሁለቱም ትክክለኛነት ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር ሲጣራ እንጂ ያ እውቀት ዘመን ስለጠገበ እውነት ሊሆን አይችልም በአንፃሩም ስለዘገየም ውሸት ሊባል አይችልም። እውቀትን እውነት የሚያደርገው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑ ብቻ ነው።
እግዚአብሔርን በተሳሳተ መንገድ የሚያመልኩት ትክክለኛ እውቀት ያላቸው ሳይሆኑ እውቀት የሌላቸው ናቸው ። ጌታ እንዳለውም '' የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል '' (ማቴዎስ 15፥9)። ከንቱ አምልኮ በሰው ስርአት ያለ እውቀት እግዚአብሔርን ማምለክ ነው።
'' እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም '' (ኢሳይያስ 45፥20)።
ያለ እግዚአብሔር ቃል እውቀት ስላሉ ሰዎች መጽሐፍ ሲናገር '' ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአልና '' (ትንቢተ ሆሴዕ 4፥6) እንደሚል ውጤቱ መጥፋት ነው። በመሆኑም በዚህ ሰዓት የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት ችላ ብሎ ነገር ግን ራሱን አማኝ አድርጎ እያሰበ ያለ አይሳሳት። " እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? " (ሮሜ 10፥14) ይላልና #በመስማት_ጀምረህ_እመን የዛሬው ምክሬ ነው።
" የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። " (ቆላ 3፥16)

Subscribe to:
Posts (Atom)